Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្គហ្វៀរ   អាយ៉ាត់:
هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَكُم مِّن تُرَابٖ ثُمَّ مِن نُّطۡفَةٖ ثُمَّ مِنۡ عَلَقَةٖ ثُمَّ يُخۡرِجُكُمۡ طِفۡلٗا ثُمَّ لِتَبۡلُغُوٓاْ أَشُدَّكُمۡ ثُمَّ لِتَكُونُواْ شُيُوخٗاۚ وَمِنكُم مَّن يُتَوَفَّىٰ مِن قَبۡلُۖ وَلِتَبۡلُغُوٓاْ أَجَلٗا مُّسَمّٗى وَلَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ
67. (ሰዎች ሆይ!) እርሱ (አላህ) ያ ከዐፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው:: ከዚያም ህፃን አድርጎ ያወጣችኋል:: ከዚያም ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ፤ ከዚያም ሽማግሌዎች ትሆኑ ዘንድ ያቆያችኋል:: ከናንተም ውስጥ ከዚህ በፊት የሚሞት አለ:: ይህንንም ያደረገው ኑራችሁ የተወሰነ ጊዜም ልትደርሱ ታውቁም ዘንድ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هُوَ ٱلَّذِي يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۖ فَإِذَا قَضَىٰٓ أَمۡرٗا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ
68. እርሱ (አላህ) ያ ህያው የሚያደርግና የሚያሞትም ነው:: አንዳችን ነገር በሻም ጊዜ ለእርሱ የሚለው ሁን ነው ወዲያዉም ይሆናል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَمۡ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِيٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ أَنَّىٰ يُصۡرَفُونَ
69.(መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወደ እነዚያ በአላህ አናቅጽ ወደሚከራከሩት ከእምነት እንዴት እንደሚመለሱ አታይምን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِٱلۡكِتَٰبِ وَبِمَآ أَرۡسَلۡنَا بِهِۦ رُسُلَنَاۖ فَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ
70. ወደ እነዚያ በመጽሐፉ በዚያም መልዕክተኞቻችንን በእርሱ በላክንበት ወዳስተባበሉበት አታይምን? ወደፊትም ያውቃሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِذِ ٱلۡأَغۡلَٰلُ فِيٓ أَعۡنَٰقِهِمۡ وَٱلسَّلَٰسِلُ يُسۡحَبُونَ
71. እንዘዝላዎቹና ሰንሰለቶቹ በአንገቶቻቸው ላይ በተደረጉ ጊዜ (በእርሷ) ይጎተታሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فِي ٱلۡحَمِيمِ ثُمَّ فِي ٱلنَّارِ يُسۡجَرُونَ
72. በገሀነም ውስጥ ይጎተታሉ፤ ከዚያም በእሳት ውስጥ ይማገዳሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ثُمَّ قِيلَ لَهُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡ تُشۡرِكُونَ
73. ከዚያም ለእነርሱ ይባላሉ፡- «(በአላህ) ታጋሯቸው የነበራችሁት የታሉ?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مِن دُونِ ٱللَّهِۖ قَالُواْ ضَلُّواْ عَنَّا بَل لَّمۡ نَكُن نَّدۡعُواْ مِن قَبۡلُ شَيۡـٔٗاۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ ٱلۡكَٰفِرِينَ
74. ከአላህ ሌላ የምታጋሩዋቸው (የት አሉ)?» «ከእኛ ተሰወሩብን፤ ከቶ ከዚህ በፊት ምንም የምንገዛ አልነበርንም» ይላሉ:: ልክ እንደዚሁ አላህ ካሐዲያንን ያሳስታል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ذَٰلِكُم بِمَا كُنتُمۡ تَفۡرَحُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ بِغَيۡرِ ٱلۡحَقِّ وَبِمَا كُنتُمۡ تَمۡرَحُونَ
75. «ይህ (ቅጣታችሁ) ያላአግባብ በምድር ውስጥ ትደሰቱ በነበራችሁትና ትንበጣረሩ በነበራችሁት ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱدۡخُلُوٓاْ أَبۡوَٰبَ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَاۖ فَبِئۡسَ مَثۡوَى ٱلۡمُتَكَبِّرِينَ
76. የገሀነምን በሮች ውስጧ ዘወታሪዎች ስትሆኑ ግቡ።» (ይባላሉ)። የትዕቢተኞችም መኖሪያ (ገሀነም) ምን ትከፋ!
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَٱصۡبِرۡ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞۚ فَإِمَّا نُرِيَنَّكَ بَعۡضَ ٱلَّذِي نَعِدُهُمۡ أَوۡ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِلَيۡنَا يُرۡجَعُونَ
77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፤ የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን በህይወትህ ብናሳይህ መልካም ነው:: ወይም ሳናሳይህ ብንገድልህ ወደ እኛ ይመለሳሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្គហ្វៀរ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ