Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់កះហ្វុី   អាយ៉ាត់:
وَٱصۡبِرۡ نَفۡسَكَ مَعَ ٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ رَبَّهُم بِٱلۡغَدَوٰةِ وَٱلۡعَشِيِّ يُرِيدُونَ وَجۡهَهُۥۖ وَلَا تَعۡدُ عَيۡنَاكَ عَنۡهُمۡ تُرِيدُ زِينَةَ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۖ وَلَا تُطِعۡ مَنۡ أَغۡفَلۡنَا قَلۡبَهُۥ عَن ذِكۡرِنَا وَٱتَّبَعَ هَوَىٰهُ وَكَانَ أَمۡرُهُۥ فُرُطٗا
28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ነፍስህንም ከእነዚያ ጌታቸውን ፊቱን የሚሹ ሆነው በጥዋትና በማታ ከሚገዙት ጋር አስታግስ:: የቅርቢቱንም ህይወት ሽልማት የምትሻ ሆነህ አይኖችህ ከእነርሱ ወደ ሌላ አይለፉ:: ያ ልቡን እኛን ከማስታወስ ያዘነጋነውንና የግል ፍላጎቱን የተከተለውን ነገሩ ሁሉ ወሰን ማለፍ የሆነውን ሰው አትታዘዝ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقُلِ ٱلۡحَقُّ مِن رَّبِّكُمۡۖ فَمَن شَآءَ فَلۡيُؤۡمِن وَمَن شَآءَ فَلۡيَكۡفُرۡۚ إِنَّآ أَعۡتَدۡنَا لِلظَّٰلِمِينَ نَارًا أَحَاطَ بِهِمۡ سُرَادِقُهَاۚ وَإِن يَسۡتَغِيثُواْ يُغَاثُواْ بِمَآءٖ كَٱلۡمُهۡلِ يَشۡوِي ٱلۡوُجُوهَۚ بِئۡسَ ٱلشَّرَابُ وَسَآءَتۡ مُرۡتَفَقًا
29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰዎች ሆይ! እውነቱ ሁሉ ከጌታችሁ ነው:: ስለዚህ የፈለገም ሰው በእውነቱ ይመን:: የፈለገም ሰው ይካድ።» በላቸው:: እኛ ለበደለኛ ከሓዲያን አጥሯ በእነርሱ ላይ የከበበ የሆነችውን እሳት አዘጋጅተናል:: ከጥም ለመዳን እርዳታን ቢፈልጉ እንደ ዘይት ዝቃጭ ባለ ፊቶችን በሚጠብስ ውሃ ይረዳሉ:: መጠጡም ከፋ፤ መደገፊያይቱም ምንኛ አስከፋች!
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجۡرَ مَنۡ أَحۡسَنَ عَمَلًا
30. እነዚያ በአላህ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ እኛ ሥራ ያሳመረን ምንዳ አናጠፋም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ جَنَّٰتُ عَدۡنٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهِمُ ٱلۡأَنۡهَٰرُ يُحَلَّوۡنَ فِيهَا مِنۡ أَسَاوِرَ مِن ذَهَبٖ وَيَلۡبَسُونَ ثِيَابًا خُضۡرٗا مِّن سُندُسٖ وَإِسۡتَبۡرَقٖ مُّتَّكِـِٔينَ فِيهَا عَلَى ٱلۡأَرَآئِكِۚ نِعۡمَ ٱلثَّوَابُ وَحَسُنَتۡ مُرۡتَفَقٗا
31.እነዚያ ለእነርሱ የመኖሪያ ገነቶች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው አሏቸው:: በእርሷ ውስጥ ከወርቅ የሆኑን አምባሮች ይሸለማሉ:: ከቀጭን ሀርና ከወፍራም ሀርም አረንጓዴ ልብሶችን ይለብሳሉ:: በውስጧ በባለ አጎበር አልጋዎች ላይ የተደገፉ ሆነው ይቀመጣሉ:: እነዚህ ሰዎች ምንዳቸው ምን ያምር! መኖሪያቸው ገነትም ምንኛ አማረች!
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ وَٱضۡرِبۡ لَهُم مَّثَلٗا رَّجُلَيۡنِ جَعَلۡنَا لِأَحَدِهِمَا جَنَّتَيۡنِ مِنۡ أَعۡنَٰبٖ وَحَفَفۡنَٰهُمَا بِنَخۡلٖ وَجَعَلۡنَا بَيۡنَهُمَا زَرۡعٗا
32. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ለከሓዲያን የሁለትን ሰዎችን ምሳሌ ግለጽላቸው:: ለአንደኛው ከሓዲ ሁለት የወይን አትክልቶች አደረግንለት። በዘንባባም ከበብናቸው። በመካከላቸውም አዝመራን አደረግን።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
كِلۡتَا ٱلۡجَنَّتَيۡنِ ءَاتَتۡ أُكُلَهَا وَلَمۡ تَظۡلِم مِّنۡهُ شَيۡـٔٗاۚ وَفَجَّرۡنَا خِلَٰلَهُمَا نَهَرٗا
33. ሁለቱም አትክልቶች ሰብላቸውን ሰጡ፤ ከርሱም ምንም አላጎደሉም። በመካከላቸዉም ወንዝን አፈሰስን።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَكَانَ لَهُۥ ثَمَرٞ فَقَالَ لِصَٰحِبِهِۦ وَهُوَ يُحَاوِرُهُۥٓ أَنَا۠ أَكۡثَرُ مِنكَ مَالٗا وَأَعَزُّ نَفَرٗا
34.ለእርሱ ከአትክልቶቹ ሌላ ፍሬያማ ሀብት ነበረው:: ለአማኙ ጓደኛዉም የሚወዳደረው ሲሆን «እኔ ካንተ በገንዘብ ይበልጥ የበዛሁ በወገንም ይበልጥ የበረታሁ ነኝ።» አለው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់កះហ្វុី
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ