Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន   អាយ៉ាត់:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ إِن تُطِيعُواْ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ يَرُدُّوكُمۡ عَلَىٰٓ أَعۡقَٰبِكُمۡ فَتَنقَلِبُواْ خَٰسِرِينَ
149. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአላህ የካዱትን ብትታዘዙ ወደ ኋላችሁ ይመልሷችኋል። ከከሳሪዎቹም ትሆናላችሁ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
بَلِ ٱللَّهُ مَوۡلَىٰكُمۡۖ وَهُوَ خَيۡرُ ٱلنَّٰصِرِينَ
150. ይልቁን አላህ ብቻ ረዳታችሁ ነው:: እርሱ ከረዳቶች ሁሉ በላጭ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
سَنُلۡقِي فِي قُلُوبِ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ ٱلرُّعۡبَ بِمَآ أَشۡرَكُواْ بِٱللَّهِ مَا لَمۡ يُنَزِّلۡ بِهِۦ سُلۡطَٰنٗاۖ وَمَأۡوَىٰهُمُ ٱلنَّارُۖ وَبِئۡسَ مَثۡوَى ٱلظَّٰلِمِينَ
151. በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ አላህ በእሱ አስረጂ ያላወረደበትን ነገር በአላህ በማጋራታቸው ምክንያት ፍርሃትን እንጥላለን:: መኖሪያቸዉም የገሀነም እሳት ናት:: የበዳዮች መኖሪያ የሆነችው ገሀነምም መኖሪያነቷ ምን ትከፋ!
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ صَدَقَكُمُ ٱللَّهُ وَعۡدَهُۥٓ إِذۡ تَحُسُّونَهُم بِإِذۡنِهِۦۖ حَتَّىٰٓ إِذَا فَشِلۡتُمۡ وَتَنَٰزَعۡتُمۡ فِي ٱلۡأَمۡرِ وَعَصَيۡتُم مِّنۢ بَعۡدِ مَآ أَرَىٰكُم مَّا تُحِبُّونَۚ مِنكُم مَّن يُرِيدُ ٱلدُّنۡيَا وَمِنكُم مَّن يُرِيدُ ٱلۡأٓخِرَةَۚ ثُمَّ صَرَفَكُمۡ عَنۡهُمۡ لِيَبۡتَلِيَكُمۡۖ وَلَقَدۡ عَفَا عَنكُمۡۗ وَٱللَّهُ ذُو فَضۡلٍ عَلَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ
152. በእርግጥ አላህ በፈቃዱ ጠላቶቻችሁን በምትጨፈጭፏቸው ጊዜ ቃልኪዳንን በእርግጥ አረጋገጠላችሁ:: የምትወዱትንም ነገር ካሳያችሁ በኋላ በፈራችሁ፣ በትዕዛዙም በተጨቃጨቃችሁና ባመፃችሁም ጊዜ (ግን እርዳታውን ከለከላችሁ):: ከናንተ ውስጥ ቅርቢቱን ዓለም የሚሻ አለ:: ከናንተም ውስጥ የመጨርሻይቱን ዓለም የሚሻ አለ:: ከዚያም ሊሞክራችሁ ከእነርሱ አዞራችሁ:: በእርግጥም ለእናንተ ይቅርታ አደረገላችሁ:: አላህ ሁልጊዜም በአማኞች ላይ የችሮታ ባለቤት ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ إِذۡ تُصۡعِدُونَ وَلَا تَلۡوُۥنَ عَلَىٰٓ أَحَدٖ وَٱلرَّسُولُ يَدۡعُوكُمۡ فِيٓ أُخۡرَىٰكُمۡ فَأَثَٰبَكُمۡ غَمَّۢا بِغَمّٖ لِّكَيۡلَا تَحۡزَنُواْ عَلَىٰ مَا فَاتَكُمۡ وَلَا مَآ أَصَٰبَكُمۡۗ وَٱللَّهُ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ
153. (የመልዕክተኛችን ሙሐመድ ባልደረቦች ሆይ!) መልዕክተኛው ከኋላችሁ ሁኖ እየጠራችሁ የማትዞሩ ሆናችሁ በርቀት በምትሸሹ ጊዜ የሆነውን አስታውሱ:: ባመለጣችሁ እድልና በደረሰባችሁም ነገር አለማዘንን ሊያስተምራችሁ በሀሳብ ላይ ሀሳብን አደረሰባችሁ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውሰጠ አዋቂ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ