Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហាទីត   អាយ៉ាត់:
هُوَ ٱلَّذِي خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٖ ثُمَّ ٱسۡتَوَىٰ عَلَى ٱلۡعَرۡشِۖ يَعۡلَمُ مَا يَلِجُ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَمَا يَخۡرُجُ مِنۡهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا يَعۡرُجُ فِيهَاۖ وَهُوَ مَعَكُمۡ أَيۡنَ مَا كُنتُمۡۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٞ
4. እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ብቻ የፈጠረ ነው:: ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ አለ። ወደ ምድር የሚገባውንና ከእርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: ከሰማይ የሚወረደውንና ወደ እርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: እርሱ የትም ብትሆኑ (በእውቀቱ) ከናንተው ጋር ነው:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لَّهُۥ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرۡجَعُ ٱلۡأُمُورُ
5. የሰማያትና የምድር ንግስና የእርሱ ብቻ ነው:: ነገሮች ሁሉ ወደ አላህ ይመለሳሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يُولِجُ ٱلَّيۡلَ فِي ٱلنَّهَارِ وَيُولِجُ ٱلنَّهَارَ فِي ٱلَّيۡلِۚ وَهُوَ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
6. ሌሊትን በቀን ውስጥ ያስገባል:: ቀንንም በሌሊት ውስጥ ያስገባል:: እርሱም በልቦች ውስጥ የተደበቁትን ሁሉ አዋቂ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ءَامِنُواْ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَأَنفِقُواْ مِمَّا جَعَلَكُم مُّسۡتَخۡلَفِينَ فِيهِۖ فَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡ وَأَنفَقُواْ لَهُمۡ أَجۡرٞ كَبِيرٞ
7. (ሰዎች ሆይ!) በአላህና በመልዕክተኛው እመኑ:: አላህ በእርሱ ላይ ተተካኪዎች ካደረጋችሁ ገንዘብ ዉስጥም ለግሱ:: እነዚያ ከእናንተ መካከል በአላህ ያመኑትና የለገሱት ሁሉ ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ አለላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَا لَكُمۡ لَا تُؤۡمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلرَّسُولُ يَدۡعُوكُمۡ لِتُؤۡمِنُواْ بِرَبِّكُمۡ وَقَدۡ أَخَذَ مِيثَٰقَكُمۡ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ
8. (ሰዎች ሆይ!) ጌታችሁም ቃልኪዳናችሁን የያዘባችሁ ሲሆን መልዕክተኛውም በጌታችሁ እንድታምኑ የሚጠራችሁ ሲሆን በአላህ የማታምኑበት ምን ምክኒያት አላችሁ? እናንተ በትክክል የምታምኑ ከሆናችሁ?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هُوَ ٱلَّذِي يُنَزِّلُ عَلَىٰ عَبۡدِهِۦٓ ءَايَٰتِۭ بَيِّنَٰتٖ لِّيُخۡرِجَكُم مِّنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِۚ وَإِنَّ ٱللَّهَ بِكُمۡ لَرَءُوفٞ رَّحِيمٞ
9. እርሱ ከጨለማዎች ወደ ብርሀን ሊያወጣችሁ ግልፆች የሆኑን አናቅጽ በባሪያው ላይ የሚያወርድ ነው:: አላህ ለእናንተ በእርግጥ ሩህሩህ አዛኝ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَا لَكُمۡ أَلَّا تُنفِقُواْ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَلِلَّهِ مِيرَٰثُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ لَا يَسۡتَوِي مِنكُم مَّنۡ أَنفَقَ مِن قَبۡلِ ٱلۡفَتۡحِ وَقَٰتَلَۚ أُوْلَٰٓئِكَ أَعۡظَمُ دَرَجَةٗ مِّنَ ٱلَّذِينَ أَنفَقُواْ مِنۢ بَعۡدُ وَقَٰتَلُواْۚ وَكُلّٗا وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلۡحُسۡنَىٰۚ وَٱللَّهُ بِمَا تَعۡمَلُونَ خَبِيرٞ
10. የሰማያትና የምድር ውርስ ለአላህ ብቻ ሲሆን በአላህ መንገድ የማትለግሱበት ምን ምክንያት አላችሁ? ከናንተ መካከል ከመካ መከፈት በፊት የለገሰና የተጋደለ ሰው ከተከፈተ በኋላ ከለገሰና ከተጋደለ ሰው ጋር አይስተከከልም:: ከእነዚያ በኋላ ከለገሱትና ከተጋደሉት እነዚህ በደረጃ በጣም የላቁ ናቸውና:: ሁሉንም አላህ የመልካሚቱን ተስፋ ቃል ገብቶላቸዋል:: አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مَّن ذَا ٱلَّذِي يُقۡرِضُ ٱللَّهَ قَرۡضًا حَسَنٗا فَيُضَٰعِفَهُۥ لَهُۥ وَلَهُۥٓ أَجۡرٞ كَرِيمٞ
11. ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ አላህ ምንዳውን የሚያነባብርለት ሰው ማን ነው? ለእርሱም መልካም ምንዳ አለው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហាទីត
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ