Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្វូរកន   អាយ៉ាត់:
وَٱلَّذِينَ لَا يَدۡعُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ وَلَا يَقۡتُلُونَ ٱلنَّفۡسَ ٱلَّتِي حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلۡحَقِّ وَلَا يَزۡنُونَۚ وَمَن يَفۡعَلۡ ذَٰلِكَ يَلۡقَ أَثَامٗا
68. እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፤ ያችንም አላህ እርም ያደርጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉ እና የማያመነዝሩት ናቸው:: ይህንን የሚፈጽም ሰው ወንጀለኛ ይሆናል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يُضَٰعَفۡ لَهُ ٱلۡعَذَابُ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ وَيَخۡلُدۡ فِيهِۦ مُهَانًا
69. በትንሳኤ ቀን ቅጣት ይደራረብበታል:: በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ዘልአለሙን ይኖራል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِلَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ عَمَلٗا صَٰلِحٗا فَأُوْلَٰٓئِكَ يُبَدِّلُ ٱللَّهُ سَيِّـَٔاتِهِمۡ حَسَنَٰتٖۗ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورٗا رَّحِيمٗا
70. ተጸጽቶ የተመለሰና ያመነ መልካምንም የሰራ ሰው ብቻ ሲቀር እነዚያም አላህ መጥፎ ስራዎቻቸውን በመልካም ስራዎች ይለውጣል:: አላህም እጅግ መሓሪና አዛኝ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَن تَابَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَإِنَّهُۥ يَتُوبُ إِلَى ٱللَّهِ مَتَابٗا
71. ተጸጽቶ የተመለሰና መልካምን ተግባር የሰራ እርሱ በአላህ ዘንድ የተወደደን መመለስ ወደ አላህ ይመለሳል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱلَّذِينَ لَا يَشۡهَدُونَ ٱلزُّورَ وَإِذَا مَرُّواْ بِٱللَّغۡوِ مَرُّواْ كِرَامٗا
72. እነዚያ በሐሰት የማይጣዱ፤ በውድቅ ቃል (ተናጋሪ) አጠገብም ባለፉ ጊዜ የተከበሩ ሆነው የሚያልፉ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِّرُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ لَمۡ يَخِرُّواْ عَلَيۡهَا صُمّٗا وَعُمۡيَانٗا
73. እነዚያም በጌታቸው አናቅጽ በተገሠጹ ጊዜ (የተረዱ ተቀባዮች ሆነው እንጂ) ደንቆሮዎችና እውሮች ሆነው በእርሷ ላይ የማይደፉት ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱلَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا هَبۡ لَنَا مِنۡ أَزۡوَٰجِنَا وَذُرِّيَّٰتِنَا قُرَّةَ أَعۡيُنٖ وَٱجۡعَلۡنَا لِلۡمُتَّقِينَ إِمَامًا
74. እነዚያ «ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያን ለእኛ ስጠን፤ አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን።» የሚሉ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أُوْلَٰٓئِكَ يُجۡزَوۡنَ ٱلۡغُرۡفَةَ بِمَا صَبَرُواْ وَيُلَقَّوۡنَ فِيهَا تَحِيَّةٗ وَسَلَٰمًا
75. እነዚያ በመታገሳቸው የገነትን ሰገነቶች ይመነዳሉ:: በእርሷም ውስጥ ውዳሴንና ሰላምታን ይሰጣሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ حَسُنَتۡ مُسۡتَقَرّٗا وَمُقَامٗا
76. በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ሆነው (ይሰጣሉ):: መርጊያና መኖሪያይቱ ገነት አማረች::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ مَا يَعۡبَؤُاْ بِكُمۡ رَبِّي لَوۡلَا دُعَآؤُكُمۡۖ فَقَدۡ كَذَّبۡتُمۡ فَسَوۡفَ يَكُونُ لِزَامَۢا
77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ) «ጸሎታችሁ ባልነበረ ኖሮ ጌታዬ እናንተን ከምንም አይቆጥራችሁም ነበር:: አስተባበላችሁ:: እናም ወደ ፊት ቅጣት ያዣችሁ ይሆናል።» በላቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្វូរកន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ