Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាស់ហ្សូមើរ   អាយ៉ាត់:
قُلۡ إِنِّيٓ أُمِرۡتُ أَنۡ أَعۡبُدَ ٱللَّهَ مُخۡلِصٗا لَّهُ ٱلدِّينَ
11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ! እንዲህ) በል: «እኔ አላህን ሃይማኖትን ለእርሱ ያጠራሁ ሆኜ እንድገዛው ታዘዝኩ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأُمِرۡتُ لِأَنۡ أَكُونَ أَوَّلَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
12. «የሙስሊሞች መጀመሪያ እንድሆን ታዘዝኩ» በል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ إِنِّيٓ أَخَافُ إِنۡ عَصَيۡتُ رَبِّي عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ» በል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلِ ٱللَّهَ أَعۡبُدُ مُخۡلِصٗا لَّهُۥ دِينِي
14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (እንዲህ) በል: «አላህን ሃይማኖቴን ለእርሱ ያጠራሁ ሆኜ እገዛዋለሁ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَٱعۡبُدُواْ مَا شِئۡتُم مِّن دُونِهِۦۗ قُلۡ إِنَّ ٱلۡخَٰسِرِينَ ٱلَّذِينَ خَسِرُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ وَأَهۡلِيهِمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۗ أَلَا ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡخُسۡرَانُ ٱلۡمُبِينُ
15. «ከእርሱ ሌላ የሻችሁትን ተገዙ:: ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በትንሳኤ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው። ሰዎች ሆይ! አስተዉሉ:: ግልጽ ከሳራ ማለት ይህ ነው።» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَهُم مِّن فَوۡقِهِمۡ ظُلَلٞ مِّنَ ٱلنَّارِ وَمِن تَحۡتِهِمۡ ظُلَلٞۚ ذَٰلِكَ يُخَوِّفُ ٱللَّهُ بِهِۦ عِبَادَهُۥۚ يَٰعِبَادِ فَٱتَّقُونِ
16. ለእነርሱ ከበላያቸው ከእሳት የሆኑ ድርብርብ ጥላዎች አሏቸው:: ከስራቸዉም እንዲሁ:: ይህ አላህ ባሮቹን እንዲጠነቀቁ በእርሱ ያስፈራራበታል:: ባሮቼ ሆይ! ስለዚህ ፍሩኝ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱلَّذِينَ ٱجۡتَنَبُواْ ٱلطَّٰغُوتَ أَن يَعۡبُدُوهَا وَأَنَابُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ لَهُمُ ٱلۡبُشۡرَىٰۚ فَبَشِّرۡ عِبَادِ
17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም ጣዖታትን ከመገዛት የራቁ እና ወደ አላህ የዞሩ ሁሉ ለእነርሱ ታላቅ ብስራት አላቸው። ስለዚህ ባሮቼን አብስር፡፡
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلَّذِينَ يَسۡتَمِعُونَ ٱلۡقَوۡلَ فَيَتَّبِعُونَ أَحۡسَنَهُۥٓۚ أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ هَدَىٰهُمُ ٱللَّهُۖ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمۡ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ
18. እነዚያን ንግግርን የሚያዳምጡትንና መልካምን የሚከተሉትን (ባሮቼን አብስር)፤ እነዚያ አላህ ወደ ቀናው መንገድ የመራቸው ናቸው። እነዚያም እነርሱ ባለ አእምሮዎቹ ናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَفَمَنۡ حَقَّ عَلَيۡهِ كَلِمَةُ ٱلۡعَذَابِ أَفَأَنتَ تُنقِذُ مَن فِي ٱلنَّارِ
19. በእርሱ ላይ የቅጣት ቃል የተረጋገጠችበትን (ትመራዋለህን?) አንተ በእሳት ውስጥ ያለን ታድናለህን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَٰكِنِ ٱلَّذِينَ ٱتَّقَوۡاْ رَبَّهُمۡ لَهُمۡ غُرَفٞ مِّن فَوۡقِهَا غُرَفٞ مَّبۡنِيَّةٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُۖ وَعۡدَ ٱللَّهِ لَا يُخۡلِفُ ٱللَّهُ ٱلۡمِيعَادَ
20. ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ፤ ለእነርሱም ከበላያቸው የታነጹ ሰገነቶች ያሏቸው ሰገነቶች ከስሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸው የሆኑ አሏቸው:: (ይህንን) አላህ ቃል ገባላቸው፤ አላህም ቃሉን አያፈርስም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ أَنزَلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءٗ فَسَلَكَهُۥ يَنَٰبِيعَ فِي ٱلۡأَرۡضِ ثُمَّ يُخۡرِجُ بِهِۦ زَرۡعٗا مُّخۡتَلِفًا أَلۡوَٰنُهُۥ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَىٰهُ مُصۡفَرّٗا ثُمَّ يَجۡعَلُهُۥ حُطَٰمًاۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَذِكۡرَىٰ لِأُوْلِي ٱلۡأَلۡبَٰبِ
21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ከሰማይ ውሃን እንዳወረደና በምድር ውስጥ ምንጮች አድርጎ እንዳስገባው አላየህምን? ከዚያም በእርሱ ብዙ አይነቶች የሆኑ የተለያዩ አዝመራዎችን ያወጣበታል:: ከዚያም ይደርቃል:: ገርጥቶም ታየዋለህ:: ከዚያ ስብርብር ያደርገዋል፤ በዚህ ውስጥ ለባለ አእምሮዎች ግሳፄ አለበት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាស់ហ្សូមើរ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ