Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាហ្សហ្សុខរ៉ហ្វ   អាយ៉ាត់:
وَلِبُيُوتِهِمۡ أَبۡوَٰبٗا وَسُرُرًا عَلَيۡهَا يَتَّكِـُٔونَ
34. ለቤቶቻቸው የብር በሮች፤ ለሚደገፉባቸዉም የብር አልጋዎች፤(ባደረግንላቸው ነበር)።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَزُخۡرُفٗاۚ وَإِن كُلُّ ذَٰلِكَ لَمَّا مَتَٰعُ ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَاۚ وَٱلۡأٓخِرَةُ عِندَ رَبِّكَ لِلۡمُتَّقِينَ
35. የወርቅ ጌጥንም ባደረግንላቸው ነበር። ይህም ሁሉ የቅርቢቱ ሕይወት መጣቀሚያ እንጂ ሌላ አይደለም:: ጠፊ ነው:: መጨረሻይቱም አገር በጌታህ ዘንድ ለጥንቁቆች ብቻ ናት::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَن يَعۡشُ عَن ذِكۡرِ ٱلرَّحۡمَٰنِ نُقَيِّضۡ لَهُۥ شَيۡطَٰنٗا فَهُوَ لَهُۥ قَرِينٞ
36. (በቁርኣን ከተወሳው) ከአል-ረሕማን ግሳጼ የሚደናበርም ሰው ለእርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን። ስለዚህ እርሱ ለእርሱ የሁልግዜ ቁራኛው ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِنَّهُمۡ لَيَصُدُّونَهُمۡ عَنِ ٱلسَّبِيلِ وَيَحۡسَبُونَ أَنَّهُم مُّهۡتَدُونَ
37. እነርሱም (ተደናባሪዎቹ) ሁሉ ወደ ትክክለኛው መንገድ ተመሪዎች መሆናቸውን የሚያስቡ ሲሆኑ እነርሱ (ሰይጣናት) ከቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ያግዷቸዋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَنَا قَالَ يَٰلَيۡتَ بَيۡنِي وَبَيۡنَكَ بُعۡدَ ٱلۡمَشۡرِقَيۡنِ فَبِئۡسَ ٱلۡقَرِينُ
38. (በትንሳኤ) ወደ እኛ በመጣ ጊዜ «(ቁራኛዬ ሆይ) በእኔና ባንተ መካከል የምስራቅና የምዕራብ ርቀት በኖረ ዋ ምኞቴ! ምን የከፋ ቁራኛ ነህ።» ይላል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَن يَنفَعَكُمُ ٱلۡيَوۡمَ إِذ ظَّلَمۡتُمۡ أَنَّكُمۡ فِي ٱلۡعَذَابِ مُشۡتَرِكُونَ
39. (ከሓዲያን ሆይ!) ስለ በደላችሁም ዛሬ እናንተ በቅጣት ተጋሪዎች መሆናችሁ አይጠቅማችሁም (ይባላሉ)።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَفَأَنتَ تُسۡمِعُ ٱلصُّمَّ أَوۡ تَهۡدِي ٱلۡعُمۡيَ وَمَن كَانَ فِي ضَلَٰلٖ مُّبِينٖ
40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተ ደንቆሮዎችን ታሰማለህን? ወይስ እውሮችንና በግልጽ ጥመት ውስጥ የሆኑ ሰዎችን ትመራለህን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَإِمَّا نَذۡهَبَنَّ بِكَ فَإِنَّا مِنۡهُم مُّنتَقِمُونَ
41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አንተም ቅጣታቸውን ሳታይ ብንወስድህ እኛ ከእነርሱ ተበቃዮች ነን።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَوۡ نُرِيَنَّكَ ٱلَّذِي وَعَدۡنَٰهُمۡ فَإِنَّا عَلَيۡهِم مُّقۡتَدِرُونَ
42. ወይም ያንን የቀጠርናቸውን ብናሳይህ እኛ በእነርሱ ቅጣት ላይ ቻይዎች ነን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَٱسۡتَمۡسِكۡ بِٱلَّذِيٓ أُوحِيَ إِلَيۡكَۖ إِنَّكَ عَلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ያንንም ወደ አንተ የተወረደልህን አጥብቀህ ያዝ:: አንተ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ነህና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِنَّهُۥ لَذِكۡرٞ لَّكَ وَلِقَوۡمِكَۖ وَسَوۡفَ تُسۡـَٔلُونَ
44. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እርሱ (ቁርኣን) ላንተም ሆነ ለህዝቦችህ ታላቅ ክብር ነው:: ወደፊተም ከርሱ በእርግጥ ትጠየቃላችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَسۡـَٔلۡ مَنۡ أَرۡسَلۡنَا مِن قَبۡلِكَ مِن رُّسُلِنَآ أَجَعَلۡنَا مِن دُونِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ءَالِهَةٗ يُعۡبَدُونَ
45. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከመልዕክተኞችም ካንተ በፊት የላክናቸው ከአር-ረሕማን ሌላ የሚገዙዋቸው የሆነን አማልክት አድርገን እንደሆነ (ተከታዮቻቸውን) ጠይቃቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ أَرۡسَلۡنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَٰتِنَآ إِلَىٰ فِرۡعَوۡنَ وَمَلَإِيْهِۦ فَقَالَ إِنِّي رَسُولُ رَبِّ ٱلۡعَٰلَمِينَ
46. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳንም በተዓምራታችን ወደ ፈርዖንና ወደ ሹማምንቶቹ በእርግጥ ላክን:: «እኔ የዓለማቱ ጌታ መልዕክተኛ ነኝ» አላቸዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَلَمَّا جَآءَهُم بِـَٔايَٰتِنَآ إِذَا هُم مِّنۡهَا يَضۡحَكُونَ
47. በተዓምራታችን በመጣላቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ በእርሷ ይስቃሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាហ្សហ្សុខរ៉ហ្វ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ