Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ម៉ារយុាំ   អាយ៉ាត់:
أَفَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي كَفَرَ بِـَٔايَٰتِنَا وَقَالَ لَأُوتَيَنَّ مَالٗا وَوَلَدًا
77. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንን በአናቅጻችን የካደውንና «በትንሣኤ ቀን ገንዘብም ሆነ ልጅ በእርግጥ እሰጣለሁ» ያለውን አየህን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَطَّلَعَ ٱلۡغَيۡبَ أَمِ ٱتَّخَذَ عِندَ ٱلرَّحۡمَٰنِ عَهۡدٗا
78. ሩቁን ምስጢር አወቀን ? ወይስ አዛኙ አምላክ ዘንድ ቃል ኪዳንን ያዘ?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
كَلَّاۚ سَنَكۡتُبُ مَا يَقُولُ وَنَمُدُّ لَهُۥ مِنَ ٱلۡعَذَابِ مَدّٗا
79. ከዚህ አቋሙ ይታቀብ:: አይሰጠዉም:: የሚለውን ሁሉ በእርግጥ እንጽፋለን:: ለእርሱም ከቅጣት ጭማሬን እንጨምርለታለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَنَرِثُهُۥ مَا يَقُولُ وَيَأۡتِينَا فَرۡدٗا
80. አለኝ የሚለውንም ሁሉ እንወርሰዋለን ወደ እኛም ብቻውን ሆኖ ይመጣል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةٗ لِّيَكُونُواْ لَهُمۡ عِزّٗا
81. ከአላህ ሌላ አማልክትን ለእነርሱ መከበሪያ አማላጅ እንዲሆኗቸው ያዙ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
كَلَّاۚ سَيَكۡفُرُونَ بِعِبَادَتِهِمۡ وَيَكُونُونَ عَلَيۡهِمۡ ضِدًّا
82. ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ (ይታቀቡ):: መገዛታቸውን በእርግጥ ወደፊት ይከዷቸዋል:: በእነርሱም ላይ ተቃራኒ (ባላጋራ) ይሆኑባቸዋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّآ أَرۡسَلۡنَا ٱلشَّيَٰطِينَ عَلَى ٱلۡكَٰفِرِينَ تَؤُزُّهُمۡ أَزّٗا
83. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሰይጣናትን በከሓዲያን ላይ በመጥፎ ሥራ የሚገፋፏቸው ሲሆኑ የላክንባቸው መሆናችንን አላየህምን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَلَا تَعۡجَلۡ عَلَيۡهِمۡۖ إِنَّمَا نَعُدُّ لَهُمۡ عَدّٗا
84. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በእነርሱም መቀጣት ላይ አትቸኩል:: ለእነርሱ ቀንን እንቆጥርላቸዋለንና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَوۡمَ نَحۡشُرُ ٱلۡمُتَّقِينَ إِلَى ٱلرَّحۡمَٰنِ وَفۡدٗا
85. ትክክለኛ አማኞችን የተከበሩ ቡድኖች ሆነው ወደ አዛኙ አምላክ የምንሰበሰብበትንና:
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَنَسُوقُ ٱلۡمُجۡرِمِينَ إِلَىٰ جَهَنَّمَ وِرۡدٗا
86. ከሓዲያንን የተጠሙ ሆነው ወደገሀነም የምንነዳበትን ቀን አስታውስ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّا يَمۡلِكُونَ ٱلشَّفَٰعَةَ إِلَّا مَنِ ٱتَّخَذَ عِندَ ٱلرَّحۡمَٰنِ عَهۡدٗا
87. አዛኙ አምላክ ዘንድ ቃል ኪዳንን የያዘ ቢሆን እንጂ ሌሎች ማማለድን አይችሉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالُواْ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَٰنُ وَلَدٗا
88. አጋሪዎች «አዛኙ አምላክ አላህ ልጅ ወለደ።» አሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّقَدۡ جِئۡتُمۡ شَيۡـًٔا إِدّٗا
89.(አጋሪዎች ሆይ!) እጅግ ከባድና መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
تَكَادُ ٱلسَّمَٰوَٰتُ يَتَفَطَّرۡنَ مِنۡهُ وَتَنشَقُّ ٱلۡأَرۡضُ وَتَخِرُّ ٱلۡجِبَالُ هَدًّا
90. ከዚህ ንግግራቸው ሰማያት ሊቀደዱ፤ ምድርም ልትሰነጠቅ፤ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَن دَعَوۡاْ لِلرَّحۡمَٰنِ وَلَدٗا
91. ይህም ለአዛኙ አምላክ ልጅ አለው ስላሉ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَا يَنۢبَغِي لِلرَّحۡمَٰنِ أَن يَتَّخِذَ وَلَدًا
92. አዛኙ ጌታ ልጅን መያዝ አይገባዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِن كُلُّ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ إِلَّآ ءَاتِي ٱلرَّحۡمَٰنِ عَبۡدٗا
93. በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ በትንሣኤ ቀን (ለአር-ረህማን) ለአዛኙ ጌታ ባሪያ ሆነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّقَدۡ أَحۡصَىٰهُمۡ وَعَدَّهُمۡ عَدّٗا
94. አላህ በእርግጥ በዕውቀቱ ከቧቸዋል:: መቁጠርንም ቆጥሯቸዋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَكُلُّهُمۡ ءَاتِيهِ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ فَرۡدًا
95. ሁሉም በትንሳኤ ቀን ለየብቻ ሆነው ወደ እርሱ መጪዎች ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ម៉ារយុាំ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ