Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្គហ្វៀរ   អាយ៉ាត់:
ٱلۡيَوۡمَ تُجۡزَىٰ كُلُّ نَفۡسِۭ بِمَا كَسَبَتۡۚ لَا ظُلۡمَ ٱلۡيَوۡمَۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلۡحِسَابِ
17. «ዛሬ ነፍስ ሁሉ በሰራችው ስራ ትመነዳለች፤ ዛሬ በደል የለም:: አላህ በእርግጥ ምርመራው ፈጣን ነው።» ይባላል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَنذِرۡهُمۡ يَوۡمَ ٱلۡأٓزِفَةِ إِذِ ٱلۡقُلُوبُ لَدَى ٱلۡحَنَاجِرِ كَٰظِمِينَۚ مَا لِلظَّٰلِمِينَ مِنۡ حَمِيمٖ وَلَا شَفِيعٖ يُطَاعُ
18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ቅርቢቱንም የትንሳኤ ቀን ልቦች ጭንቀትን የተሞሉ ሆነው ላንቃዎች ዘንድ የሚደርሱበትን ጊዜ አስጠንቅቃቸው:: ለበዳዮች ምንም ወዳጅና ተሰሚ አማላጅ የላቸዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَعۡلَمُ خَآئِنَةَ ٱلۡأَعۡيُنِ وَمَا تُخۡفِي ٱلصُّدُورُ
19. አላህ የዓይኖችን ክዳት ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱللَّهُ يَقۡضِي بِٱلۡحَقِّۖ وَٱلَّذِينَ يَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَقۡضُونَ بِشَيۡءٍۗ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ
20. አላህም በእውነት ይፈርዳል:: እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚገዟቸው በምንም አይፈርዱም:: አላህ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ أَوَلَمۡ يَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَيَنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ كَانُواْ مِن قَبۡلِهِمۡۚ كَانُواْ هُمۡ أَشَدَّ مِنۡهُمۡ قُوَّةٗ وَءَاثَارٗا فِي ٱلۡأَرۡضِ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمۡ وَمَا كَانَ لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن وَاقٖ
21. የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ፍፃሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? በሀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶች ከእነርሱም ይበልጥ የበረቱ ነበሩ:: አላህም በኃጢአቶቻቸው ያዛቸው። ለእነርሱም ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ አልነበራቸዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ كَانَت تَّأۡتِيهِمۡ رُسُلُهُم بِٱلۡبَيِّنَٰتِ فَكَفَرُواْ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُۚ إِنَّهُۥ قَوِيّٞ شَدِيدُ ٱلۡعِقَابِ
22. ይህ (መያዝ) እነርሱ መልዕክተኞቻቸው በተዓምራት ይመጡባቸው ስለ ነበሩና ስለካዱ ነው:: አላህም ያዛቸው። እርሱ ኃያል፤ ቅጣተ ብርቱ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَا وَسُلۡطَٰنٖ مُّبِينٍ
23. ሙሳንም በተዓምራቶቻችንና በግልጽ ማስረጃ በእርግጥ ላክነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَهَٰمَٰنَ وَقَٰرُونَ فَقَالُواْ سَٰحِرٞ كَذَّابٞ
24. ወደ ፈርዖን ወደ ሃማን እና ወደ ቃሩንም ላክነው:: «ድግምተኛ እና ውሸታም ነው» አሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَلَمَّا جَآءَهُم بِٱلۡحَقِّ مِنۡ عِندِنَا قَالُواْ ٱقۡتُلُوٓاْ أَبۡنَآءَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مَعَهُۥ وَٱسۡتَحۡيُواْ نِسَآءَهُمۡۚ وَمَا كَيۡدُ ٱلۡكَٰفِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَٰلٖ
25. ከእኛ ዘንድ እውነትን ይዞ በመጣላቸውም ጊዜ: «የእነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑት ሰዎች ወንድ ልጆች ግደሉ፤ ሴቶቻቸውንም አስቀሩ።» አሉ፤ የከሓዲያንም ተንኮል በጥፋት ውስጥ እንጂ ሌላ አይደለም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ហ្គហ្វៀរ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ