Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ជាស៊ីយ៉ះ   អាយ៉ាត់:
أَفَرَءَيۡتَ مَنِ ٱتَّخَذَ إِلَٰهَهُۥ هَوَىٰهُ وَأَضَلَّهُ ٱللَّهُ عَلَىٰ عِلۡمٖ وَخَتَمَ عَلَىٰ سَمۡعِهِۦ وَقَلۡبِهِۦ وَجَعَلَ عَلَىٰ بَصَرِهِۦ غِشَٰوَةٗ فَمَن يَهۡدِيهِ مِنۢ بَعۡدِ ٱللَّهِۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ዝንባሌውን አምላኩ ያደረገውን አላህም ከእውቀት ጋር ያጠመመውን በጆሮውና በልቡም ላይ ያተመበትን በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን? ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሰጹምን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالُواْ مَا هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنۡيَا نَمُوتُ وَنَحۡيَا وَمَا يُهۡلِكُنَآ إِلَّا ٱلدَّهۡرُۚ وَمَا لَهُم بِذَٰلِكَ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِنۡ هُمۡ إِلَّا يَظُنُّونَ
24. (ከሓዲያን) «እርሷም(ሕይወት) የቅርቢቱ ሕይወታችን ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም:: እንሞታለን:: ህያዉም እንሆናለን:: ከጊዜም (ማለፍ) በሰተቀር ሌላ አያጠፋንም» አሉ:: ለእነርሱም በዚህ በሚሉት ምንም እውቀት የላቸዉም:: እነርሱ የሚጠራጠሩ እንጂ ሌላ አይደሉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَا تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِمۡ ءَايَٰتُنَا بَيِّنَٰتٖ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمۡ إِلَّآ أَن قَالُواْ ٱئۡتُواْ بِـَٔابَآئِنَآ إِن كُنتُمۡ صَٰدِقِينَ
25. አናቅጻችንም ግልፆች ሆነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ የክርክራቸው ማስረጃ «እውነተኞች እንደሆናችሁ እስቲ የቀድሞ አባቶቻችንን አምጡ» ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قُلِ ٱللَّهُ يُحۡيِيكُمۡ ثُمَّ يُمِيتُكُمۡ ثُمَّ يَجۡمَعُكُمۡ إِلَىٰ يَوۡمِ ٱلۡقِيَٰمَةِ لَا رَيۡبَ فِيهِ وَلَٰكِنَّ أَكۡثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعۡلَمُونَ
26. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ ህያው ያደርጋችኋል ከዚያም ያሞታችኋልም:: ከዚያም በትንሳኤ ቀን ይሰበስባችኋል:: ይህም ጥርጥር የለበትም:: ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።» በላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَيَوۡمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يَوۡمَئِذٖ يَخۡسَرُ ٱلۡمُبۡطِلُونَ
27. የሰማያትና የምድር ግዛት የአላህ ብቻ ነው:: ሰዓቲቱም በምትከሰትበት ቀን ያን ጊዜ አጥፊዎች ሁሉ ይከስራሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَتَرَىٰ كُلَّ أُمَّةٖ جَاثِيَةٗۚ كُلُّ أُمَّةٖ تُدۡعَىٰٓ إِلَىٰ كِتَٰبِهَا ٱلۡيَوۡمَ تُجۡزَوۡنَ مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
28. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ህዝቦችን ሁሉ ተንበርካኪ ሆነው ታያቸዋለህ:: ህዝብም ሁሉ ወደ ግል መጽሐፋቸው ይጠራሉ:: ይባላሉም: «ዛሬ ቀደም ሲል ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ትመነዳላችሁ
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هَٰذَا كِتَٰبُنَا يَنطِقُ عَلَيۡكُم بِٱلۡحَقِّۚ إِنَّا كُنَّا نَسۡتَنسِخُ مَا كُنتُمۡ تَعۡمَلُونَ
29. «ይህ መጽሐፋችን ነው:: በእናንተ ላይ በእውነት ይናገራል:: እኛ ያንን ትሰሩት የነበራችሁትን ሁሉ እናስገለብጥ ነበርንና» (ይባላሉ)::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ فَيُدۡخِلُهُمۡ رَبُّهُمۡ فِي رَحۡمَتِهِۦۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡمُبِينُ
30. እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩትማ ጌታቸው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባቸዋል:: ይህ እርሱ ግልጽ የሆነ እድልን ማግኘት ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَفَلَمۡ تَكُنۡ ءَايَٰتِي تُتۡلَىٰ عَلَيۡكُمۡ فَٱسۡتَكۡبَرۡتُمۡ وَكُنتُمۡ قَوۡمٗا مُّجۡرِمِينَ
31. እነዚያም የካዱትማ ለእነርሱ ይባላሉ: «አናቅጾቼ በእናንተ ላይ ይነበቡ አልነበሩምን? ኮራችሁም :: ከሓዲያን ህዝቦችም ነበራችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَا قِيلَ إِنَّ وَعۡدَ ٱللَّهِ حَقّٞ وَٱلسَّاعَةُ لَا رَيۡبَ فِيهَا قُلۡتُم مَّا نَدۡرِي مَا ٱلسَّاعَةُ إِن نَّظُنُّ إِلَّا ظَنّٗا وَمَا نَحۡنُ بِمُسۡتَيۡقِنِينَ
32. «የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው:: በእርሷ መምጣት (ጥርጥር) የለም:: በተባለ ጊዜም 'ሰዓቲቱ ምን እንደሆነች አናውቅም መጠራጠርን የምንጠራጠር እንጂ ሌላ አይደለንም:: እኛም አረጋጋጮች አይደለንም' አላችሁ::» (ይባላሉ)
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ជាស៊ីយ៉ះ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ