Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្វូសស៊ីឡាត់   អាយ៉ាត់:
۞ إِلَيۡهِ يُرَدُّ عِلۡمُ ٱلسَّاعَةِۚ وَمَا تَخۡرُجُ مِن ثَمَرَٰتٖ مِّنۡ أَكۡمَامِهَا وَمَا تَحۡمِلُ مِنۡ أُنثَىٰ وَلَا تَضَعُ إِلَّا بِعِلۡمِهِۦۚ وَيَوۡمَ يُنَادِيهِمۡ أَيۡنَ شُرَكَآءِي قَالُوٓاْ ءَاذَنَّٰكَ مَا مِنَّا مِن شَهِيدٖ
47. የትንሳኤ መከሰቻ ሰዐቱን ማወቅ ወደ እርሱ ብቻ ይመለሳል:: ከፍሬዎችም ከሽፋኖቻቸው አይወጡም ከሴትም አንዲትም አታረግዝም፤ አትወልድምም በእውቀቱ ቢሆን እንጂ:: «ተጋሪዎቼ የት ናቸው?» በማለት በሚጠራቸው ቀንም ከእኛ ውስጥ («ተጋሪ አለህ» ብሎ) ምንም መስካሪ አለመኖሩን አምነናል» ይላሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَضَلَّ عَنۡهُم مَّا كَانُواْ يَدۡعُونَ مِن قَبۡلُۖ وَظَنُّواْ مَا لَهُم مِّن مَّحِيصٖ
48. ያም በፊት ይገዙት የነበሩት ጣዖት ከእነርሱ ይጠፋቸዋል:: ለእነርሱም ምንም መሸሻ የሌላቸው መሆኑን ያረጋግጣሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّا يَسۡـَٔمُ ٱلۡإِنسَٰنُ مِن دُعَآءِ ٱلۡخَيۡرِ وَإِن مَّسَّهُ ٱلشَّرُّ فَيَـُٔوسٞ قَنُوطٞ
49. ሰው በጎ ነገርን ከመለመን አይሰለችም:: ክፋት ቢያገኘው (ግን) ወዲያውኑ በጣም ተስፋ ቆራጭ ተበሳጭ ይሆናል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَئِنۡ أَذَقۡنَٰهُ رَحۡمَةٗ مِّنَّا مِنۢ بَعۡدِ ضَرَّآءَ مَسَّتۡهُ لَيَقُولَنَّ هَٰذَا لِي وَمَآ أَظُنُّ ٱلسَّاعَةَ قَآئِمَةٗ وَلَئِن رُّجِعۡتُ إِلَىٰ رَبِّيٓ إِنَّ لِي عِندَهُۥ لَلۡحُسۡنَىٰۚ فَلَنُنَبِّئَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِمَا عَمِلُواْ وَلَنُذِيقَنَّهُم مِّنۡ عَذَابٍ غَلِيظٖ
50. ካገኘችዉም መከራ በኋላ ከእኛ የሆነን እዝነት ብናቀምሰው «ይህ ለእኔ በስራየ የተገባኝ ነው፤ ሰዓቲቱም መጪ ናት ብየ አላስብም። ወደ ጌታየ ብመለስ (እንኳ) ለእኔ እርሱ ዘንድ መልካሚቱ ገነት በእርግጥ አለችኝ» ይላል:: እነዚህም የካዱትን ስራዎቻቸውን በእርግጥ እንነግራቸዋለን:: ከበረታዉም ስቃይም በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَآ أَنۡعَمۡنَا عَلَى ٱلۡإِنسَٰنِ أَعۡرَضَ وَنَـَٔا بِجَانِبِهِۦ وَإِذَا مَسَّهُ ٱلشَّرُّ فَذُو دُعَآءٍ عَرِيضٖ
51. በሰዉም ላይ ጸጋችንን በለገስን ጊዜ ከማመስገን ይዞራል በጎኑም ይርቃል:: መከራም ባገኘው ጊዜ የብዙ ልመና ባለቤት ይሆናል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ أَرَءَيۡتُمۡ إِن كَانَ مِنۡ عِندِ ٱللَّهِ ثُمَّ كَفَرۡتُم بِهِۦ مَنۡ أَضَلُّ مِمَّنۡ هُوَ فِي شِقَاقِۭ بَعِيدٖ
52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸው: «እስቲ ንገሩኝ ቁርኣን ከአላህ ዘንድ ቢሆንና ከዚያም በእርሱ ብትክዱ፤ ከእውነት በራቀ ጭቅጭቅ ላይ ከሆነ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማን ነው?»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
سَنُرِيهِمۡ ءَايَٰتِنَا فِي ٱلۡأٓفَاقِ وَفِيٓ أَنفُسِهِمۡ حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَهُمۡ أَنَّهُ ٱلۡحَقُّۗ أَوَلَمۡ يَكۡفِ بِرَبِّكَ أَنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ
53. እርሱም (ቁርኣን) እውነት መሆኑ ለእነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ በአጽናፎችና በነፍሶቻቸዉም ውስጥ ያሉትን ታዐምራቶቻችንን በእርግጥ እናሳያቸዋለን:: ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸዉምን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَآ إِنَّهُمۡ فِي مِرۡيَةٖ مِّن لِّقَآءِ رَبِّهِمۡۗ أَلَآ إِنَّهُۥ بِكُلِّ شَيۡءٖ مُّحِيطُۢ
54. (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እነርሱ ከጌታቸው ጋር መገናኘትን በመጠራጠር ውስጥ ናቸው:: (ሙስሊሞች ሆይ!) አስተውሉ! እርሱ በነገሩ ሁሉ በእውቀቱ ከባቢ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្វូសស៊ីឡាត់
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ