Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្វូរកន   អាយ៉ាត់:
وَلَا يَأۡتُونَكَ بِمَثَلٍ إِلَّا جِئۡنَٰكَ بِٱلۡحَقِّ وَأَحۡسَنَ تَفۡسِيرًا
33. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በየትኛዉም ጥያቄ አይመጡብህም እውነተኛውን መልስና መልካም ፍቹንም የምናመጣልህ ብንሆን እንጅ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلَّذِينَ يُحۡشَرُونَ عَلَىٰ وُجُوهِهِمۡ إِلَىٰ جَهَنَّمَ أُوْلَٰٓئِكَ شَرّٞ مَّكَانٗا وَأَضَلُّ سَبِيلٗا
34. እነዚያ በፊቶቻቻው ላይ እየተጎተቱ ወደ ገሀነም የሚሰበሰቡት እነዚያ ስፍራቸው የከፋ መንገዳቸዉም የጠመመ ናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ وَجَعَلۡنَا مَعَهُۥٓ أَخَاهُ هَٰرُونَ وَزِيرٗا
35. በእርግጥም ለሙሳ መጽሐፍን ሰጠነው:: ከእርሱም ጋር ወንድሙን ሃሩንን ረዳት አደረግንለት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَقُلۡنَا ٱذۡهَبَآ إِلَى ٱلۡقَوۡمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُواْ بِـَٔايَٰتِنَا فَدَمَّرۡنَٰهُمۡ تَدۡمِيرٗا
36. «ወደ እነዚያም በተዓምራታችን ወደ አስተባበሉት ህዝቦች ሂዱ።» አልናቸው። (አስዋሿቸዉም) ማጥፋትንም አጠፋናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَوۡمَ نُوحٖ لَّمَّا كَذَّبُواْ ٱلرُّسُلَ أَغۡرَقۡنَٰهُمۡ وَجَعَلۡنَٰهُمۡ لِلنَّاسِ ءَايَةٗۖ وَأَعۡتَدۡنَا لِلظَّٰلِمِينَ عَذَابًا أَلِيمٗا
37. የኑህን ሰዎችም መልዕክተኞችን ባስተባበሉ ጊዜ አሰመጥናቸው:: ለሰዎችም መገሰጫ አደረግናቸው፤ ለበደለኞችም አሳማሚን ቅጣት አዘጋጅተናል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَعَادٗا وَثَمُودَاْ وَأَصۡحَٰبَ ٱلرَّسِّ وَقُرُونَۢا بَيۡنَ ذَٰلِكَ كَثِيرٗا
38. ዓድንም፤ሰሙድንም፤ የረስ ሰዎችንና በዚህ መካከል የነበሩትንም ብዙ የክፍለ ዘመናት ህዝቦችንም አጠፋን።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَكُلّٗا ضَرَبۡنَا لَهُ ٱلۡأَمۡثَٰلَۖ وَكُلّٗا تَبَّرۡنَا تَتۡبِيرٗا
39. ሁሉንም (ገሠጽን):: ለእነርሱ ምሳሌዎችን ገለጽን:: ሁሉንም ማጥፋትን አጠፋናቸዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ أَتَوۡاْ عَلَى ٱلۡقَرۡيَةِ ٱلَّتِيٓ أُمۡطِرَتۡ مَطَرَ ٱلسَّوۡءِۚ أَفَلَمۡ يَكُونُواْ يَرَوۡنَهَاۚ بَلۡ كَانُواْ لَا يَرۡجُونَ نُشُورٗا
40. በዚያችም ክፉ ዝናብን በተዘነበችው ከተማ ላይ (የመካ ከሓዲያን) በእርግጥ መጥተዋል:: የሚያዩዋት አልነበሩምን? በእውነቱ መቀስቀስን የማይፈሩ ነበሩ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَا رَأَوۡكَ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَٰذَا ٱلَّذِي بَعَثَ ٱللَّهُ رَسُولًا
41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ባዩህም ጊዜ (እንዲህ) እያሉ መሳለቂያ እንጅ ሌላ አያደርጉህም: «ያ አላህ መልዕክተኛ እድርጎ የላከው ይህ ነውን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِن كَادَ لَيُضِلُّنَا عَنۡ ءَالِهَتِنَا لَوۡلَآ أَن صَبَرۡنَا عَلَيۡهَاۚ وَسَوۡفَ يَعۡلَمُونَ حِينَ يَرَوۡنَ ٱلۡعَذَابَ مَنۡ أَضَلُّ سَبِيلًا
42. «እነሆ በእርሷ ላይ መታገሳችን (ጽናታችን) ባልነበረ ኖሮ ከአማልክቶቻችን ሊያሳስተን ቀርቦ ነበር።» ሲሉም ይሳለቃሉ:: ወደ ፊትም ቅጣትን በሚያዩ ጊዜ መንገድን በጣም የተሳሳተው ማን እንደ ሆነ በእርግጥ ያኔ ያውቃሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَرَءَيۡتَ مَنِ ٱتَّخَذَ إِلَٰهَهُۥ هَوَىٰهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيۡهِ وَكِيلًا
43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘን ሰው አየህን? አንተም በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្វូរកន
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ