Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្វូសស៊ីឡាត់   អាយ៉ាត់:
إِنَّ ٱلَّذِينَ قَالُواْ رَبُّنَا ٱللَّهُ ثُمَّ ٱسۡتَقَٰمُواْ تَتَنَزَّلُ عَلَيۡهِمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَلَّا تَخَافُواْ وَلَا تَحۡزَنُواْ وَأَبۡشِرُواْ بِٱلۡجَنَّةِ ٱلَّتِي كُنتُمۡ تُوعَدُونَ
30. እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉና ከዚያም ቀጥ ያሉ። እንዲህ እያሉ መላዕክቱ በነርሱ ላይ ይወርዳሉ: «አትፍሩ አትዘኑ:: በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላቸሁ:: በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
نَحۡنُ أَوۡلِيَآؤُكُمۡ فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَفِي ٱلۡأٓخِرَةِۖ وَلَكُمۡ فِيهَا مَا تَشۡتَهِيٓ أَنفُسُكُمۡ وَلَكُمۡ فِيهَا مَا تَدَّعُونَ
31. «እኛ በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም ረዳቶቻችሁ ነን! ለእናተም በእርሷ ውስጥ ነፍሶቻችሁ የሚሹት ሁሉ አላችሁ:: ለእናንተም በእርሷ ውስጥ የምታዙት ሁሉ አለላችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
نُزُلٗا مِّنۡ غَفُورٖ رَّحِيمٖ
32. «መሀሪና አዛኝ ከሆነው አላህ መስተንግዶ ሲሆን» ይባላሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَنۡ أَحۡسَنُ قَوۡلٗا مِّمَّن دَعَآ إِلَى ٱللَّهِ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ ٱلۡمُسۡلِمِينَ
33. ወደ አላህ ከጠራንና መልካምንም ከሰራ፤ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለው ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَا تَسۡتَوِي ٱلۡحَسَنَةُ وَلَا ٱلسَّيِّئَةُۚ ٱدۡفَعۡ بِٱلَّتِي هِيَ أَحۡسَنُ فَإِذَا ٱلَّذِي بَيۡنَكَ وَبَيۡنَهُۥ عَدَٰوَةٞ كَأَنَّهُۥ وَلِيٌّ حَمِيمٞ
34. መልካሚቱና ክፉይቱም ጸባይ አይስተካሉም በዚያች እርሷ መልካም በሆነችው ጸባይ መጥፎይቱን ገፍትር፤ ያን ጊዜ ባንተና በእርሱ መካከል ጠብ ያለው ሰው እርሱ ልክ እንደ ወዳጅ ዘመድ ይሆናል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَا يُلَقَّىٰهَآ إِلَّا ٱلَّذِينَ صَبَرُواْ وَمَا يُلَقَّىٰهَآ إِلَّا ذُو حَظٍّ عَظِيمٖ
35. ይህችንም ጸባይ እነዚያን የታገሱት እንጂ ሌላው አያገኛትም:: የትልቅም እድል ባለቤት እንጂ ማንም አያገኛትም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ ٱلشَّيۡطَٰنِ نَزۡغٞ فَٱسۡتَعِذۡ بِٱللَّهِۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡعَلِيمُ
36. ከሰይጣን ጉትጎታ ቢያገኝህ (ከመልካም ጸባይ ቢመልስህ) በአላህ ተጠበቅ እነሆ እርሱ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِ ٱلَّيۡلُ وَٱلنَّهَارُ وَٱلشَّمۡسُ وَٱلۡقَمَرُۚ لَا تَسۡجُدُواْ لِلشَّمۡسِ وَلَا لِلۡقَمَرِ وَٱسۡجُدُواْۤ لِلَّهِۤ ٱلَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمۡ إِيَّاهُ تَعۡبُدُونَ
37. ሌሊትና ቀንም ጸሀይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው። ለጸሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ:: እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደሆናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَإِنِ ٱسۡتَكۡبَرُواْ فَٱلَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ يُسَبِّحُونَ لَهُۥ بِٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَهُمۡ لَا يَسۡـَٔمُونَ۩
38. ቢኮሩም እነዚያ በጌታህ ዘንድ ያሉት መላዕክት በቀንም በሌሊትም ለእርሱ ያወድሳሉ:: እነርሱም አይሰለቹም:: {1}
{1} እዚህ የቲላዋ ሱጁድ ይደረጋል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្វូសស៊ីឡាត់
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ