Check out the new design

আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ- মুহাম্মদ ছাদিক * - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

অৰ্থানুবাদ ছুৰা: আন-নূৰ   আয়াত:
يُقَلِّبُ ٱللَّهُ ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَعِبۡرَةٗ لِّأُوْلِي ٱلۡأَبۡصَٰرِ
አላህ ሌሊትንና ቀንን ያገላብጣል፡፡ በዚህም ለባለ ውስጥ ዓይኖች በእርግጥ ማስረጃ አልለበት፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَٱللَّهُ خَلَقَ كُلَّ دَآبَّةٖ مِّن مَّآءٖۖ فَمِنۡهُم مَّن يَمۡشِي عَلَىٰ بَطۡنِهِۦ وَمِنۡهُم مَّن يَمۡشِي عَلَىٰ رِجۡلَيۡنِ وَمِنۡهُم مَّن يَمۡشِي عَلَىٰٓ أَرۡبَعٖۚ يَخۡلُقُ ٱللَّهُ مَا يَشَآءُۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٞ
አላህም ተንቀሳቃሽን ሁሉ ከውሃ ፈጠረ፡፡ ከእነሱም በሆዱ ላይ የሚኼድ አልለ፡፡ ከእነሱም በሁለት እግሮች ላይ የሚኼድ አልለ፡፡ከእነሱም በአራት (እግሮች) ላይ የሚኼድ አልለ። አላህ የሚሻውን ሁሉ ይፈጥራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
لَّقَدۡ أَنزَلۡنَآ ءَايَٰتٖ مُّبَيِّنَٰتٖۚ وَٱللَّهُ يَهۡدِي مَن يَشَآءُ إِلَىٰ صِرَٰطٖ مُّسۡتَقِيمٖ
አብራሪን አንቀጾች በእርግጥ አወረድን፡፡ አላህም የሚሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይመራዋል፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَيَقُولُونَ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَبِٱلرَّسُولِ وَأَطَعۡنَا ثُمَّ يَتَوَلَّىٰ فَرِيقٞ مِّنۡهُم مِّنۢ بَعۡدِ ذَٰلِكَۚ وَمَآ أُوْلَٰٓئِكَ بِٱلۡمُؤۡمِنِينَ
በአላህና በመልክተኛውም አምነናል ታዘናልም ይላሉ፡፡ ከዚያም ከዚህ በኋላ ከእነሱ ከፊሉ ይሸሻል፡፡ እነዚያም ምእምናን አይደሉም፤
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَإِذَا دُعُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ لِيَحۡكُمَ بَيۡنَهُمۡ إِذَا فَرِيقٞ مِّنۡهُم مُّعۡرِضُونَ
ወደ አላህና ወደ መልክተኛውም በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ከእነሱ ከፊሉ ወዲያውኑ ይሸሻሉ፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَإِن يَكُن لَّهُمُ ٱلۡحَقُّ يَأۡتُوٓاْ إِلَيۡهِ مُذۡعِنِينَ
እውነቱም (ሐቁ) ለእነሱ ቢኾን ወደርሱ ታዛዦች ኾነው ይመጣሉ፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
أَفِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ أَمِ ٱرۡتَابُوٓاْ أَمۡ يَخَافُونَ أَن يَحِيفَ ٱللَّهُ عَلَيۡهِمۡ وَرَسُولُهُۥۚ بَلۡ أُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلظَّٰلِمُونَ
በልቦቻቸው ውስጥ በሺታ አለን? ወይስ (በነቢይነቱ) ተጠራጠሩን? ወይስ አላህና መልክተኛው በእነሱ ላይ የሚበድሉ መኾንን ይፈራሉን ይልቁንም፤ እነዚያ እነሱ በዳዮቹ ናቸው፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
إِنَّمَا كَانَ قَوۡلَ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ إِذَا دُعُوٓاْ إِلَى ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ لِيَحۡكُمَ بَيۡنَهُمۡ أَن يَقُولُواْ سَمِعۡنَا وَأَطَعۡنَاۚ وَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡمُفۡلِحُونَ
የምእምናን ቃል የነበረው ወደ አላህና ወደ መልክተኛው በመካከላቸው ሊፈርድ በተጠሩ ጊዜ ሰማን፤ ታዘዝንም ማለት ብቻ ነው፡፡ እነዚህም እነሱ የፈለጉትን የሚያገኙ ናቸው፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَيَخۡشَ ٱللَّهَ وَيَتَّقۡهِ فَأُوْلَٰٓئِكَ هُمُ ٱلۡفَآئِزُونَ
አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው፣ አላህንም የሚፈራና የሚጠነቀቀው ሰው፤ እነዚያ እነርሱ ፍለጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
۞ وَأَقۡسَمُواْ بِٱللَّهِ جَهۡدَ أَيۡمَٰنِهِمۡ لَئِنۡ أَمَرۡتَهُمۡ لَيَخۡرُجُنَّۖ قُل لَّا تُقۡسِمُواْۖ طَاعَةٞ مَّعۡرُوفَةٌۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ
(ለዘመቻ) ብታዛቸውም በእርግጥ ሊወጡ የጠነከሩ መሓሎቻቸውን በአላህ ስም ይምላሉ፡፡ «አትማሉ፤ የታወቀች (የንፍቅና) መታዘዝ ናትና፡፡ አላህ በምትሠሩት ነገር ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው።
আৰবী তাফছীৰসমূহ:
 
অৰ্থানুবাদ ছুৰা: আন-নূৰ
ছুৰাৰ তালিকা পৃষ্ঠা নং
 
আল-কোৰআনুল কাৰীমৰ অৰ্থানুবাদ - আমহাৰিক অনুবাদ- মুহাম্মদ ছাদিক - অনুবাদসমূহৰ সূচীপত্ৰ

অনুবাদ কৰিছে শ্বাইখ মুহাম্মদ চাদিক্ব আৰু মুহাম্মদ ছানী হাবীব চাহাবে। মৰ্কজ ৰুৱাদুত তাৰ্জামাৰ তত্ত্বাৱধানত ইয়াক উন্নীত কৰা হৈছে। ধাৰাবাহিক উন্নীত কৰণ, মূল্যায়ন আৰু মতামত প্ৰকাশৰ উদ্দেশ্যে মূল অনুবাদটো উন্মুক্ত কৰা হ'ল।

বন্ধ