Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្វូរកន   អាយ៉ាត់:
۞ وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرۡجُونَ لِقَآءَنَا لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡنَا ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ أَوۡ نَرَىٰ رَبَّنَاۗ لَقَدِ ٱسۡتَكۡبَرُواْ فِيٓ أَنفُسِهِمۡ وَعَتَوۡ عُتُوّٗا كَبِيرٗا
21. እነዚያ መገናኘታችንን የማይጠብቁ ሰዎች «በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም ወይም ጌታችንን ለምን አናይም?» አሉ። በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ። ታላቅንም አመጽ አመጹ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَوۡمَ يَرَوۡنَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ لَا بُشۡرَىٰ يَوۡمَئِذٖ لِّلۡمُجۡرِمِينَ وَيَقُولُونَ حِجۡرٗا مَّحۡجُورٗا
22. መላዕክትን በሚያዩበት ቀን በዚያ ጊዜ ለአመጸኞች የምስራች የላቸዉም። (መላዕክቱም) «የተከለከለ ክልክል» ይላሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَدِمۡنَآ إِلَىٰ مَا عَمِلُواْ مِنۡ عَمَلٖ فَجَعَلۡنَٰهُ هَبَآءٗ مَّنثُورًا
23. ወደ ሰሩት ስራም እናስባለን:: ከዚያም እንደ ተበተነ ትቢያ እናደርገዋለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَصۡحَٰبُ ٱلۡجَنَّةِ يَوۡمَئِذٍ خَيۡرٞ مُّسۡتَقَرّٗا وَأَحۡسَنُ مَقِيلٗا
24. የገነት ሰዎች በዚያ ቀን በመርጊያ የተሻሉ በማረፊያም በጣም ያማሩ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَوۡمَ تَشَقَّقُ ٱلسَّمَآءُ بِٱلۡغَمَٰمِ وَنُزِّلَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ تَنزِيلًا
25. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰማይ በደመና የምትቀደድበትንና መላእክትም መውረድን የሚወርዱበትን ቀን አስታውስ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلۡمُلۡكُ يَوۡمَئِذٍ ٱلۡحَقُّ لِلرَّحۡمَٰنِۚ وَكَانَ يَوۡمًا عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ عَسِيرٗا
26. እውነተኛው ንግስና በዚያ ቀን ለአር-ረህማን ብቻ ነው:: በከሓዲያን ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَوۡمَ يَعَضُّ ٱلظَّالِمُ عَلَىٰ يَدَيۡهِ يَقُولُ يَٰلَيۡتَنِي ٱتَّخَذۡتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِيلٗا
27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በዳይም «ዋ ምኞቴ! ከመልዕክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ምነው ይዤ በሆነ፤ እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆችን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَٰوَيۡلَتَىٰ لَيۡتَنِي لَمۡ أَتَّخِذۡ فُلَانًا خَلِيلٗا
28. «ዋ ጥፋቴ! እገሌን በወዳጅነት ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّقَدۡ أَضَلَّنِي عَنِ ٱلذِّكۡرِ بَعۡدَ إِذۡ جَآءَنِيۗ وَكَانَ ٱلشَّيۡطَٰنُ لِلۡإِنسَٰنِ خَذُولٗا
29. (የእምነት ቃል የሆነው) «ቁርኣን ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ።» ይላል:: ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነውና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالَ ٱلرَّسُولُ يَٰرَبِّ إِنَّ قَوۡمِي ٱتَّخَذُواْ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ مَهۡجُورٗا
30. መልዕክተኛዉም (ሙሐመድ) «ጌታዬ ሆይ! ህዝቦቼ ይህንን ቁርኣን የተተወ ነገር አደረጉት።» አለ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَكَذَٰلِكَ جَعَلۡنَا لِكُلِّ نَبِيٍّ عَدُوّٗا مِّنَ ٱلۡمُجۡرِمِينَۗ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ هَادِيٗا وَنَصِيرٗا
31. ልክ እንደዚሁም ለነብያቱ ሁሉ ከአመጸኞች የሆነ ጠላትን አድርገናል:: መሪነትና ረዳትነት በጌታህ በቃ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡلَا نُزِّلَ عَلَيۡهِ ٱلۡقُرۡءَانُ جُمۡلَةٗ وَٰحِدَةٗۚ كَذَٰلِكَ لِنُثَبِّتَ بِهِۦ فُؤَادَكَۖ وَرَتَّلۡنَٰهُ تَرۡتِيلٗا
32. እነዚያ በአላህ የካዱ ሰዎችም «ቁርኣንን በእርሱ ላይ ለምን በጠቅላላ በአንድ ጊዜ አልተወረደለትም።» አሉ። ልክ እንደዚሁ በእርሱ ልብህን ልናረጋ (ከፋፍለን በተለያየ አወረድነው):: ቀስ በቀስ መለያየትንም ለየነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្វូរកន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ