Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម   អាយ៉ាត់:
وَقَالُواْ هَٰذِهِۦٓ أَنۡعَٰمٞ وَحَرۡثٌ حِجۡرٞ لَّا يَطۡعَمُهَآ إِلَّا مَن نَّشَآءُ بِزَعۡمِهِمۡ وَأَنۡعَٰمٌ حُرِّمَتۡ ظُهُورُهَا وَأَنۡعَٰمٞ لَّا يَذۡكُرُونَ ٱسۡمَ ٱللَّهِ عَلَيۡهَا ٱفۡتِرَآءً عَلَيۡهِۚ سَيَجۡزِيهِم بِمَا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
138. በሀሳባቸውም «እነዚህ እርም የሆኑ ለማዳ እንሰሳና አዝመራ ናቸው:: የምንሻለት ሰው እንጂ ሌላ ማንም አይበላቸዉም:: እነዚህ ደግሞ ጀርባዎቻቸው እርም የተደረገ ለማዳ እንሰሳ ናቸው:: አይጫኑም:: እነዚህ ሲታረዱ በእነርሱ ላይ የአላህን ስም የማይጠሩባቸዉም እንሳሳት ናቸው።» አሉ:: በእርሱ ላይ ለመቅጠፍ ነገሩን ወደ አላህ አስጠጉ:: ይቀጥፉት በነበሩት ነገር በእርግጥ ይቀጣቸዋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالُواْ مَا فِي بُطُونِ هَٰذِهِ ٱلۡأَنۡعَٰمِ خَالِصَةٞ لِّذُكُورِنَا وَمُحَرَّمٌ عَلَىٰٓ أَزۡوَٰجِنَاۖ وَإِن يَكُن مَّيۡتَةٗ فَهُمۡ فِيهِ شُرَكَآءُۚ سَيَجۡزِيهِمۡ وَصۡفَهُمۡۚ إِنَّهُۥ حَكِيمٌ عَلِيمٞ
139. «በእነዚህ እንስሳት ሆዶች ውስጥ ያለው ጽንሱ ሁሉ ለወንዶቻችን ብቻ በተለይ የተፈቀደ ነው:: በሚስቶቻችን ላይ ግን እርም የተደረገ ነው:: ሙት ሆኖ ቢወለድ ግን ወንዶቹም ሆነ ሴቶች በእርሱ ላይ ተጋሪዎች ናቸው።» አሉ:: ይህን በመቅጠፋቸው አላህ በእርግጥ ይቀጣቸዋል:: እርሱ ጥበበኛና አዋቂ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَدۡ خَسِرَ ٱلَّذِينَ قَتَلُوٓاْ أَوۡلَٰدَهُمۡ سَفَهَۢا بِغَيۡرِ عِلۡمٖ وَحَرَّمُواْ مَا رَزَقَهُمُ ٱللَّهُ ٱفۡتِرَآءً عَلَى ٱللَّهِۚ قَدۡ ضَلُّواْ وَمَا كَانُواْ مُهۡتَدِينَ
140. እነዚያ ያለ እውቀት በሞኝነት ልጆቻቸውን የገደሉና አላህም የሰጣቸውን ሲሳይ በአላህ ላይ በመቅጠፍ በራሳቸው ላይ እርም ያደረጉ ሰዎች ሁሉ በእርግጥ ከሰሩ:: ተሳሳቱም:: ወደ ትክክለኛው መንገድም የተመሩ አልነበሩም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ وَهُوَ ٱلَّذِيٓ أَنشَأَ جَنَّٰتٖ مَّعۡرُوشَٰتٖ وَغَيۡرَ مَعۡرُوشَٰتٖ وَٱلنَّخۡلَ وَٱلزَّرۡعَ مُخۡتَلِفًا أُكُلُهُۥ وَٱلزَّيۡتُونَ وَٱلرُّمَّانَ مُتَشَٰبِهٗا وَغَيۡرَ مُتَشَٰبِهٖۚ كُلُواْ مِن ثَمَرِهِۦٓ إِذَآ أَثۡمَرَ وَءَاتُواْ حَقَّهُۥ يَوۡمَ حَصَادِهِۦۖ وَلَا تُسۡرِفُوٓاْۚ إِنَّهُۥ لَا يُحِبُّ ٱلۡمُسۡرِفِينَ
141. አላህ ያ (በሀረጉ) ዳስ የሚያደርግላቸውንና ዳስ የማያደርግላቸውን አትክልቶች የፈጠረ ነው:: የተምርን ዛፍ፣ አዝመራን፣ ፍሬዎቹ የተለያዩ ሲሆኑ ወይራንና ሩማንንም ቅጠላቸው ተመሳሳይና ጣዕማቸው የማይመሳሰል ሲሆኑ ፈጠረ:: (ሰዎች ሆይ!) ባፈራ ጊዜም ከፍሬው ብሉ:: ባጨዳዉም ቀን ተገቢውን (ዘካ) ለተገቢው ስጡለት:: አታባክኑም:: አላህ አባካኞችን አይወድምና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمِنَ ٱلۡأَنۡعَٰمِ حَمُولَةٗ وَفَرۡشٗاۚ كُلُواْ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ وَلَا تَتَّبِعُواْ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيۡطَٰنِۚ إِنَّهُۥ لَكُمۡ عَدُوّٞ مُّبِينٞ
142. ከለማዳ እንሰሳዎችም የሚጫኑትንም የማይጫኑትንም ፈጠረ:: (ሰዎች ሆይ!) አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ብሉ:: የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ:: እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អាន់អាម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ