Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អ៊ីព្រហ៊ីម   អាយ៉ាត់:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضَ بِٱلۡحَقِّۚ إِن يَشَأۡ يُذۡهِبۡكُمۡ وَيَأۡتِ بِخَلۡقٖ جَدِيدٖ
19. (የሰው ልጅ ሆይ!) አላህ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ መሆኑን አታይምን? ቢሻ ያጠፋችኋል:: አዲስ ፍጡርንም ያመጣል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَا ذَٰلِكَ عَلَى ٱللَّهِ بِعَزِيزٖ
20. ይህም እናንተን አጥፍቶ አዲስ ፍጥረትን ማምጣት በአላህ ላይ አስቸጋሪ ጉዳይ አይደለም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَبَرَزُواْ لِلَّهِ جَمِيعٗا فَقَالَ ٱلضُّعَفَٰٓؤُاْ لِلَّذِينَ ٱسۡتَكۡبَرُوٓاْ إِنَّا كُنَّا لَكُمۡ تَبَعٗا فَهَلۡ أَنتُم مُّغۡنُونَ عَنَّا مِنۡ عَذَابِ ٱللَّهِ مِن شَيۡءٖۚ قَالُواْ لَوۡ هَدَىٰنَا ٱللَّهُ لَهَدَيۡنَٰكُمۡۖ سَوَآءٌ عَلَيۡنَآ أَجَزِعۡنَآ أَمۡ صَبَرۡنَا مَا لَنَا مِن مَّحِيصٖ
21. የተሰበሰቡ ሆነው ለአላህ ይገለጻሉ። ሐሳበ ደካማዎቹም ተከታዮች ለእነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርን እናንተ ከአላህ ቅጣት ከእኛ ላይ አንዳችን ነገር ተከላካዮች ናችሁን?» ይሏቸዋል። አስከታዮቹም። «አላህ ባቀናን ኖሮ በመራናችሁ ነበር።» ይሏቸዋል:: «ብንበሳጭ ወይም ብንታገሥም በእኛ ላይ ሁሉም እኩል ነው:: ለእኛ ምንም መጠጊያ የለንም።» ይላሉ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالَ ٱلشَّيۡطَٰنُ لَمَّا قُضِيَ ٱلۡأَمۡرُ إِنَّ ٱللَّهَ وَعَدَكُمۡ وَعۡدَ ٱلۡحَقِّ وَوَعَدتُّكُمۡ فَأَخۡلَفۡتُكُمۡۖ وَمَا كَانَ لِيَ عَلَيۡكُم مِّن سُلۡطَٰنٍ إِلَّآ أَن دَعَوۡتُكُمۡ فَٱسۡتَجَبۡتُمۡ لِيۖ فَلَا تَلُومُونِي وَلُومُوٓاْ أَنفُسَكُمۖ مَّآ أَنَا۠ بِمُصۡرِخِكُمۡ وَمَآ أَنتُم بِمُصۡرِخِيَّ إِنِّي كَفَرۡتُ بِمَآ أَشۡرَكۡتُمُونِ مِن قَبۡلُۗ إِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
22. ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ ሰይጣን ይላቸዋል: «አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ እኔም ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ:: አፈረስኩባችሁም:: ለእኔም በእናንተ ላይ ምንም ሥልጣን አልነበረኝም:: ግና ጠራኋችሁና ታዘዛችሁኝ:: ስለዚህ አትውቀሱኝ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ:: እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም። እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ሁሉ ካድኩ በዳዮቹ ሁሉ አሳማሚ ቅጣት አለባቸው።»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأُدۡخِلَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَعَمِلُواْ ٱلصَّٰلِحَٰتِ جَنَّٰتٖ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا بِإِذۡنِ رَبِّهِمۡۖ تَحِيَّتُهُمۡ فِيهَا سَلَٰمٌ
23. እነዚያ በትክክል ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ በጌታቸው ፈቃድ እንዲገቡ ይደረጋሉ:: በውስጣቸው መከባበሪያቸው ሰላምታቸው «ሰላም ለእናንተ ይሁን መባባል» ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَمۡ تَرَ كَيۡفَ ضَرَبَ ٱللَّهُ مَثَلٗا كَلِمَةٗ طَيِّبَةٗ كَشَجَرَةٖ طَيِّبَةٍ أَصۡلُهَا ثَابِتٞ وَفَرۡعُهَا فِي ٱلسَّمَآءِ
24. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ መልካምን ቃል ሥሯ በምድር ውስጥ የተደላደለች ቅርንጫፏም ወደ ሰማይ የረዘመች እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየህምን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អ៊ីព្រហ៊ីម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ