Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់កះហ្វុី   អាយ៉ាត់:
ٱلۡمَالُ وَٱلۡبَنُونَ زِينَةُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَٱلۡبَٰقِيَٰتُ ٱلصَّٰلِحَٰتُ خَيۡرٌ عِندَ رَبِّكَ ثَوَابٗا وَخَيۡرٌ أَمَلٗا
46. ገንዘብና ልጆች የቅርቢቱ ህይወት ጌጦች ብቻ ናቸው:: መልካም ቀሪ ሥራዎች ግን በጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው:: በተስፋም በላጭ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَوۡمَ نُسَيِّرُ ٱلۡجِبَالَ وَتَرَى ٱلۡأَرۡضَ بَارِزَةٗ وَحَشَرۡنَٰهُمۡ فَلَمۡ نُغَادِرۡ مِنۡهُمۡ أَحَدٗا
47. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ተራራዎችን የምናስኬድበትን ቀን አስታውስ:: ምድርንም ግልጽ ሆና ታያታለህ:: እንሰበስባቸዋለንም:: ከእነርሱ አንድንም አንተዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَعُرِضُواْ عَلَىٰ رَبِّكَ صَفّٗا لَّقَدۡ جِئۡتُمُونَا كَمَا خَلَقۡنَٰكُمۡ أَوَّلَ مَرَّةِۭۚ بَلۡ زَعَمۡتُمۡ أَلَّن نَّجۡعَلَ لَكُم مَّوۡعِدٗا
48. የተሰለፉ ሆነው በጌታህ ላይ ይቀርባሉ:: ይባላሉም «በመጀመሪያ ጊዜ እንደፈጠርናችሁ በእርግጥ ወደ እኛ መጣችሁ:: በእውነቱ ለእናንተ የመቀስቀሻ ጊዜን አናደርግም መስሏችሁ ነበር።»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَوُضِعَ ٱلۡكِتَٰبُ فَتَرَى ٱلۡمُجۡرِمِينَ مُشۡفِقِينَ مِمَّا فِيهِ وَيَقُولُونَ يَٰوَيۡلَتَنَا مَالِ هَٰذَا ٱلۡكِتَٰبِ لَا يُغَادِرُ صَغِيرَةٗ وَلَا كَبِيرَةً إِلَّآ أَحۡصَىٰهَاۚ وَوَجَدُواْ مَا عَمِلُواْ حَاضِرٗاۗ وَلَا يَظۡلِمُ رَبُّكَ أَحَدٗا
49 ለሰው ሁሉ መጽሐፉ ይቀርባል:: ወዲያዉም ከሓዲያንን በውስጡ ካለው ነገር ፈሪዎች ሆነው ታያቸዋለህ። «ዋ ጥፋታችን! ይህ መጽሐፍ ከሥራ ትንሽንም ትልቅንም የቆጠራት ቢሆን እንጂ የማይተወው ምን አለው?» ይላሉ:: የሠሩትንም ነገር ሁሉ ቅርብ ሆኖ ያገኙታል:: ጌታህም አንድንም አይበድልም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذۡ قُلۡنَا لِلۡمَلَٰٓئِكَةِ ٱسۡجُدُواْ لِأٓدَمَ فَسَجَدُوٓاْ إِلَّآ إِبۡلِيسَ كَانَ مِنَ ٱلۡجِنِّ فَفَسَقَ عَنۡ أَمۡرِ رَبِّهِۦٓۗ أَفَتَتَّخِذُونَهُۥ وَذُرِّيَّتَهُۥٓ أَوۡلِيَآءَ مِن دُونِي وَهُمۡ لَكُمۡ عَدُوُّۢۚ بِئۡسَ لِلظَّٰلِمِينَ بَدَلٗا
50. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለመላዕክት «ለአደም ስገዱ።» ባልናቸው ጊዜ (የሆነውን አስታውስ):: ወዲያዉም ዲያብሎስ ብቻ ሲቀር ሁሉም ሰገዱ:: ከአጋንንት ጎሳ ነበርና:: ከጌታዉም ትዕዛዝ ወጣ:: እርሱንና ዘሮቹን እነርሱም ለእናንተ ጠላቶች ሲሆኑ ከኔ ሌላ ረዳቶች ታደርጋላችሁን? ለበዳዮች ልዋጭነቱ ከፋ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ مَّآ أَشۡهَدتُّهُمۡ خَلۡقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَلَا خَلۡقَ أَنفُسِهِمۡ وَمَا كُنتُ مُتَّخِذَ ٱلۡمُضِلِّينَ عَضُدٗا
51.የሰማያትና የምድርም አፈጣጠር አላሰየኋቸዉም:: የነፍሶቻቸውንም አፈጣጠር እንደዚሁ አሳሳቾችንም ረዳቶች አድርጌ የምይዝ አይደለሁም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَوۡمَ يَقُولُ نَادُواْ شُرَكَآءِيَ ٱلَّذِينَ زَعَمۡتُمۡ فَدَعَوۡهُمۡ فَلَمۡ يَسۡتَجِيبُواْ لَهُمۡ وَجَعَلۡنَا بَيۡنَهُم مَّوۡبِقٗا
52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያንም አምላክ የምትሏቸውን ተጋሪዎቼን ጥሩ።» የሚልበትን ቀን አስታውስ:: ይጠሯቸዋልም። ግን አይመልሱላቸዉም:: በመካከላቸዉም መጥፊያን ስፍራ ገሀነምንም አደረግን።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَرَءَا ٱلۡمُجۡرِمُونَ ٱلنَّارَ فَظَنُّوٓاْ أَنَّهُم مُّوَاقِعُوهَا وَلَمۡ يَجِدُواْ عَنۡهَا مَصۡرِفٗا
53. ከሓዲያንም እሳትን ያያሉ፤ እነርሱም በውስጧ ወዳቂዎች መሆናቸውን ያረጋግጣሉ:: ከእርሷም መሸሻን አያገኙም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់កះហ្វុី
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ