Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي * - د ژباړو فهرست (لړلیک)

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

د معناګانو ژباړه سورت: نمل   آیت:
إِنِّي وَجَدتُّ ٱمۡرَأَةٗ تَمۡلِكُهُمۡ وَأُوتِيَتۡ مِن كُلِّ شَيۡءٖ وَلَهَا عَرۡشٌ عَظِيمٞ
23. «እኔ የምትገዛቸው የሆነችን ሴት ከነገሩም ሁሉ የተሰጠችን አገኘሁ:: ለእርሷም ታላቅ ዙፋን አላት።
عربي تفسیرونه:
وَجَدتُّهَا وَقَوۡمَهَا يَسۡجُدُونَ لِلشَّمۡسِ مِن دُونِ ٱللَّهِ وَزَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيۡطَٰنُ أَعۡمَٰلَهُمۡ فَصَدَّهُمۡ عَنِ ٱلسَّبِيلِ فَهُمۡ لَا يَهۡتَدُونَ
24. «እርስዋንም ሕዝቦችዋንም ከአላህ ሌላ ለጸሐይ ሲሰግዱ አገኘኋቸው። ሰይጣንም ለእነርሱ ሥራዎቻቸውን ሸልሞላቸዋል። ከእውነተኛዉም መንገድ አግዷቸዋል:: ስለዚህ እነርሱ ወደ እውነት አይመሩም።
عربي تفسیرونه:
أَلَّاۤ يَسۡجُدُواْۤ لِلَّهِ ٱلَّذِي يُخۡرِجُ ٱلۡخَبۡءَ فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَيَعۡلَمُ مَا تُخۡفُونَ وَمَا تُعۡلِنُونَ
25. «ለዚያም በሰማያትና በምድር ዉስጥ የተደበቀውን ለሚያወጣው የምትሸሽጉትንና የምትገልጹትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ ሰይጣን አግዷቸዋል።
عربي تفسیرونه:
ٱللَّهُ لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ ٱلۡعَرۡشِ ٱلۡعَظِيمِ۩
26. «አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም:: የታላቁ ዐርሽ ጌታ ነው።» (አለ) {1}
{1} እዚህ የንባብ ሱጁድ (ሱጁዱ ትላወህ) ይደረጋል።
عربي تفسیرونه:
۞ قَالَ سَنَنظُرُ أَصَدَقۡتَ أَمۡ كُنتَ مِنَ ٱلۡكَٰذِبِينَ
27. ሱለይማንም አለ፡- «እውነት እንደ ተናገርክ ወይም ከውሸታሞቹ እንደሆንክ ወደ ፊት እናያለን።
عربي تفسیرونه:
ٱذۡهَب بِّكِتَٰبِي هَٰذَا فَأَلۡقِهۡ إِلَيۡهِمۡ ثُمَّ تَوَلَّ عَنۡهُمۡ فَٱنظُرۡ مَاذَا يَرۡجِعُونَ
28. «ይህንን ደብዳቤዬን ይዘህ ሂድ:: ወደ እነርሱም ጣለው ከዚያ ከእነርሱ ዘወር በልና ምን እንደሚመልሱም ተመልከት።»
عربي تفسیرونه:
قَالَتۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَؤُاْ إِنِّيٓ أُلۡقِيَ إِلَيَّ كِتَٰبٞ كَرِيمٌ
29. እርሷም በደረሳት ጊዜ አለች፡- «እናንተ መማክርቶች ሆይ! እኔ ክብር ያለው ጽሑፍ ወደ እኔ ተጣለ።
عربي تفسیرونه:
إِنَّهُۥ مِن سُلَيۡمَٰنَ وَإِنَّهُۥ بِسۡمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحۡمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
30. «እርሱ ከሱለይማን ነው። እርሱም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
عربي تفسیرونه:
أَلَّا تَعۡلُواْ عَلَيَّ وَأۡتُونِي مُسۡلِمِينَ
31. «‹በእኔ ላይ አትኩሩ:: ታዛዦችም ሆናችሁ ወደ እኔ ኑ› የሚል ነው።»
عربي تفسیرونه:
قَالَتۡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلۡمَلَؤُاْ أَفۡتُونِي فِيٓ أَمۡرِي مَا كُنتُ قَاطِعَةً أَمۡرًا حَتَّىٰ تَشۡهَدُونِ
32. «እናንተ መማክርቶች ሆይ! በነገሬ የሚበጀውን ንገሩኝ እስከምትነግሩኝ ድረስ አንድንም ነገር ቆራጭ አይደለሁምና» አለች።
عربي تفسیرونه:
قَالُواْ نَحۡنُ أُوْلُواْ قُوَّةٖ وَأُوْلُواْ بَأۡسٖ شَدِيدٖ وَٱلۡأَمۡرُ إِلَيۡكِ فَٱنظُرِي مَاذَا تَأۡمُرِينَ
33. «እኛ የሃይል ባለቤቶች የብርቱ ጦርም ባለቤቶች ነን:: ግን ትዕዛዙ ከወደ አንቺ ብቻ ነው። ምን እንደምታዝዢንም አስተውይ» አሏት::
عربي تفسیرونه:
قَالَتۡ إِنَّ ٱلۡمُلُوكَ إِذَا دَخَلُواْ قَرۡيَةً أَفۡسَدُوهَا وَجَعَلُوٓاْ أَعِزَّةَ أَهۡلِهَآ أَذِلَّةٗۚ وَكَذَٰلِكَ يَفۡعَلُونَ
34. እርሷም አለች፡- «ንጉሶች ከተማን በሃይል በገቡባት ጊዜ ያበላሿታል የተከበሩ ሰዎቿንም ወራዶች ያደርጋሉ:: ልክ እንደዚሁ ነው የሚያደርጉት።
عربي تفسیرونه:
وَإِنِّي مُرۡسِلَةٌ إِلَيۡهِم بِهَدِيَّةٖ فَنَاظِرَةُۢ بِمَ يَرۡجِعُ ٱلۡمُرۡسَلُونَ
35. «እኔም ወደ እነርሱ ገጸበረከትን የምልክና መልዕክተኞቹ በምን እንደሚመልሱ የምጠባበቅ ነኝ።»
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: نمل
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي - د ژباړو فهرست (لړلیک)

محمد زین زهرالدین ژباړلی دی . د افریقا اکاډمۍ لخوا خپره شوې.

بندول