Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម   អាយ៉ាត់:
ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖ فَٱعۡبُدُوهُۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ وَكِيلٞ
102. ይህ ጌታችሁ አላህ ነው:: ከእርሱ በስተቀር አምላክ የለም:: ሁሉን ነገር ፈጣሪ ነው:: ስለዚህ እርሱን ብቻ ተገዙት:: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ተጠባባቂ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّا تُدۡرِكُهُ ٱلۡأَبۡصَٰرُ وَهُوَ يُدۡرِكُ ٱلۡأَبۡصَٰرَۖ وَهُوَ ٱللَّطِيفُ ٱلۡخَبِيرُ
103. አይኖች አያገኙትም:: እርሱ ግን አይኖችን ያያል:: እርሱም ሩህሩህና ውስጠ አዋቂ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَدۡ جَآءَكُم بَصَآئِرُ مِن رَّبِّكُمۡۖ فَمَنۡ أَبۡصَرَ فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ عَمِيَ فَعَلَيۡهَاۚ وَمَآ أَنَا۠ عَلَيۡكُم بِحَفِيظٖ
104. (ሰዎች ሆይ!) «ከጌታችሁ ዘንድ ብርሃኖች በእርግጥ መጡላችሁ:: እውነቱን የተመለከተ ሰው ጥቅሙ ለነፍሱ ብቻ ነው:: የታወረም ሰው ጉዳቱ በራሱ ላይ ብቻ ነው:: እኔ በእናንተ ላይ ጠባቂ አይደለሁም።» በላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَكَذَٰلِكَ نُصَرِّفُ ٱلۡأٓيَٰتِ وَلِيَقُولُواْ دَرَسۡتَ وَلِنُبَيِّنَهُۥ لِقَوۡمٖ يَعۡلَمُونَ
105. ልክ እንደዚሁ ገምግመው «መጽሐፍ አጥንተሃል» እንዲሉና ለሚያውቁ ህዝቦች ቁርኣንን እንድናብራራ አናቅጽን እንገልፃለን።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱتَّبِعۡ مَآ أُوحِيَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡمُشۡرِكِينَ
106. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደውን ብቻ ተከተል:: ከእርሱ በስተቀር ትክክለኛ አምላክ የለም:: አጋሪዎችንም ተዋቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَوۡ شَآءَ ٱللَّهُ مَآ أَشۡرَكُواْۗ وَمَا جَعَلۡنَٰكَ عَلَيۡهِمۡ حَفِيظٗاۖ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡهِم بِوَكِيلٖ
107. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በፈለገ ኖሮ እነርሱ ጣኦትን ባላጋሩ ነበር:: በእነርሱም ላይ ጠባቂ አላደረግንህም:: አንተም በእነርሱ ላይ ኃላፊ አይደለህም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَا تَسُبُّواْ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ فَيَسُبُّواْ ٱللَّهَ عَدۡوَۢا بِغَيۡرِ عِلۡمٖۗ كَذَٰلِكَ زَيَّنَّا لِكُلِّ أُمَّةٍ عَمَلَهُمۡ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِم مَّرۡجِعُهُمۡ فَيُنَبِّئُهُم بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
108. (ሙስሊሞች ሆይ!) እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸውን ጣዖታትን አትስደቡ:: እነርሱም ድንበርን በማለፍ ያለ እውቀት አላህን ይሰድባሉና:: ልክ እንደዚሁ ለህዝቦች ሁሉ ስራቸውን ደግ አስመሰልንላቸው:: ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጌታቸው ብቻ ነው:: ይሰሩት የነበሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ لَئِن جَآءَتۡهُمۡ ءَايَةٞ لَّيُؤۡمِنُنَّ بِهَاۚ قُلۡ إِنَّمَا ٱلۡأٓيَٰتُ عِندَ ٱللَّهِۖ وَمَا يُشۡعِرُكُمۡ أَنَّهَآ إِذَا جَآءَتۡ لَا يُؤۡمِنُونَ
109. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተዐምር ብትመጣላቸው በእርሷ በቁርጥ እንደሚያምኑ ጥብቅ መሀላዎቻቸውን በአላህ ማሉ:: «ተዓምራትም ሁሉ የሚከሰቱት ከአላህ ብቻ ነው። እርሷ በመጣች ጊዜም አለማመናቸውን ወይም ማመናቸውን ምን አሳወቃችሁ?» በላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَنُقَلِّبُ أَفۡـِٔدَتَهُمۡ وَأَبۡصَٰرَهُمۡ كَمَا لَمۡ يُؤۡمِنُواْ بِهِۦٓ أَوَّلَ مَرَّةٖ وَنَذَرُهُمۡ فِي طُغۡيَٰنِهِمۡ يَعۡمَهُونَ
110. በመጀመሪያም ጊዜ በእርሱ እንዳላመኑ ሁሉ ልቦቻቸውንና አይኖቻቸውን እናገላብጣለን:: በጥመታቸዉም ውስጥ የሚዋልሉ ሲሆኑ እንተዋቸዋለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ