Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម   អាយ៉ាត់:
فَمَن يُرِدِ ٱللَّهُ أَن يَهۡدِيَهُۥ يَشۡرَحۡ صَدۡرَهُۥ لِلۡإِسۡلَٰمِۖ وَمَن يُرِدۡ أَن يُضِلَّهُۥ يَجۡعَلۡ صَدۡرَهُۥ ضَيِّقًا حَرَجٗا كَأَنَّمَا يَصَّعَّدُ فِي ٱلسَّمَآءِۚ كَذَٰلِكَ يَجۡعَلُ ٱللَّهُ ٱلرِّجۡسَ عَلَى ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ
125. አላህ ሊመራው የሚሻውን ሁሉ ልቡን ለኢስላም ይከፍትለታል:: ሊያጠመው የሚሻውን ደግሞ ልቡን ጠባብና ተቸጋሪ ወደ ሰማይ ለመውጣት እንደሚታገል ያደርገዋል:: ልክ እንደዚሁ አላህ በእነዚያ በማያምኑት ሰዎች ላይ ርክሰትን ያደርጋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَهَٰذَا صِرَٰطُ رَبِّكَ مُسۡتَقِيمٗاۗ قَدۡ فَصَّلۡنَا ٱلۡأٓيَٰتِ لِقَوۡمٖ يَذَّكَّرُونَ
126. ይህ ያለህበት መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን የጌታህ መንገድ ነው:: ለሚያስታውሱ ህዝቦች አናቅጽን እርግጥ ዘርዝረናል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ لَهُمۡ دَارُ ٱلسَّلَٰمِ عِندَ رَبِّهِمۡۖ وَهُوَ وَلِيُّهُم بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
127. ለእነርሱም በጌታቸው ዘንድ የሰላም ሀገር አለላቸው። እርሱ ይሰሩት በነበሩት ምክንያትም ረዳታቸው ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَوۡمَ يَحۡشُرُهُمۡ جَمِيعٗا يَٰمَعۡشَرَ ٱلۡجِنِّ قَدِ ٱسۡتَكۡثَرۡتُم مِّنَ ٱلۡإِنسِۖ وَقَالَ أَوۡلِيَآؤُهُم مِّنَ ٱلۡإِنسِ رَبَّنَا ٱسۡتَمۡتَعَ بَعۡضُنَا بِبَعۡضٖ وَبَلَغۡنَآ أَجَلَنَا ٱلَّذِيٓ أَجَّلۡتَ لَنَاۚ قَالَ ٱلنَّارُ مَثۡوَىٰكُمۡ خَٰلِدِينَ فِيهَآ إِلَّا مَا شَآءَ ٱللَّهُۚ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٞ
128. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሁሉንም በአንድ ቦታ በሚሰበስባቸው ቀን የሚሆነውን አስታውስ:: «የአጋንንት ቡድኖች ሆይ! ከሰዎች ቡድንን በማጥመም በእርግጥ አበዛችሁ።» ይባላሉ:: ከሰዎችም መካከል የሆኑት ወዳጆቻቸው «ጌታችን ሆይ! ከፊላችን በከፊሉ ተጠቀመ:: ያንን ለእኛ የወሰንክልንን ጊዜያችንን ደረስን።» ይላሉ:: «እሳቲቱ አላህ የሻው ጊዜ ሲቀር በውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ መኖሪያችሁ ናት።» ይላቸዋል:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ጌታህ ጥበበኛና አዋቂ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَكَذَٰلِكَ نُوَلِّي بَعۡضَ ٱلظَّٰلِمِينَ بَعۡضَۢا بِمَا كَانُواْ يَكۡسِبُونَ
129. ልክ እንደዚሁ አንዳንድ በደለኞችን ይሰሩት በነበሩት ጥፋት ምክንያት በከፊሎች ላይ እንሾማለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰمَعۡشَرَ ٱلۡجِنِّ وَٱلۡإِنسِ أَلَمۡ يَأۡتِكُمۡ رُسُلٞ مِّنكُمۡ يَقُصُّونَ عَلَيۡكُمۡ ءَايَٰتِي وَيُنذِرُونَكُمۡ لِقَآءَ يَوۡمِكُمۡ هَٰذَاۚ قَالُواْ شَهِدۡنَا عَلَىٰٓ أَنفُسِنَاۖ وَغَرَّتۡهُمُ ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا وَشَهِدُواْ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمۡ أَنَّهُمۡ كَانُواْ كَٰفِرِينَ
130. «የአጋንትና የሰዎች ቡድኖች ሆይ! አንቀፆቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን ቅጣት ማግኘትን የሚያስፈራሯችሁ ከናንተው የሆኑ መልዕክተኞች አልመጡላችሁም ነበርን?» ይባላሉ:: «በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን።» ይላሉ። የዱንያ ህይወት አታለለቻቸው። በነፍሶቻቸው ላይ እነርሱ ከሓዲያን የነበሩ መሆናቸውንም በራሳቸው መሰከሩ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ