Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់កះហ្វុី   អាយ៉ាត់:
وَكَذَٰلِكَ أَعۡثَرۡنَا عَلَيۡهِمۡ لِيَعۡلَمُوٓاْ أَنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞ وَأَنَّ ٱلسَّاعَةَ لَا رَيۡبَ فِيهَآ إِذۡ يَتَنَٰزَعُونَ بَيۡنَهُمۡ أَمۡرَهُمۡۖ فَقَالُواْ ٱبۡنُواْ عَلَيۡهِم بُنۡيَٰنٗاۖ رَّبُّهُمۡ أَعۡلَمُ بِهِمۡۚ قَالَ ٱلَّذِينَ غَلَبُواْ عَلَىٰٓ أَمۡرِهِمۡ لَنَتَّخِذَنَّ عَلَيۡهِم مَّسۡجِدٗا
21. ልክ እንደዚሁም የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ መሆኑን ሰዓቲቱም በእርሷ ጥርጣሬ የሌለ መሆኑን ያውቁ ዘንድ በእነርሱ ላይ ሰዎችን አሳወቅን:: አማኞቹና ከሓዲያን ነገራቸውን በመካከላቸው ሲከራከሩ የሆነውን አስታውስ:: ከሓዲያን «በእነርሱ ላይ ግንብን ገንቡ።» አሉ:: ጌታቸው ለእነርሱ ይበልጥ አዋቂ ነው:: እነዚያ በነገራቸው ላይ ያሸነፉት ግን «በእነርሱ ላይ በእርግጥ መስጊድን እንሰራለን።» አሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
سَيَقُولُونَ ثَلَٰثَةٞ رَّابِعُهُمۡ كَلۡبُهُمۡ وَيَقُولُونَ خَمۡسَةٞ سَادِسُهُمۡ كَلۡبُهُمۡ رَجۡمَۢا بِٱلۡغَيۡبِۖ وَيَقُولُونَ سَبۡعَةٞ وَثَامِنُهُمۡ كَلۡبُهُمۡۚ قُل رَّبِّيٓ أَعۡلَمُ بِعِدَّتِهِم مَّا يَعۡلَمُهُمۡ إِلَّا قَلِيلٞۗ فَلَا تُمَارِ فِيهِمۡ إِلَّا مِرَآءٗ ظَٰهِرٗا وَلَا تَسۡتَفۡتِ فِيهِم مِّنۡهُمۡ أَحَدٗا
22. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) (ስለ እነርሱ የተወሰኑ ቡድኖች በጥርጣሬ) «ሶስት ናቸው አራተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ:: (ሌሎች ቡድኖች) «አምስት ናቸው ስድስተኛው ውሻቸው ነው።» ይላሉ። በሩቅ ወርዋሪዎች ሆነው (ባላወቁት አለም) ሲገምቱ። (ሶስተኛው ቡድን ደግሞ) «ሰባት ናቸው ስምንተኛቸው ውሻቸው ነዉ።» ይላሉ:: «ጌታዬ ብቻ ቁጥራቸውን አዋቂ ነው:: ጥቂት ሰው እንጂ አያውቃቸዉም።» በላቸው:: እናም በእነርሱ ነገር ግልጽን ክርክር እንጂ ጠልቀህ አትከራከር:: በእነርሱም ጉዳይ ከመጽሐፉ ሰዎች አንድንም አትጠይቅ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَا تَقُولَنَّ لِشَاْيۡءٍ إِنِّي فَاعِلٞ ذَٰلِكَ غَدًا
23 ለማንኛዉም ነገር «እኔ ይህንን ነገ ሠሪ ነኝ።» አትበል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِلَّآ أَن يَشَآءَ ٱللَّهُۚ وَٱذۡكُر رَّبَّكَ إِذَا نَسِيتَ وَقُلۡ عَسَىٰٓ أَن يَهۡدِيَنِ رَبِّي لِأَقۡرَبَ مِنۡ هَٰذَا رَشَدٗا
24. «አላህ ቢሻ እሠራዋለሁ።» ብትል እንጂ። በረሳህ ጊዜም ጌታህን አውሳ። «ጌታዬም ከዚህ ይበልጥ ለቀጥታ የቀረበን ሊመራኝ ይከጀላል» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَبِثُواْ فِي كَهۡفِهِمۡ ثَلَٰثَ مِاْئَةٖ سِنِينَ وَٱزۡدَادُواْ تِسۡعٗا
25. በዋሻቸዉም ውስጥ ሶስት መቶ ዓመታትን ቆዩ:: ዘጠኝ አመታትንም ጨመሩ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلِ ٱللَّهُ أَعۡلَمُ بِمَا لَبِثُواْۖ لَهُۥ غَيۡبُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ أَبۡصِرۡ بِهِۦ وَأَسۡمِعۡۚ مَا لَهُم مِّن دُونِهِۦ مِن وَلِيّٖ وَلَا يُشۡرِكُ فِي حُكۡمِهِۦٓ أَحَدٗا
26.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ብቻ የቆዩትን ልክ በትክክል አዋቂ ነው። የሰማያትና የምድር ሚስጢር የእሱ ብቻ ነዉ። እርሱ (አላህ) ሁሉን ተመልካች ሁሉን ሰሚ መሆኑ ይግረምህ። ለእነርሱ ከእርሱ በስተቀር ምንም ወዳጅ የላቸዉም:: በፍርዱም አንድንም አያጋራም።» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱتۡلُ مَآ أُوحِيَ إِلَيۡكَ مِن كِتَابِ رَبِّكَۖ لَا مُبَدِّلَ لِكَلِمَٰتِهِۦ وَلَن تَجِدَ مِن دُونِهِۦ مُلۡتَحَدٗا
27.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ መጽሀፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ:: ለቃሎቹ ለዋጭ የላቸዉም:: ከርሱም በስተቀር መጠጊያን በፍጹም አታገኝም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់កះហ្វុី
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ