Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ម៉ារយុាំ   អាយ៉ាត់:
وَنَٰدَيۡنَٰهُ مِن جَانِبِ ٱلطُّورِ ٱلۡأَيۡمَنِ وَقَرَّبۡنَٰهُ نَجِيّٗا
52. ከጡር ጋራ በስተቀኝ ጎን በኩልም ጠራነው። በሚስጥር ያነጋገርነውም ስንሆን አቀረብነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَوَهَبۡنَا لَهُۥ مِن رَّحۡمَتِنَآ أَخَاهُ هَٰرُونَ نَبِيّٗا
53. ከእዝነታችንም (ከችሮታችንም) ወንድሙን ሃሩንን ነብይ አደረግንለት።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱذۡكُرۡ فِي ٱلۡكِتَٰبِ إِسۡمَٰعِيلَۚ إِنَّهُۥ كَانَ صَادِقَ ٱلۡوَعۡدِ وَكَانَ رَسُولٗا نَّبِيّٗا
54. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢስማዒልንም አውሳ:: እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበርና። መልዕክተኛ ነብይም ነበር።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَكَانَ يَأۡمُرُ أَهۡلَهُۥ بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱلزَّكَوٰةِ وَكَانَ عِندَ رَبِّهِۦ مَرۡضِيّٗا
55. ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር:: በጌታዉም ዘንድ ተወዳጅ ነበር::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱذۡكُرۡ فِي ٱلۡكِتَٰبِ إِدۡرِيسَۚ إِنَّهُۥ كَانَ صِدِّيقٗا نَّبِيّٗا
56. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመጽሐፉ ውስጥ ኢድሪስንም አውሳ:: እርሱ እውነተኛ ነብይ ነበርና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَرَفَعۡنَٰهُ مَكَانًا عَلِيًّا
57. (ኢድሪስን) ወደ ከፍተኛም ስፍራ አነሳነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ أَنۡعَمَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِم مِّنَ ٱلنَّبِيِّـۧنَ مِن ذُرِّيَّةِ ءَادَمَ وَمِمَّنۡ حَمَلۡنَا مَعَ نُوحٖ وَمِن ذُرِّيَّةِ إِبۡرَٰهِيمَ وَإِسۡرَٰٓءِيلَ وَمِمَّنۡ هَدَيۡنَا وَٱجۡتَبَيۡنَآۚ إِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُ ٱلرَّحۡمَٰنِ خَرُّواْۤ سُجَّدٗاۤ وَبُكِيّٗا۩
58. እነዚህ (አሥሩ) እነዚያ አላህ በእነርሱ ላይ ችሮታውን የለገሰላቸው ከነብያት ከአዳም ዘር ከኑሕ ጋር በመርከቢቱ ላይ ከጫንናቸዉም ዘሮች ከኢብራሂምና ከኢስራኢልም ዘሮች ከመራናቸውና ከመረጥናቸዉም የሆኑት የአር-ረህማን አናቅጽ በእነርሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ ሰጋጆችና አልቃሾች ሆነው ወደ መሬት የሚወድቁ (የሚደፉ) ናቸው። {1}
{1} እዚህ ሱጁዱ ትላዋ ይደረጋል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ فَخَلَفَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡ خَلۡفٌ أَضَاعُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَٱتَّبَعُواْ ٱلشَّهَوَٰتِۖ فَسَوۡفَ يَلۡقَوۡنَ غَيًّا
59. ከእነርሱም በኋላ ሶላትን ያጎደሉ ከንቱ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ትውልዶች ተተኩ:: «ገይ» የሚባልን የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِلَّا مَن تَابَ وَءَامَنَ وَعَمِلَ صَٰلِحٗا فَأُوْلَٰٓئِكَ يَدۡخُلُونَ ٱلۡجَنَّةَ وَلَا يُظۡلَمُونَ شَيۡـٔٗا
60. ግና ከእነርሱ የተጸጸቱ በአላህ ያመኑ በጎንም ስራ የሰሩ ሰዎች ወደ ገነት ይገባሉ:: አንዳችንም አይበደሉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
جَنَّٰتِ عَدۡنٍ ٱلَّتِي وَعَدَ ٱلرَّحۡمَٰنُ عِبَادَهُۥ بِٱلۡغَيۡبِۚ إِنَّهُۥ كَانَ وَعۡدُهُۥ مَأۡتِيّٗا
61. የመኖሪያን ገነቶች ያችን አር-ረህማን ለባሮቹ በሩቅ ሆነው ሳሉ ተስፋ ቃል የገባላቸውን ይገባሉ:: እርሱ ተስፋው ሁልጊዜም ተፈጻሚ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّا يَسۡمَعُونَ فِيهَا لَغۡوًا إِلَّا سَلَٰمٗاۖ وَلَهُمۡ رِزۡقُهُمۡ فِيهَا بُكۡرَةٗ وَعَشِيّٗا
62. በእርሷ ሰላምን እንጂ ውድቅን ነገር አይሰሙም:: ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ ጧትም ማታም ሲሳያቸው አላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
تِلۡكَ ٱلۡجَنَّةُ ٱلَّتِي نُورِثُ مِنۡ عِبَادِنَا مَن كَانَ تَقِيّٗا
63. ይህ ያቺ ከባሮቻችን ጥንቁቆች ለሆኑት ሁሉ የምናወርሳት ገነት ናት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَا نَتَنَزَّلُ إِلَّا بِأَمۡرِ رَبِّكَۖ لَهُۥ مَا بَيۡنَ أَيۡدِينَا وَمَا خَلۡفَنَا وَمَا بَيۡنَ ذَٰلِكَۚ وَمَا كَانَ رَبُّكَ نَسِيّٗا
64. (ጂብሪልም ለነቢዩ) «በጌታህ ትእዛዝ እንጂ አንወርድም:: በፊታችን፤ በኋላችንና በዚህም መካከል ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው:: ጌታህም ረሺ አይደለም።» አለ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ម៉ារយុាំ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ