Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់កះហ្វុី   អាយ៉ាត់:
وَدَخَلَ جَنَّتَهُۥ وَهُوَ ظَالِمٞ لِّنَفۡسِهِۦ قَالَ مَآ أَظُنُّ أَن تَبِيدَ هَٰذِهِۦٓ أَبَدٗا
35. እርሱም ነፍሱንም በዳይ ሆኖ ወደ አትክልቱ ገባ። (እንዲህም) አለ: «ይህች አትክልት መቸም ትጠፋለች ብዬ አልጠረጥርም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَآ أَظُنُّ ٱلسَّاعَةَ قَآئِمَةٗ وَلَئِن رُّدِدتُّ إِلَىٰ رَبِّي لَأَجِدَنَّ خَيۡرٗا مِّنۡهَا مُنقَلَبٗا
36. «ሰዓቲቱንም ትከሰታለች ብዬ አልጠረጥርም፤ እንደምትለው ወደ ጌታዬም ብመለስ ከእርሷ የበለጠን መመለሻ በእርግጥ አገኛለሁ።» አለው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ لَهُۥ صَاحِبُهُۥ وَهُوَ يُحَاوِرُهُۥٓ أَكَفَرۡتَ بِٱلَّذِي خَلَقَكَ مِن تُرَابٖ ثُمَّ مِن نُّطۡفَةٖ ثُمَّ سَوَّىٰكَ رَجُلٗا
37. አማኙ ጓደኛውም ለእርሱ የሚመላለሰው ሲሆን (እንዲህ) አለው: «በዚያ ከአፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ በፈጠረህ ከዚያም ሰው ባደረገህ ሃያል አምላክ ካድክን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّٰكِنَّا۠ هُوَ ٱللَّهُ رَبِّي وَلَآ أُشۡرِكُ بِرَبِّيٓ أَحَدٗا
38. «እኔ ግን አላህ ጌታዬ ነው እላለሁ። በጌታዬም አንድንም አላጋራም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَوۡلَآ إِذۡ دَخَلۡتَ جَنَّتَكَ قُلۡتَ مَا شَآءَ ٱللَّهُ لَا قُوَّةَ إِلَّا بِٱللَّهِۚ إِن تَرَنِ أَنَا۠ أَقَلَّ مِنكَ مَالٗا وَوَلَدٗا
39. «እኔን በገንዘብም ሆነ በልጅ ካንተ በጣም ያነስኩ ሆኜ ብታየኝም ወደ አትክልትህ በገባህ ጊዜ ‹አላህ የሻው ሆኗል። በአላህ ቢሆን እንጂ ብልሃትም የለም› አትልም ኖሯልን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَعَسَىٰ رَبِّيٓ أَن يُؤۡتِيَنِ خَيۡرٗا مِّن جَنَّتِكَ وَيُرۡسِلَ عَلَيۡهَا حُسۡبَانٗا مِّنَ ٱلسَّمَآءِ فَتُصۡبِحَ صَعِيدٗا زَلَقًا
40. «ጌታዬ ከአትክልትህ የበለጠን ሊሰጠኝ በአትክልትህ ላይ ደግሞ በሰማይ መብረቆችን ሊልክባትና የምታንዳልጥ ምልጥ ምድር ልትሆንም ይቻላል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَوۡ يُصۡبِحَ مَآؤُهَا غَوۡرٗا فَلَن تَسۡتَطِيعَ لَهُۥ طَلَبٗا
41. «ወይም ውሀው ሰራጊ ሊሆንብህ ይችላል። ያን ጊዜ እርሱን መፈለጉን ፈጽሞ አትችልም።» አለው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأُحِيطَ بِثَمَرِهِۦ فَأَصۡبَحَ يُقَلِّبُ كَفَّيۡهِ عَلَىٰ مَآ أَنفَقَ فِيهَا وَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَىٰ عُرُوشِهَا وَيَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي لَمۡ أُشۡرِكۡ بِرَبِّيٓ أَحَدٗا
42. ሀብቱም ተጠፋ:: እርሷ በዳሶችዋ ላይ የወደቀች ሆና በእርሷ ባወጣው ገንዘብ ላይ የተጸጸተ መዳፎቹን የሚያገላብጥና «ወይ ጸጸቴ! በጌታዬ አንድንም ባላጋራሁ።» የሚል ሆነ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَمۡ تَكُن لَّهُۥ فِئَةٞ يَنصُرُونَهُۥ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَمَا كَانَ مُنتَصِرًا
43.እርሱም ከአላህ ሌላ የሚረዱት ቡድኖች አልነበሩትም:: ተረጂም አልነበረም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هُنَالِكَ ٱلۡوَلَٰيَةُ لِلَّهِ ٱلۡحَقِّۚ هُوَ خَيۡرٞ ثَوَابٗا وَخَيۡرٌ عُقۡبٗا
44.እዚያ ዘንድ በትንሳኤ ቀን ስልጣኑ እውነተኛ ለሆነው ለአላህ ብቻ ነው:: እርሱ በመመንዳት የበለጠ ፍጻሜንም በማሳመር የበለጠ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱضۡرِبۡ لَهُم مَّثَلَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا كَمَآءٍ أَنزَلۡنَٰهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ فَٱخۡتَلَطَ بِهِۦ نَبَاتُ ٱلۡأَرۡضِ فَأَصۡبَحَ هَشِيمٗا تَذۡرُوهُ ٱلرِّيَٰحُۗ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ مُّقۡتَدِرًا
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለእነርሱም የቅርቢቱን ህይወት ምሳሌ አውሳላቸው:: እርሷ ከሰማይ እንዳወረድነው ውሃ በእርሱም የምድር ቡቃያ እንደተቀላቀለበት፤ ከተዋበ በኋላም ደርቆ ንፋሶች የሚያበኑት ደቃቅ እንደሆነ ብጤ ናት:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់កះហ្វុី
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ