Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ម៉ារយុាំ   អាយ៉ាត់:
رَّبُّ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا بَيۡنَهُمَا فَٱعۡبُدۡهُ وَٱصۡطَبِرۡ لِعِبَٰدَتِهِۦۚ هَلۡ تَعۡلَمُ لَهُۥ سَمِيّٗا
65. እርሱ የሰማያትና የምድር በሁለቱም መካከል ላለው ሁሉ ጌታ ነውና ተገዛው:: እርሱን በመገዛትም ላይ ታገሥ:: ለእርሱ ሞክሼን ታውቃለህን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَقُولُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَءِذَا مَا مِتُّ لَسَوۡفَ أُخۡرَجُ حَيًّا
66. ሰው «በሞትኩ ጊዜ ወደ ፊት ህያው ሆኜ ከመቃብር እወጣለሁን?» ይላል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَوَلَا يَذۡكُرُ ٱلۡإِنسَٰنُ أَنَّا خَلَقۡنَٰهُ مِن قَبۡلُ وَلَمۡ يَكُ شَيۡـٔٗا
67. ሰው ከዚህ በፊት ምንም ነገር ያልነበረ ሲሆን የፈጠርነው መሆኑን አያስታውስምን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَوَرَبِّكَ لَنَحۡشُرَنَّهُمۡ وَٱلشَّيَٰطِينَ ثُمَّ لَنُحۡضِرَنَّهُمۡ حَوۡلَ جَهَنَّمَ جِثِيّٗا
68. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በጌታህ እንምላለን ሰይጣናት ጋር በእርግጥ እንሰበስባቸዋለን:: ከዚያም በገሀነም ዙሪያ የተንበረከኩ ሆነው እናቀርባቸዋለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ثُمَّ لَنَنزِعَنَّ مِن كُلِّ شِيعَةٍ أَيُّهُمۡ أَشَدُّ عَلَى ٱلرَّحۡمَٰنِ عِتِيّٗا
69. ከዚያም ከየቡድኖቹ ሁሉ ከእነርሱ ያንን በአር-ረህማን ላይ በድፍረት በጣም ብርቱ የሆነውን መዘን እናወጣለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ثُمَّ لَنَحۡنُ أَعۡلَمُ بِٱلَّذِينَ هُمۡ أَوۡلَىٰ بِهَا صِلِيّٗا
70. ከዚያም እነዚያን በእርሷ ለመቃጠል ይበልጥ ተገቢ የሆኑትን ሰዎች እናውቃለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِن مِّنكُمۡ إِلَّا وَارِدُهَاۚ كَانَ عَلَىٰ رَبِّكَ حَتۡمٗا مَّقۡضِيّٗا
71. (ሰዎች ሆይ!) ከናንተ መካከል ወደ ገሀነም የማይወርድ አንድም የለም:: መውረዱም ጌታህ የፈረደው ግዴታና አይቀሬ ዉሳኔ ነው:: {1}
{1} ይህ ጀሀነም መውረድ ትርጉሙ ሙስሊሞች በርሷ ላይ በተዘረገው ሲራጥ በተባለ በጣም ቀጭን ድልድይ ላይ ያልፋሉ ማለት ነው፣ ሰው ያለ ጥፋት ገሀነም የማይገባ መሆኑ የተወቀ ነው [ተፍሲር ኢብኑጀሪር አጥጠበሪ]
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ثُمَّ نُنَجِّي ٱلَّذِينَ ٱتَّقَواْ وَّنَذَرُ ٱلظَّٰلِمِينَ فِيهَا جِثِيّٗا
72. ከዚያም እነዚያን አላህን የፈሩትን ብቻ እናድናለን:: አመጸኞችን ደግሞ የተንበረከኩ ሆነው በውስጧ እንተዋቸዋለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٖ قَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَيُّ ٱلۡفَرِيقَيۡنِ خَيۡرٞ مَّقَامٗا وَأَحۡسَنُ نَدِيّٗا
73. በእነርሱም ላይ አናቅጻችን ግልጽ ማስረጃዎች ሆነው በተነበቡላቸው ጊዜ እነዚያ የካዱት ለእነዚያ ላመኑት «ከሁለቱ ክፍሎች መኖሪያው የበለጠውና ሸንጎዉም ይበልጥ የሚያምረው ማንኛው ነው?» ይላሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَكَمۡ أَهۡلَكۡنَا قَبۡلَهُم مِّن قَرۡنٍ هُمۡ أَحۡسَنُ أَثَٰثٗا وَرِءۡيٗا
74. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ህዝቦች እነርሱ በእይታ በጣም ያማሩትን ብዙዎችን አጥፍተናል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلۡ مَن كَانَ فِي ٱلضَّلَٰلَةِ فَلۡيَمۡدُدۡ لَهُ ٱلرَّحۡمَٰنُ مَدًّاۚ حَتَّىٰٓ إِذَا رَأَوۡاْ مَا يُوعَدُونَ إِمَّا ٱلۡعَذَابَ وَإِمَّا ٱلسَّاعَةَ فَسَيَعۡلَمُونَ مَنۡ هُوَ شَرّٞ مَّكَانٗا وَأَضۡعَفُ جُندٗا
75. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «በስህተት ውስጥ የሆነውን አዛኙ አምላክ ለእርሱ ጥመትን ይጨምርለት (ማዘግየትን ያዘግየው::) የሚዛትባቸውንም ቅጣትን ወይም ሰዓቲቱን ባዩ ጊዜ እርሱ ስፍራው መጥፎና ሰራዊቱ ደካማ ማን እንደሆነ በእርግጥ ያውቃሉ።» በላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيَزِيدُ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ٱهۡتَدَوۡاْ هُدٗىۗ وَٱلۡبَٰقِيَٰتُ ٱلصَّٰلِحَٰتُ خَيۡرٌ عِندَ رَبِّكَ ثَوَابٗا وَخَيۡرٞ مَّرَدًّا
76. እነዚያንም የቀኑትን ሰዎች አላህ ቅንነትን ይጨምርላቸዋል:: መልካም ቀሪ ስራዎች በጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው:: በመመለሻነትም የተሻሉ ናቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: ម៉ារយុាំ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ