Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាស់ហ្សូមើរ   អាយ៉ាត់:
خَلَقَكُم مِّن نَّفۡسٖ وَٰحِدَةٖ ثُمَّ جَعَلَ مِنۡهَا زَوۡجَهَا وَأَنزَلَ لَكُم مِّنَ ٱلۡأَنۡعَٰمِ ثَمَٰنِيَةَ أَزۡوَٰجٖۚ يَخۡلُقُكُمۡ فِي بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡ خَلۡقٗا مِّنۢ بَعۡدِ خَلۡقٖ فِي ظُلُمَٰتٖ ثَلَٰثٖۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ لَهُ ٱلۡمُلۡكُۖ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ فَأَنَّىٰ تُصۡرَفُونَ
6. (ሰዎች ሆይ!) ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ:: ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን ፈጠረ:: ለእናንተም ከግመልና ከዳልጋ ከብት፤ ከፍየልና ከበግ ስምንት አይነቶችን (ጥንዶችን) አወረደ:: በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ በሶስት ጨለማዎች ውስጥ ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል፤ ይህን ያደረገው ጌታችሁ አላህ ነው:: ስልጣኑም የእርሱ ብቻ ነው:: ከእርሱ ሌላ ትክክለኛ አምላክ የለም:: ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِن تَكۡفُرُواْ فَإِنَّ ٱللَّهَ غَنِيٌّ عَنكُمۡۖ وَلَا يَرۡضَىٰ لِعِبَادِهِ ٱلۡكُفۡرَۖ وَإِن تَشۡكُرُواْ يَرۡضَهُ لَكُمۡۗ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۚ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُم مَّرۡجِعُكُمۡ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
7. በአላህ ብትክዱ አላህ ከናንተ የተብቃቃ ነው:: ለባሪያዎቹም ክህደትን አይወድም፤ ብታመሰግኑም እርሱን ይወድላችኋል:: ማንኛይቱም ኃጢአትን ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም:: ከዚያም የሁላችሁም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ብቻ ነው:: ትሰሩት የነበራችሁትንም ሁሉ ይነግራችኋል:: እርሱ በልቦች ውስጥ ያሉትን ሁሉ አዋቂ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ وَإِذَا مَسَّ ٱلۡإِنسَٰنَ ضُرّٞ دَعَا رَبَّهُۥ مُنِيبًا إِلَيۡهِ ثُمَّ إِذَا خَوَّلَهُۥ نِعۡمَةٗ مِّنۡهُ نَسِيَ مَا كَانَ يَدۡعُوٓاْ إِلَيۡهِ مِن قَبۡلُ وَجَعَلَ لِلَّهِ أَندَادٗا لِّيُضِلَّ عَن سَبِيلِهِۦۚ قُلۡ تَمَتَّعۡ بِكُفۡرِكَ قَلِيلًا إِنَّكَ مِنۡ أَصۡحَٰبِ ٱلنَّارِ
8. የሰውን ልጅ ጉዳት ባገኘው ጊዜ ወደ እርሱ ተመላሽ ሆኖ ጌታወን ይጠራል:: ከዚያም ከእርሱ ዘንድ ጸጋን በሰጠው ጊዜ ያንን ከዚያ በፊት ወደ እርሱ ይጸልይበት የነበረውን መከራ ይረሳል:: ከመንገዱ ለማሳሳትም ለአላህ ባላንጣዎችን ያደርጋል:: ለእንዲህ አይነቱ ሰው «በክህደት ጥቂትን ተጣቀም፤ አንተ በእርግጥ ከእሳት ጓዶች ነህ።» በለው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَمَّنۡ هُوَ قَٰنِتٌ ءَانَآءَ ٱلَّيۡلِ سَاجِدٗا وَقَآئِمٗا يَحۡذَرُ ٱلۡأٓخِرَةَ وَيَرۡجُواْ رَحۡمَةَ رَبِّهِۦۗ قُلۡ هَلۡ يَسۡتَوِي ٱلَّذِينَ يَعۡلَمُونَ وَٱلَّذِينَ لَا يَعۡلَمُونَۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ
9. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያ የመጨረሻይቱን ዓለም ቅጣት የሚፈራ የጌታውንም ችሮታ የሚከጅል ሲሆን በሌሊት ሰዓቶችም ሰጋጅና ቋሚ ሆኖ ለጌታው የሚገዛ ሰው (እንደ ተስፋ ቢሱ ከሓዲ ነውን? በለው።) «እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው:: የሚገሰፁት ባለ አእምሮዎች ብቻ ናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ يَٰعِبَادِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱتَّقُواْ رَبَّكُمۡۚ لِلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ فِي هَٰذِهِ ٱلدُّنۡيَا حَسَنَةٞۗ وَأَرۡضُ ٱللَّهِ وَٰسِعَةٌۗ إِنَّمَا يُوَفَّى ٱلصَّٰبِرُونَ أَجۡرَهُم بِغَيۡرِ حِسَابٖ
10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ጌታችሁ) «እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ለነዚያ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው፡፡ የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው» (ይላል) በላቸው፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាស់ហ្សូមើរ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ