Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម   អាយ៉ាត់:
هَلۡ يَنظُرُونَ إِلَّآ أَن تَأۡتِيَهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَوۡ يَأۡتِيَ رَبُّكَ أَوۡ يَأۡتِيَ بَعۡضُ ءَايَٰتِ رَبِّكَۗ يَوۡمَ يَأۡتِي بَعۡضُ ءَايَٰتِ رَبِّكَ لَا يَنفَعُ نَفۡسًا إِيمَٰنُهَا لَمۡ تَكُنۡ ءَامَنَتۡ مِن قَبۡلُ أَوۡ كَسَبَتۡ فِيٓ إِيمَٰنِهَا خَيۡرٗاۗ قُلِ ٱنتَظِرُوٓاْ إِنَّا مُنتَظِرُونَ
158. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከሓዲያን መላዕክት ልትመጣላቸው ወይንም ጌታህ ሊመጣ ወይም ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ ሊመጣ እንጂ ሌላን ይጠባበቃሉን? ከጌታህ ምልክቶች ከፊሉ የሚመጣበት ቀን ግን ከዚያ በፊት አማኝ ያልነበረች ነፍስ ሁሉ ወይም አምና በእምነቷ በጎ ያልሰራች ነፍስ ሁሉ እምነቷ (ጸጸቷ) አይጠቅማትም:: «ያን ቀን እናንተም ተጠባበቁ እኛም ተጠባባቂዎች ነን።» በላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ فَرَّقُواْ دِينَهُمۡ وَكَانُواْ شِيَعٗا لَّسۡتَ مِنۡهُمۡ فِي شَيۡءٍۚ إِنَّمَآ أَمۡرُهُمۡ إِلَى ٱللَّهِ ثُمَّ يُنَبِّئُهُم بِمَا كَانُواْ يَفۡعَلُونَ
159. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነዚያ ሃይማኖታቸውን ከለያዩና ቡድን ቡድን ከሆኑ (ሰዎች) ጋር አይደለህም:: ነገራቸው ወደ አላህ ብቻ ነው:: ከዚያም ይሰሩት የነበሩትን ሁሉ ይነግራቸዋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مَن جَآءَ بِٱلۡحَسَنَةِ فَلَهُۥ عَشۡرُ أَمۡثَالِهَاۖ وَمَن جَآءَ بِٱلسَّيِّئَةِ فَلَا يُجۡزَىٰٓ إِلَّا مِثۡلَهَا وَهُمۡ لَا يُظۡلَمُونَ
160. መልካምን ስራ የሰራ ሁሉ ለእርሱ አስር እጥፍ ምንዳ አሉት:: ክፉ ስራን የሰራ ግን መሰሏን ብቻ እንጂ አይመነዳም:: እነርሱም ቅንጣት አይበደሉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ إِنَّنِي هَدَىٰنِي رَبِّيٓ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ دِينٗا قِيَمٗا مِّلَّةَ إِبۡرَٰهِيمَ حَنِيفٗاۚ وَمَا كَانَ مِنَ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
161. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ፤ የተስተካከለ ወደሆነው ሃይማኖት የኢብራሂም መንገድ መራኝ:: እሱም ከአጋሪዎች አልነበረም።» በል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحۡيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
162.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «ስግደቴ፤ መገዛቴ (መስዋዕቴ)፣ ሕይወቴ፤ ሞቴ የሚገባው ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَا شَرِيكَ لَهُۥۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرۡتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
163. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ለእርሱ (ለአላህ) አጋር የለዉም:: በዚህ (አላህን ከተጋሪ በማጥራት) ታዘዝኩ:: እኔ የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ።» በል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ أَغَيۡرَ ٱللَّهِ أَبۡغِي رَبّٗا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَيۡءٖۚ وَلَا تَكۡسِبُ كُلُّ نَفۡسٍ إِلَّا عَلَيۡهَاۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُم مَّرۡجِعُكُمۡ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ فِيهِ تَخۡتَلِفُونَ
164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የሁሉ ጌታ ሲሆን ከአላህ በስተቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስ ሁሉ በራሷ ላይ እንጂ ክፉን አትሰራም:: ወንጀለኛ ነፍስ ሁሉ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው:: ከዚያም ትለያዩበት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَهُوَ ٱلَّذِي جَعَلَكُمۡ خَلَٰٓئِفَ ٱلۡأَرۡضِ وَرَفَعَ بَعۡضَكُمۡ فَوۡقَ بَعۡضٖ دَرَجَٰتٖ لِّيَبۡلُوَكُمۡ فِي مَآ ءَاتَىٰكُمۡۗ إِنَّ رَبَّكَ سَرِيعُ ٱلۡعِقَابِ وَإِنَّهُۥ لَغَفُورٞ رَّحِيمُۢ
165. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ (አላህ) ያ በምድር ላይ ምትኮች ያደረጋችሁ በሰጣችሁም ጸጋ ሊፈትናችሁ ከፊላችሁን በከፊሉ ላይ በደረጃዎች ከፍ ያደረገ ሃያል ጌታ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ቅጣቱ ፈጣን ነው:: አላህ እጅግ መሀሪና ሩህሩህ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ