Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្វូសស៊ីឡាត់   អាយ៉ាត់:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنَّكَ تَرَى ٱلۡأَرۡضَ خَٰشِعَةٗ فَإِذَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡهَا ٱلۡمَآءَ ٱهۡتَزَّتۡ وَرَبَتۡۚ إِنَّ ٱلَّذِيٓ أَحۡيَاهَا لَمُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰٓۚ إِنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ
39. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ምድርን ደረቅ ሆና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው:: በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ በቡቃያዎችዋ ትላወሳለች፤ ትነፋለችም። ያ ህያው ያደረጋት ጌታ በእርግጥ ሙታንንም ህያው አድራጊ ነው:: እርሱ በነገሩ ሁሉ ቻይ ነውና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا لَا يَخۡفَوۡنَ عَلَيۡنَآۗ أَفَمَن يُلۡقَىٰ فِي ٱلنَّارِ خَيۡرٌ أَم مَّن يَأۡتِيٓ ءَامِنٗا يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ ٱعۡمَلُواْ مَا شِئۡتُمۡ إِنَّهُۥ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٌ
40. እነዚያ አናቅጻችንን የሚያጣምሙ በእኛ ላይ አይደበቁም:: (የሚያጣምም) በእሳት ውስጥ የሚጣለው ይበልጣልን? ወይስ በትንሳኤ ቀን ደህነኛ ሆኖ የሚመጣው? የሻችሁትን ስሩ:: ዋጋችሁን ታገላችሁ:: እርሱም (አላህ) የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِٱلذِّكۡرِ لَمَّا جَآءَهُمۡۖ وَإِنَّهُۥ لَكِتَٰبٌ عَزِيزٞ
41. እነዚያ በቁርኣን እርሱ አሸናፊው መጽሐፍ ሲሆን በመጣላቸው ጊዜ የካዱ ሁሉ ጠፊዎች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّا يَأۡتِيهِ ٱلۡبَٰطِلُ مِنۢ بَيۡنِ يَدَيۡهِ وَلَا مِنۡ خَلۡفِهِۦۖ تَنزِيلٞ مِّنۡ حَكِيمٍ حَمِيدٖ
42. ከኋላዉም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም:: ጥበበኛ ምስጉን ከሆነው ጌታ የተወረደ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مَّا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدۡ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِن قَبۡلِكَۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغۡفِرَةٖ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٖ
43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለነበሩት መልዕክተኞች የተባለው ቢጤ እንጂ ላንተ ሌላ አይባልም:: ጌታህ የምህረት ባለቤትና የአሳማሚ ቅጣትም ባለቤት ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَوۡ جَعَلۡنَٰهُ قُرۡءَانًا أَعۡجَمِيّٗا لَّقَالُواْ لَوۡلَا فُصِّلَتۡ ءَايَٰتُهُۥٓۖ ءَا۬عۡجَمِيّٞ وَعَرَبِيّٞۗ قُلۡ هُوَ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ هُدٗى وَشِفَآءٞۚ وَٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ فِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٞ وَهُوَ عَلَيۡهِمۡ عَمًىۚ أُوْلَٰٓئِكَ يُنَادَوۡنَ مِن مَّكَانِۭ بَعِيدٖ
44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአዕጀምኛ የሆነ ቁርኣን ባረግነው ኖሮ «አናቅጹ በምናውቀው ቋንቋ አይብራሩም ኖሯልን? (ቁርኣኑ) አዕጀምኛና (መልዕክተኛው) አረባዊ ይሆናልን?» ባሉ ነበር:: እርሱ ለእነዚያ በአላህ ላመኑት ሰዎች መመሪያና መፈወሻ ነው:: እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው ውስጥ ድንቁርና ነው (አይሰሙትም):: እርሱ በእነርሱ ላይ እውርነት ነው:: እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጠሩ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ فَٱخۡتُلِفَ فِيهِۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۚ وَإِنَّهُمۡ لَفِي شَكّٖ مِّنۡهُ مُرِيبٖ
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው። በእርሱም ተለያዩበት። ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው በተፈረደ ነበር፤ እነርሱም በእርሱ አወላዋይ በሆነ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مَّنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ أَسَآءَ فَعَلَيۡهَاۗ وَمَا رَبُّكَ بِظَلَّٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ
46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) መልካምን የሰራ ለነፍሱ ነው:: ያጠፋም በእርሷው ላይ ነው:: ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្វូសស៊ីឡាត់
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ