Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ជាស៊ីយ៉ះ   អាយ៉ាត់:

አል ጃሲያህ

حمٓ
1. ሓ፤ሚይም፤
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
تَنزِيلُ ٱلۡكِتَٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلۡعَزِيزِ ٱلۡحَكِيمِ
2. የመጽሐፉ መወረድ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ከሆነው ከአላህ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ لَأٓيَٰتٖ لِّلۡمُؤۡمِنِينَ
3. በሰማያትና በምድር ውስጥ ለአማኞች ሁሉ እርግጠኛ ምልክቶች አሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَفِي خَلۡقِكُمۡ وَمَا يَبُثُّ مِن دَآبَّةٍ ءَايَٰتٞ لِّقَوۡمٖ يُوقِنُونَ
4. (ሰዎች ሆይ!) እናንተን በመፍጠር እና ከተንቀሳቃሽ ነገሮች በምድር ላይ የሚበተነውን ሁሉ በመፍጠሩ ለሚያረጋግጡ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተአምራት አሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱخۡتِلَٰفِ ٱلَّيۡلِ وَٱلنَّهَارِ وَمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مِن رِّزۡقٖ فَأَحۡيَا بِهِ ٱلۡأَرۡضَ بَعۡدَ مَوۡتِهَا وَتَصۡرِيفِ ٱلرِّيَٰحِ ءَايَٰتٞ لِّقَوۡمٖ يَعۡقِلُونَ
5. በሌሊትና በቀን መተካካትም፤ አላህ ከሰማይ ባወረደው ሲሳይ (ዝናብ) በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ህያው በማድረጉ፤ ንፋሶችንም (በየ አቅጣጫው) በማዘዋወሩ ለሚያውቁ ህዝቦች ሁሉ በቂ ማስረጃዎች አሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
تِلۡكَ ءَايَٰتُ ٱللَّهِ نَتۡلُوهَا عَلَيۡكَ بِٱلۡحَقِّۖ فَبِأَيِّ حَدِيثِۭ بَعۡدَ ٱللَّهِ وَءَايَٰتِهِۦ يُؤۡمِنُونَ
6. እነዚህ ባንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው የሆኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው:: ከአላህና ከማስረጃዎቹ በኋላ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَيۡلٞ لِّكُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٖ
7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ውሸታም፤ ኃጢአተኛ ለሆነ ሁሉ ወዮለት (ጥፋት ተገባው)።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَسۡمَعُ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ تُتۡلَىٰ عَلَيۡهِ ثُمَّ يُصِرُّ مُسۡتَكۡبِرٗا كَأَن لَّمۡ يَسۡمَعۡهَاۖ فَبَشِّرۡهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٖ
8. የአላህን አናቅጽ በእርሱ ላይ የሚነበቡለት ሲሆኑ ይሰማል:: ከዚያም የኮራ ሲሆን እንዳልሰማ ሆኖ በክህደቱ ላይ ይዘወትራል:: እናም እርሱን በአሳማሚ ቅጣት አብስረው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَا عَلِمَ مِنۡ ءَايَٰتِنَا شَيۡـًٔا ٱتَّخَذَهَا هُزُوًاۚ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عَذَابٞ مُّهِينٞ
9. ከአናቅጻችንም አንዲትን ነገር ባወቀ ጊዜ መሳለቂያ ያደርጋታል:: እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አለባቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مِّن وَرَآئِهِمۡ جَهَنَّمُۖ وَلَا يُغۡنِي عَنۡهُم مَّا كَسَبُواْ شَيۡـٔٗا وَلَا مَا ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوۡلِيَآءَۖ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٌ
10. ከፊታቸዉም ገሀነም አለች:: የሰበሰቡት ሀብትም ከእነርሱ ላይ ምንንም አይመልስላቸዉም:: ከአላህ ሌላም ረዳቶች ያደረጓቸው ሁሉ ምንንም አይጠቅሟቸዉም:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
هَٰذَا هُدٗىۖ وَٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِـَٔايَٰتِ رَبِّهِمۡ لَهُمۡ عَذَابٞ مِّن رِّجۡزٍ أَلِيمٌ
11. ይህ ቁርኣን መሪ ነው:: እነዚያም በጌታቸው አናቅጽ የካዱት ሁሉ ለእነርሱ ከብርቱ ቅጣት ድርሻቸው አለባቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
۞ ٱللَّهُ ٱلَّذِي سَخَّرَ لَكُمُ ٱلۡبَحۡرَ لِتَجۡرِيَ ٱلۡفُلۡكُ فِيهِ بِأَمۡرِهِۦ وَلِتَبۡتَغُواْ مِن فَضۡلِهِۦ وَلَعَلَّكُمۡ تَشۡكُرُونَ
12. አላህ ያ ባህርን በውስጡ ታንኳዎች በፈቃዱ እንዲንሻለሉበት ከችሮታዉም እንድትፈልጉበት እንድታመሰግኑትም ለእናንተ የገራላችሁ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ جَمِيعٗا مِّنۡهُۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَأٓيَٰتٖ لِّقَوۡمٖ يَتَفَكَّرُونَ
13. ለእናንተ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ በመላ ከእርሱ ሲሆን ያገራላችሁ ነው። በዚህ ለሚያስተነትኑ ህዝቦች ሁሉ አያሌ ተዐምራት አሉበት።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ហ្ជាស៊ីយ៉ះ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ