Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន   អាយ៉ាត់:
ثُمَّ أَنزَلَ عَلَيۡكُم مِّنۢ بَعۡدِ ٱلۡغَمِّ أَمَنَةٗ نُّعَاسٗا يَغۡشَىٰ طَآئِفَةٗ مِّنكُمۡۖ وَطَآئِفَةٞ قَدۡ أَهَمَّتۡهُمۡ أَنفُسُهُمۡ يَظُنُّونَ بِٱللَّهِ غَيۡرَ ٱلۡحَقِّ ظَنَّ ٱلۡجَٰهِلِيَّةِۖ يَقُولُونَ هَل لَّنَا مِنَ ٱلۡأَمۡرِ مِن شَيۡءٖۗ قُلۡ إِنَّ ٱلۡأَمۡرَ كُلَّهُۥ لِلَّهِۗ يُخۡفُونَ فِيٓ أَنفُسِهِم مَّا لَا يُبۡدُونَ لَكَۖ يَقُولُونَ لَوۡ كَانَ لَنَا مِنَ ٱلۡأَمۡرِ شَيۡءٞ مَّا قُتِلۡنَا هَٰهُنَاۗ قُل لَّوۡ كُنتُمۡ فِي بُيُوتِكُمۡ لَبَرَزَ ٱلَّذِينَ كُتِبَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡقَتۡلُ إِلَىٰ مَضَاجِعِهِمۡۖ وَلِيَبۡتَلِيَ ٱللَّهُ مَا فِي صُدُورِكُمۡ وَلِيُمَحِّصَ مَا فِي قُلُوبِكُمۡۚ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
154. ከዚያም ከጭንቅ በኋላ ጸጥታን ከናንተ ከፊሎችን የሚሸፍንን እንቅልፍ በእናንተ ላይ አወረደ:: ከፊሎችንም ነፍሶቻቸው በእርግጥ አሳሰቧቸው:: እውነት ያልሆነውን የመሀይምነትን መጠራጠር በአላህ ላይ ይጠራጠራሉ:: «በነገሩ ላይ ምንም የመወሰን መብት አለን? (የለንም።») ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «የመወሰን መብት ሁሉ የአላህ ብቻ ነው።» በላቸው:: ላንተ ግልጽ የማያደርጉትን በልቦቻቸው ውስጥ ይደብቃሉ:: «የመወሰን መብት ቢኖረን ኖሮ በዚህ ቦታ ላይ ባልተገደልን ነበር» ይላሉ:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በቤታችሁ ውስጥ በሆናችሁም ኖሮ እነዚያ በእነርሱ ላይ መገደል የተጸፈባቸው ወደየመውደቂያቸው በወጡ ነበር።» በላቸው:: አላህ ፍርዱን ሊፈጽምና በደረቶቻችሁም ውስጥ ያለውን ሊፈትን በልቦቻችሁም ውስጥ ያለውን ነገር ሊገልጽ ይህንን ሰራ:: አላህ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ነገር ሳይቀር አዋቂ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ تَوَلَّوۡاْ مِنكُمۡ يَوۡمَ ٱلۡتَقَى ٱلۡجَمۡعَانِ إِنَّمَا ٱسۡتَزَلَّهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ بِبَعۡضِ مَا كَسَبُواْۖ وَلَقَدۡ عَفَا ٱللَّهُ عَنۡهُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ حَلِيمٞ
155.(የመልዕክተኛችን ባልደረቦች ሆይ!) እነዚያ ሁለቱ ቡድኖች በተገናኙ ቀን ከናንተ የሸሹትን ሰዎች በዚያ በሰሩት ከፊል ምክንያት ያሳሳታቸው ሰይጣን ነው:: አላህ ከእነርሱ በእርግጥ ይቅር ብሏል:: አላህ መሀሪና ለቅጣት የማይቸኩል ታጋሽ ነውና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ وَقَالُواْ لِإِخۡوَٰنِهِمۡ إِذَا ضَرَبُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ أَوۡ كَانُواْ غُزّٗى لَّوۡ كَانُواْ عِندَنَا مَا مَاتُواْ وَمَا قُتِلُواْ لِيَجۡعَلَ ٱللَّهُ ذَٰلِكَ حَسۡرَةٗ فِي قُلُوبِهِمۡۗ وَٱللَّهُ يُحۡيِۦ وَيُمِيتُۗ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ
156. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እነደነዚያ በአላህ እንደካዱትና ስለ ወንድሞቻቸው በምድር ላይ በተጓዙና ወይም ዘማቾች በሆኑ ጊዜ እኛ ዘንድ በነበሩ ኖሮ ባልሞቱ ባልተገደሉም ነበር እንደሚሉት ሰዎች አትሁኑ:: አላህ በልቦቻቸው ውስጥ ጸጸት ያደርግባቸው ዘንድ ይህንን አሉ:: አላህ የፈለገውን ሕያው ያደርጋል:: የፈለገውን ይገድላልም:: አላህ የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَئِن قُتِلۡتُمۡ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ أَوۡ مُتُّمۡ لَمَغۡفِرَةٞ مِّنَ ٱللَّهِ وَرَحۡمَةٌ خَيۡرٞ مِّمَّا يَجۡمَعُونَ
157. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) በአላህ መንገድ ላይ ስትዋጉ ብትገደሉ ወይም ብትሞቱ ከአላህ የሆነው ምህረትና እዝነት እነርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት ሁሉ የእናንተ ምንዳ በላጭ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ