Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហាទីត   អាយ៉ាត់:
يَوۡمَ تَرَى ٱلۡمُؤۡمِنِينَ وَٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ يَسۡعَىٰ نُورُهُم بَيۡنَ أَيۡدِيهِمۡ وَبِأَيۡمَٰنِهِمۖ بُشۡرَىٰكُمُ ٱلۡيَوۡمَ جَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَاۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ
12. ወንድ ትክክለኛ አማኞችንና ሴት ትክክለኛ አማኞችን በስተፊቶቻቸው በቀኞቻቸዉም ብርሀናቸው የሚሮጥ ሲሆን በምታያቸው ቀን (ታላቅ ምንዳ አለላቸው።) "ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትኾኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ናቸው (ይባላሉ)፡፡ ይህ እርሱ ታላቅ እድል ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَوۡمَ يَقُولُ ٱلۡمُنَٰفِقُونَ وَٱلۡمُنَٰفِقَٰتُ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ ٱنظُرُونَا نَقۡتَبِسۡ مِن نُّورِكُمۡ قِيلَ ٱرۡجِعُواْ وَرَآءَكُمۡ فَٱلۡتَمِسُواْ نُورٗاۖ فَضُرِبَ بَيۡنَهُم بِسُورٖ لَّهُۥ بَابُۢ بَاطِنُهُۥ فِيهِ ٱلرَّحۡمَةُ وَظَٰهِرُهُۥ مِن قِبَلِهِ ٱلۡعَذَابُ
13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የወንድ አስመሳዮችና የሴት አስመሳዮች ለእነዚያ በአላህ ላመኑት "ጠብቁን ከብርሀናችሁ እናበራለንና" የሚሉበትን ቀን አስታውስ:: "ወደ ኋላችሁ ተመለሱ:: ብርሀንንም እዚያው ፈልጉ" ይባላሉ:: በመካከላቸዉም ለእርሱ ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል:: ግቢው በውስጡ ገነት ያለበት ከውጪዉም በኩሉ ደግሞ የእሳት (ስቃይ) ያለበት የሆነ (ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል)።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يُنَادُونَهُمۡ أَلَمۡ نَكُن مَّعَكُمۡۖ قَالُواْ بَلَىٰ وَلَٰكِنَّكُمۡ فَتَنتُمۡ أَنفُسَكُمۡ وَتَرَبَّصۡتُمۡ وَٱرۡتَبۡتُمۡ وَغَرَّتۡكُمُ ٱلۡأَمَانِيُّ حَتَّىٰ جَآءَ أَمۡرُ ٱللَّهِ وَغَرَّكُم بِٱللَّهِ ٱلۡغَرُورُ
14. "ከናንተ ጋር አልነበርንምን?" በማለት ይጠሯቸዋል:: "እውነት ነው እኛ ጋር ነበራችሁ:: ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ:: በነብዩ አደጋዎችን ተጠባበቃችሁ ትጠራጠራላችሁም:: የአላህ ትዕዛዝ እስከ መጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ። አታላዩም ሰይጣን በአላህ መታገስ ሸነገላችሁ ይሏቸዋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَٱلۡيَوۡمَ لَا يُؤۡخَذُ مِنكُمۡ فِدۡيَةٞ وَلَا مِنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْۚ مَأۡوَىٰكُمُ ٱلنَّارُۖ هِيَ مَوۡلَىٰكُمۡۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِيرُ
15. በመሆኑም ዛሬ ከናንተም ሆነ በአላህ ከካዱት ሰዎች የገንዘብ ክፍያ (ቤዛ) አይወሰድም:: መኖሪያችሁ የገሀነም እሳት ብቻ ናት:: እርሷ ተገቢያችሁ ናትና:: የገሀነም እሳት መመለሻነቷ ምን ትከፋም" (ይሏቸዋል)::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ أَلَمۡ يَأۡنِ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓاْ أَن تَخۡشَعَ قُلُوبُهُمۡ لِذِكۡرِ ٱللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ ٱلۡحَقِّ وَلَا يَكُونُواْ كَٱلَّذِينَ أُوتُواْ ٱلۡكِتَٰبَ مِن قَبۡلُ فَطَالَ عَلَيۡهِمُ ٱلۡأَمَدُ فَقَسَتۡ قُلُوبُهُمۡۖ وَكَثِيرٞ مِّنۡهُمۡ فَٰسِقُونَ
16. ለእነዚያ (በአላህ) ላመኑት ለአላህ ተግሳጽና ከቁርኣንም ለወረደው እውነታ ልቦቻቸው ሊፈሩ፤ እንደነዚያ በፊት መጽሐፍን እንደ ተሰጡትና በእነርሱ ላይ ጊዜ ስለ ረዘመባቸው ልቦቻቸውም እንደ ደረቁባቸው ህዝቦች የማይሆኑበት ጊዜ አልቀረበምን? ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱعۡلَمُوٓاْ أَنَّ ٱللَّهَ يُحۡيِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَاۚ قَدۡ بَيَّنَّا لَكُمُ ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّكُمۡ تَعۡقِلُونَ
17. (ሰዎች ሆይ!) አላህ ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው የሚደርጋት መሆኑን እወቁ። ታውቁም ዘንድ አናቅጽን ለእናንተ በእርግጥ አብራራንላችሁ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلۡمُصَّدِّقِينَ وَٱلۡمُصَّدِّقَٰتِ وَأَقۡرَضُواْ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنٗا يُضَٰعَفُ لَهُمۡ وَلَهُمۡ أَجۡرٞ كَرِيمٞ
18. የመጸወቱ ወንዶችና የመጸወቱ ሴቶች ለአላህ መልካምን ብድር ያበደሩ ሁሉ ለእነርሱም ምንዳ ይደራረብላቸዋል:: ለእነርሱም መልካም የተከበረ ምንዳ አለላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហាទីត
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ