Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាស់ហ្សូមើរ   អាយ៉ាត់:
إِنَّآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡكَ ٱلۡكِتَٰبَ لِلنَّاسِ بِٱلۡحَقِّۖ فَمَنِ ٱهۡتَدَىٰ فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيۡهَاۖ وَمَآ أَنتَ عَلَيۡهِم بِوَكِيلٍ
41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ መጽሐፉን ባንተ ላይ ለሰዎች ጥቅም በእውነት አወረድነው:: እናም በሱ የተመራ ሰው ሁሉ ፋይዳው ለነፍሱ ነው:: የጠመመም ሰው ጉዳቱ ለራሱ ነው የሚጠመው:: አንተም ታስገድዳቸው ዘንድ በእነርሱ ላይ ጠባቂ አይደለህም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱللَّهُ يَتَوَفَّى ٱلۡأَنفُسَ حِينَ مَوۡتِهَا وَٱلَّتِي لَمۡ تَمُتۡ فِي مَنَامِهَاۖ فَيُمۡسِكُ ٱلَّتِي قَضَىٰ عَلَيۡهَا ٱلۡمَوۡتَ وَيُرۡسِلُ ٱلۡأُخۡرَىٰٓ إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمًّىۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ
42. አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ ይወስዳል:: ያችንም ያልሞተችውን ነፍስ በእንቅልፈ ጊዜ ይወስዳታል:: ከዚያም ያችን ሞትን የፈረደባትን ነፍስ ይይዛታል:: ሌላይቱን ደግሞ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ይለቃታል:: በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተአምራት አሉበት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَمِ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ شُفَعَآءَۚ قُلۡ أَوَلَوۡ كَانُواْ لَا يَمۡلِكُونَ شَيۡـٔٗا وَلَا يَعۡقِلُونَ
43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ይልቁንም ቁረይሾች ከአላህ ሌላ አማላጆችን ያዙ። «እነርሱ ምንም የማይችሉና ምንም የማያውቁ ቢሆኑም ታመልኳቸዋላችሁን?» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُل لِّلَّهِ ٱلشَّفَٰعَةُ جَمِيعٗاۖ لَّهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ ثُمَّ إِلَيۡهِ تُرۡجَعُونَ
44. «ምልጃ ሁሉም የአላህ ብቻ ነው:: የሰማያትና የምድር ስልጣንም የእርሱ ብቻ ነው:: ከዚያም ወደ እርሱ ትመለሳላችሁ» በላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَحۡدَهُ ٱشۡمَأَزَّتۡ قُلُوبُ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِۖ وَإِذَا ذُكِرَ ٱلَّذِينَ مِن دُونِهِۦٓ إِذَا هُمۡ يَسۡتَبۡشِرُونَ
45. አላህ ብቻዉን በተወሳ ጊዜ የእነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ሰዎች ልቦች ይሸማቀቃሉ (ይደነብራሉ) እነዚያ ከእርሱ ሌላ የሆኑት ጣዖታት በተወሱ ጊዜ ደግሞ እነርሱ ወዲያውኑ ይደሰታሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلِ ٱللَّهُمَّ فَاطِرَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ عَٰلِمَ ٱلۡغَيۡبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ أَنتَ تَحۡكُمُ بَيۡنَ عِبَادِكَ فِي مَا كَانُواْ فِيهِ يَخۡتَلِفُونَ
46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን የፈጠርክ ሩቁንም ቅርቡንም አዋቂ የሆንከው አላህ ሆይ! አንተ በባሮችህ መካከል በዚያም ይለያዩበት በነበሩት ነገር ትፈርዳለህ» በል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَوۡ أَنَّ لِلَّذِينَ ظَلَمُواْ مَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا وَمِثۡلَهُۥ مَعَهُۥ لَٱفۡتَدَوۡاْ بِهِۦ مِن سُوٓءِ ٱلۡعَذَابِ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ وَبَدَا لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مَا لَمۡ يَكُونُواْ يَحۡتَسِبُونَ
47. ለነዚያም ለበደሉት በምድር ያለው ሁሉ መላዉም ከእርሱ ጋር መሰሉም ቢኖራቸው ኖሮ በትንሳኤ ቀን ከቅጣቱ ክፋት የተነሳ በእርሱ ነፍሶቻቸውን በተበዡበት ነበር:: ለእነርሱም ከአላህ ዘንድ ያስቡት ያልነበሩት ሁሉ ይገለጽላቸዋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាស់ហ្សូមើរ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ