Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាស់ហ្សូមើរ   អាយ៉ាត់:
أَفَمَن شَرَحَ ٱللَّهُ صَدۡرَهُۥ لِلۡإِسۡلَٰمِ فَهُوَ عَلَىٰ نُورٖ مِّن رَّبِّهِۦۚ فَوَيۡلٞ لِّلۡقَٰسِيَةِ قُلُوبُهُم مِّن ذِكۡرِ ٱللَّهِۚ أُوْلَٰٓئِكَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٍ
22. አላህ ደረቱን ለእስልምና ያሰፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የሆነ ሰው (ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን?) ልቦቻቸዉም ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወየውላቸው፤ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱللَّهُ نَزَّلَ أَحۡسَنَ ٱلۡحَدِيثِ كِتَٰبٗا مُّتَشَٰبِهٗا مَّثَانِيَ تَقۡشَعِرُّ مِنۡهُ جُلُودُ ٱلَّذِينَ يَخۡشَوۡنَ رَبَّهُمۡ ثُمَّ تَلِينُ جُلُودُهُمۡ وَقُلُوبُهُمۡ إِلَىٰ ذِكۡرِ ٱللَّهِۚ ذَٰلِكَ هُدَى ٱللَّهِ يَهۡدِي بِهِۦ مَن يَشَآءُۚ وَمَن يُضۡلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنۡ هَادٍ
23. አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን ተመሳሳይ ተደጋጋሚ የሆነን መጽሐፍ (ቁርኣንን) አወረደ:: ከእርሱ ግሳፄ የእነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎች ይኮማተራሉ:: ከዚያም ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ ተስፋ ማስታወስ ይለዝባሉ:: ይህ የአላህ መምሪያ ነው፤ በእርሱ የሚሻዉን ሰው ይመራበታል። አላህም የሚያጠመውን ሰው ለእርሱ ምንም አቅኝ የለዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَفَمَن يَتَّقِي بِوَجۡهِهِۦ سُوٓءَ ٱلۡعَذَابِ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ وَقِيلَ لِلظَّٰلِمِينَ ذُوقُواْ مَا كُنتُمۡ تَكۡسِبُونَ
24. በትንሳኤ ቀን ክፉን ቅጣት በፊቱ የሚመክት ሰው (ከቅጣቱ እንደዳነው ነውን?) ለበዳዮችም «ትሰሩት የነበራችሁን ቅጣትን ቅመሱ» ይባላሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
كَذَّبَ ٱلَّذِينَ مِن قَبۡلِهِمۡ فَأَتَىٰهُمُ ٱلۡعَذَابُ مِنۡ حَيۡثُ لَا يَشۡعُرُونَ
25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት የነበሩት አስተባበሉ:: ቅጣቱም ከማያውቁት በኩል መጣባቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَأَذَاقَهُمُ ٱللَّهُ ٱلۡخِزۡيَ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَعَذَابُ ٱلۡأٓخِرَةِ أَكۡبَرُۚ لَوۡ كَانُواْ يَعۡلَمُونَ
26. አላህም በቅርቢቱ ሕይወት ውርደትን አቀመሳቸው:: የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም ትልቅ ነው:: የሚያውቁ ቢሆኑ ኖሮ አያስተባብሉም ነበር::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ ضَرَبۡنَا لِلنَّاسِ فِي هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانِ مِن كُلِّ مَثَلٖ لَّعَلَّهُمۡ يَتَذَكَّرُونَ
27. በዚህም ቁርኣን ውስጥ ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ከየምሳሌው ሁሉ በእርግጥ አብራራን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُرۡءَانًا عَرَبِيًّا غَيۡرَ ذِي عِوَجٖ لَّعَلَّهُمۡ يَتَّقُونَ
28. መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ሲሆን (አብራራነው):: ሊጠነቀቁ ይከጀላልና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا رَّجُلٗا فِيهِ شُرَكَآءُ مُتَشَٰكِسُونَ وَرَجُلٗا سَلَمٗا لِّرَجُلٍ هَلۡ يَسۡتَوِيَانِ مَثَلًاۚ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِۚ بَلۡ أَكۡثَرُهُمۡ لَا يَعۡلَمُونَ
29. አላህ በእርሱ ተጨቃጫቂዎች የሆኑ ተጋሪዎች ያሉትን ባሪያና ለአንድ ሰው ብቻ ንጹህ የሆነን ባሪያ ለሚያጋራና በአንድነት ለሚያምን ሰው ምሳሌ አደረገ። በምሳሌ ይስተካካላሉን? ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይገባው:: በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّكَ مَيِّتٞ وَإِنَّهُم مَّيِّتُونَ
30. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ثُمَّ إِنَّكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ عِندَ رَبِّكُمۡ تَخۡتَصِمُونَ
31 ከዚያም እናንተ በትንሳኤ ቀን እጌታችሁ ዘንድ ትከራከራላችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាស់ហ្សូមើរ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ