Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អ៊ីព្រហ៊ីម   អាយ៉ាត់:
قَالَتۡ لَهُمۡ رُسُلُهُمۡ إِن نَّحۡنُ إِلَّا بَشَرٞ مِّثۡلُكُمۡ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يَمُنُّ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنۡ عِبَادِهِۦۖ وَمَا كَانَ لَنَآ أَن نَّأۡتِيَكُم بِسُلۡطَٰنٍ إِلَّا بِإِذۡنِ ٱللَّهِۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُؤۡمِنُونَ
11. መልዕክተኞቻቸውም ለእነርሱ አሉ: «እኛ ብጤያችሁ ሰዎች እንጂ ሌላ አይደለንም:: ግን አላህ ከባሮቹ መካከል በሚሻው ሰው ላይ ይለግሳል:: እኛም በአላህ ፈቃድ እንጂ ማስረጃን ልናመጣላችሁ አይገባንም:: በአላህ ላይ ብቻ ምእመናን ይጠጉ (ይመኩ)።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَا لَنَآ أَلَّا نَتَوَكَّلَ عَلَى ٱللَّهِ وَقَدۡ هَدَىٰنَا سُبُلَنَاۚ وَلَنَصۡبِرَنَّ عَلَىٰ مَآ ءَاذَيۡتُمُونَاۚ وَعَلَى ٱللَّهِ فَلۡيَتَوَكَّلِ ٱلۡمُتَوَكِّلُونَ
12. «መንገዳችንን በእርግጥ የመራን ሲሆን በአላህ ላይ የማንመካበት ምን አለን? በማሰቃየታችሁም ላይ እንታገሳለን:: በአላህ ላይ ብቻ ተመኪዎች ሁሉ ይመኩ።» (አሉ)
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لِرُسُلِهِمۡ لَنُخۡرِجَنَّكُم مِّنۡ أَرۡضِنَآ أَوۡ لَتَعُودُنَّ فِي مِلَّتِنَاۖ فَأَوۡحَىٰٓ إِلَيۡهِمۡ رَبُّهُمۡ لَنُهۡلِكَنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ
13. እነዚያ በአላህ የካዱት ለመልእክተኞቻቸው: «ከምድራችን በእርግጥ እናወጣችኋለን ወይም ወደ ሃይማኖታችን ትመለሳላችሁ።» አሉ:: ወደ እነርሱም ጌታቸው እንዲህ ሲል ላከ: «(ከሓዲያን) በዳዮችን እናጠፋለን።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَنُسۡكِنَنَّكُمُ ٱلۡأَرۡضَ مِنۢ بَعۡدِهِمۡۚ ذَٰلِكَ لِمَنۡ خَافَ مَقَامِي وَخَافَ وَعِيدِ
14. «ከእነርሱ በኋላም በምድሪቱ በእርግጥ እናስቀምጣችኋለን:: ይህ በፊቴ መቆሙን ለሚፈራና ዛቻዬን ለሚፈራ ነው።»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱسۡتَفۡتَحُواْ وَخَابَ كُلُّ جَبَّارٍ عَنِيدٖ
15. እርዳታንም ከአላህ ፈለጉ፤ ተረዱም። ጨካኝ ሞገደኛ የሆነም ሁሉ አፈረ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مِّن وَرَآئِهِۦ جَهَنَّمُ وَيُسۡقَىٰ مِن مَّآءٖ صَدِيدٖ
16. ከስተፊቱ ገሀነም አለበት:: እዥ ከሆነም ውሃ ይጋታል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
يَتَجَرَّعُهُۥ وَلَا يَكَادُ يُسِيغُهُۥ وَيَأۡتِيهِ ٱلۡمَوۡتُ مِن كُلِّ مَكَانٖ وَمَا هُوَ بِمَيِّتٖۖ وَمِن وَرَآئِهِۦ عَذَابٌ غَلِيظٞ
17. ይጎነጨዋል፤ ሊውጠዉም አይቀርብም:: ሞትም ከየስፍራው ሁሉ ይመጣበታል:: እርሱም የሚሞት አይደለም:: ከበስተፊቱም ከባድ ቅጣት አለ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مَّثَلُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِرَبِّهِمۡۖ أَعۡمَٰلُهُمۡ كَرَمَادٍ ٱشۡتَدَّتۡ بِهِ ٱلرِّيحُ فِي يَوۡمٍ عَاصِفٖۖ لَّا يَقۡدِرُونَ مِمَّا كَسَبُواْ عَلَىٰ شَيۡءٖۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلضَّلَٰلُ ٱلۡبَعِيدُ
18. የእነዚያ በጌታቸው የካዱት ሰዎች መልካም ሥራዎቻቸው ምሳሌ በነፋሻ ቀን ነፋስ እንደ በረታችበት አመድ ነው:: በሠሩት ሥራ በምንም ላይ ሊጠቀሙ አይችሉም። ይህ እርሱ ሩቅ ጥፋት ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អ៊ីព្រហ៊ីម
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ