Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាហ្សហ្សុខរ៉ហ្វ   អាយ៉ាត់:
وَٱلَّذِي نَزَّلَ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءَۢ بِقَدَرٖ فَأَنشَرۡنَا بِهِۦ بَلۡدَةٗ مَّيۡتٗاۚ كَذَٰلِكَ تُخۡرَجُونَ
11. ያም ከሰማይ ውሃን በልክ ያወረደላችሁ ነው። በእርሱም (በውሀው) የሞተችውን አገር ህያው አደረግን:: (ሰዎች ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ከየመቃብሮቻችሁ ትወጣለችሁ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱلَّذِي خَلَقَ ٱلۡأَزۡوَٰجَ كُلَّهَا وَجَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلۡفُلۡكِ وَٱلۡأَنۡعَٰمِ مَا تَرۡكَبُونَ
12. ያም የፍጡር ዓይነቶችን ሁሉ (ጥንድ) አድርጎ የፈጠረ ለእናንተም ከመርከቦችና ከቤት እንሰሳዎች መካከል የምትጋልቧቸውን ያደረገላችሁ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لِتَسۡتَوُۥاْ عَلَىٰ ظُهُورِهِۦ ثُمَّ تَذۡكُرُواْ نِعۡمَةَ رَبِّكُمۡ إِذَا ٱسۡتَوَيۡتُمۡ عَلَيۡهِ وَتَقُولُواْ سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِي سَخَّرَ لَنَا هَٰذَا وَمَا كُنَّا لَهُۥ مُقۡرِنِينَ
13. በጀርባዎቻቸው ላይ እንድትደላደሉ ከዚያም በእርሱ ላይ በተደላደላችሁ ጊዜ የጌታችሁን ጸጋ እንድታስታውሱ፤ እንድትሉም «ይህንን የማንችለው ስንሆን ለእኛ ያገራልን ጌታ ጥራት ተገባው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا لَمُنقَلِبُونَ
14. እኛም በእርግጥ ወደ ጌታችን አላህ ተመላሾች ነን» እንድትሉ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَجَعَلُواْ لَهُۥ مِنۡ عِبَادِهِۦ جُزۡءًاۚ إِنَّ ٱلۡإِنسَٰنَ لَكَفُورٞ مُّبِينٌ
15. ከባሮቹም መካከል ለእርሱ ክፋይን (የተወሰነን) ብቻ አደረጉለት:: ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَمِ ٱتَّخَذَ مِمَّا يَخۡلُقُ بَنَاتٖ وَأَصۡفَىٰكُم بِٱلۡبَنِينَ
16. አላህ ከሚፈጥረው ፍጡር መካከል ሴቶች ልጆችን ብቻ ለይቶ የራሱ ልጅ አድርጎ ያዘን? (ከዚያም) እናንተን በወንዶች ልጆች መረጣችሁን? (አይደለም)።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذَا بُشِّرَ أَحَدُهُم بِمَا ضَرَبَ لِلرَّحۡمَٰنِ مَثَلٗا ظَلَّ وَجۡهُهُۥ مُسۡوَدّٗا وَهُوَ كَظِيمٌ
17. አንዳቸዉም ለአር-ረህማን ምሳሌ ባደረገው ነገር (በሴት ልጅ) በተበሰረ ጊዜ በቁጭት የተሞላ ሆኖ ፊቱ ጥቁር ይሆናል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَوَمَن يُنَشَّؤُاْ فِي ٱلۡحِلۡيَةِ وَهُوَ فِي ٱلۡخِصَامِ غَيۡرُ مُبِينٖ
18. በጌጣጌጥ ተከልሶ እንዲያድግ የሚደረገውን ክፍል እርሱም ከደካማነቱ የተነሳ በክርክር የማያብራራውን ፍጡር ለይተው ለአላህ ያደርጋሉን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَجَعَلُواْ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ ٱلَّذِينَ هُمۡ عِبَٰدُ ٱلرَّحۡمَٰنِ إِنَٰثًاۚ أَشَهِدُواْ خَلۡقَهُمۡۚ سَتُكۡتَبُ شَهَٰدَتُهُمۡ وَيُسۡـَٔلُونَ
19. እነዚያን የአር-ረሕማን ቅን ባሮች የሆኑትን መላእክትንም ሴቶች አደረጓቸው። ለመሆኑ እነርሱ መላእክት ሲፈጠሩ አብረው ነበሩን? መመስከራቸው በእርግጥ ትፃፋለች:: ስለ እርሷም ይጠየቃሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالُواْ لَوۡ شَآءَ ٱلرَّحۡمَٰنُ مَا عَبَدۡنَٰهُمۗ مَّا لَهُم بِذَٰلِكَ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِنۡ هُمۡ إِلَّا يَخۡرُصُونَ
20. «አር-ረሕማንም በፈለገ ኖሮ ባልተገዛናቸው ነበር» አሉ። ለእነርሱም በዚህ ምንም እውቀት የላቸዉም፤ እነርሱ የሚዋሹ ህዝቦች እንጂ ሌላ አይደሉም።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَمۡ ءَاتَيۡنَٰهُمۡ كِتَٰبٗا مِّن قَبۡلِهِۦ فَهُم بِهِۦ مُسۡتَمۡسِكُونَ
21. ከእርሱ (ቁርኣን) በፊት መጽሐፍን ሰጠናቸውና እሱን አጥብቀው የያዙ ናቸውን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
بَلۡ قَالُوٓاْ إِنَّا وَجَدۡنَآ ءَابَآءَنَا عَلَىٰٓ أُمَّةٖ وَإِنَّا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم مُّهۡتَدُونَ
22. ከቶውንም «እኛ አባቶቻችንን (በዚሁ) ሃይማኖት ላይ አገኘናቸው:: እኛም በፈለጎቻቸው ላይ ተመሪዎች ነን» አሉ እንጂ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាហ្សហ្សុខរ៉ហ្វ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ