Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន   អាយ៉ាត់:
۞ وَسَارِعُوٓاْ إِلَىٰ مَغۡفِرَةٖ مِّن رَّبِّكُمۡ وَجَنَّةٍ عَرۡضُهَا ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلۡأَرۡضُ أُعِدَّتۡ لِلۡمُتَّقِينَ
133. ወደ ጌታችሁ ምህረትና ስፋቷ ሰባቱ ሰማያትንና ምድርን ያክል ወደ ሆነችው ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትሆን ተቻኮሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلَّذِينَ يُنفِقُونَ فِي ٱلسَّرَّآءِ وَٱلضَّرَّآءِ وَٱلۡكَٰظِمِينَ ٱلۡغَيۡظَ وَٱلۡعَافِينَ عَنِ ٱلنَّاسِۗ وَٱللَّهُ يُحِبُّ ٱلۡمُحۡسِنِينَ
134. ለእነዚያ በድሎትም ሆነ በችግር ጊዜ ለሚለግሱት፤ ቁጭትንም ገቺዎች፤ ለሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለሆኑት፤ አላህ በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ይወዳልና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱلَّذِينَ إِذَا فَعَلُواْ فَٰحِشَةً أَوۡ ظَلَمُوٓاْ أَنفُسَهُمۡ ذَكَرُواْ ٱللَّهَ فَٱسۡتَغۡفَرُواْ لِذُنُوبِهِمۡ وَمَن يَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ إِلَّا ٱللَّهُ وَلَمۡ يُصِرُّواْ عَلَىٰ مَا فَعَلُواْ وَهُمۡ يَعۡلَمُونَ
135. ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኃጢአቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት ተደግሳለች:: ከአላህ ሌላ ኃጢአቶችን የሚምር ማን ነው? (አንድም የለም::) በስህተት በሰሩት ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ የማይዘወትሩ ለሆኑት ሁሉ ተደግሳለች::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أُوْلَٰٓئِكَ جَزَآؤُهُم مَّغۡفِرَةٞ مِّن رَّبِّهِمۡ وَجَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ وَنِعۡمَ أَجۡرُ ٱلۡعَٰمِلِينَ
136. እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምህረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው:: የመልካም ሰሪዎች ሁሉ ምንዳ የሆነችው ገነት ምንኛ አማረች!
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَدۡ خَلَتۡ مِن قَبۡلِكُمۡ سُنَنٞ فَسِيرُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ فَٱنظُرُواْ كَيۡفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلۡمُكَذِّبِينَ
137. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) ከእናንተ በፊት በእርግጥ ብዙ አልፈዋል። በምድር ላይ ሂዱና ያስተባባዮች ፍፃሜ እንዴት እንደነበረ ተመልከቱ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هَٰذَا بَيَانٞ لِّلنَّاسِ وَهُدٗى وَمَوۡعِظَةٞ لِّلۡمُتَّقِينَ
138. ይህ ቁርኣን ለሰዎች ሁሉ ማብራርያ፤ ለጥንቁቆችም መመሪያና ገሳጭ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَا تَهِنُواْ وَلَا تَحۡزَنُواْ وَأَنتُمُ ٱلۡأَعۡلَوۡنَ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ
139. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ የበላዮች ናችሁና ትክክለኛ አማኞች እንደሆናችሁ አትድከሙ (አትስነፉ)። አትዘኑም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِن يَمۡسَسۡكُمۡ قَرۡحٞ فَقَدۡ مَسَّ ٱلۡقَوۡمَ قَرۡحٞ مِّثۡلُهُۥۚ وَتِلۡكَ ٱلۡأَيَّامُ نُدَاوِلُهَا بَيۡنَ ٱلنَّاسِ وَلِيَعۡلَمَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَيَتَّخِذَ مِنكُمۡ شُهَدَآءَۗ وَٱللَّهُ لَا يُحِبُّ ٱلظَّٰلِمِينَ
140. አማኞች ሆይ! የመቁስል ጉዳት ቢያገኛችሁ ሌሎች ህዝቦችም መሰሉ የመቁሰል ጉዳት አግኝቷቸዋል። እንዲሁ ቀናትን በሰዎች መካከል እናፈራርቃቸዋለን:: አላህ እነዚያን በትክክል በሱ ያመኑትን ሊለይና ከእናንተም መካከል ሰማዕታትን ሊመርጥ እንዲህ አይነት ቀናት እንዲፈራረቁ ያደርጋል:: አላህም በዳዮችን ሁሉ አይወድምና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាលីអុិមរ៉ន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ