Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្គហ្វៀរ   អាយ៉ាត់:
إِنَّ ٱلسَّاعَةَ لَأٓتِيَةٞ لَّا رَيۡبَ فِيهَا وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤۡمِنُونَ
59. ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት:: በእርሷ ጥርጥር የለም:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያምኑም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدۡعُونِيٓ أَسۡتَجِبۡ لَكُمۡۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسۡتَكۡبِرُونَ عَنۡ عِبَادَتِي سَيَدۡخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ
60. (ባሮቼ ሆይ!) ጌታችሁም አለ: «ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና። እነዚያ እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነም በእርግጥ ይገባሉ።»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱللَّهُ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيۡلَ لِتَسۡكُنُواْ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبۡصِرًاۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشۡكُرُونَ
61. አላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት ጨለማ፤ ቀንኑ ደግሞ ልትሰሩበት የሚያሳይ ብርሃን ያደረገላችሁ ነው:: አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነውና:: ግን አብዛሀኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡ خَٰلِقُ كُلِّ شَيۡءٖ لَّآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَۖ فَأَنَّىٰ تُؤۡفَكُونَ
62. ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው:: የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ታዲያ ከእምነት ወዴት ትመለሳላችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
كَذَٰلِكَ يُؤۡفَكُ ٱلَّذِينَ كَانُواْ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ يَجۡحَدُونَ
63. ልክ እንደዚሁ እነዚያ በአላህ አናቅጽ ይክዱ የነበሩት ከእምነት ይመለሳሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱللَّهُ ٱلَّذِي جَعَلَ لَكُمُ ٱلۡأَرۡضَ قَرَارٗا وَٱلسَّمَآءَ بِنَآءٗ وَصَوَّرَكُمۡ فَأَحۡسَنَ صُوَرَكُمۡ وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمۡۖ فَتَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
64. (ሰዎች ሆይ)! አላህ ያ ምድርን መርጊያ ሰማይንም ጣሪያ ያደረገላችሁ ነው፡፡ የቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም ያሳመረ፤ ከጣፋጭ ሲሳዮችም የሰጣችሁ ነው:: ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው። የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هُوَ ٱلۡحَيُّ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ فَٱدۡعُوهُ مُخۡلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَۗ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
65. እርሱ ብቻ ሁል ጊዜ ህያው ነው:: ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: ሃይማኖትንም ለርሱ ያጠራችሁ ስትሆኑ «ምስጋና ሁሉ ለዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ ብቻ ይገባው›› የምትሉ ሆናችሁ ተገዙት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ قُلۡ إِنِّي نُهِيتُ أَنۡ أَعۡبُدَ ٱلَّذِينَ تَدۡعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَمَّا جَآءَنِيَ ٱلۡبَيِّنَٰتُ مِن رَّبِّي وَأُمِرۡتُ أَنۡ أُسۡلِمَ لِرَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
66. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እኔ ከጌታዬ አስረጂዎች በመጡልኝ ጊዜ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዙዋቸውን እንዳልገዛ ተከልክያለሁ፤ ለዓለማትም ጌታ ብቻም እንድገዛ ታዝዣለሁ።» በላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្គហ្វៀរ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ