Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي * - د ژباړو فهرست (لړلیک)

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

د معناګانو ژباړه سورت: اسراء   آیت:

አል ኢስራዕ

سُبۡحَٰنَ ٱلَّذِيٓ أَسۡرَىٰ بِعَبۡدِهِۦ لَيۡلٗا مِّنَ ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡحَرَامِ إِلَى ٱلۡمَسۡجِدِ ٱلۡأَقۡصَا ٱلَّذِي بَٰرَكۡنَا حَوۡلَهُۥ لِنُرِيَهُۥ مِنۡ ءَايَٰتِنَآۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلۡبَصِيرُ
1. ጥራት ለዚያ ባሪያውን (ሙሐመድን) ከተከበረው የሐረም መስጊድ ወደ እዚያ ዙሪያውን ወደ ባረክነው ሩቁ (አል አቅሷ) መስጊድ በሌሊት ለወሰደው አምላክ ለአላህ ይሁን:: ይህን ያደረግን ተዓምራታችንን ልናሳየው ነው:: እነሆ እርሱ (አላህ) ሰሚዉና ተመልካቹ ነው::
عربي تفسیرونه:
وَءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ وَجَعَلۡنَٰهُ هُدٗى لِّبَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ أَلَّا تَتَّخِذُواْ مِن دُونِي وَكِيلٗا
2. ለሙሳም (ተውራት የተባለውን) መጽሐፍ ሰጠነውና ለኢስራኢል ልጆች መሪ አደረግነው:: ከእኔ ሌላ ወኪል (መጠጊያ) አድርጋችሁ ማንንም አታድርጉ“ስንልም አዘዝናቸው::
عربي تفسیرونه:
ذُرِّيَّةَ مَنۡ حَمَلۡنَا مَعَ نُوحٍۚ إِنَّهُۥ كَانَ عَبۡدٗا شَكُورٗا
3. «ከኑህ ጋር (በመርከቧ ላይ) የጫንናቸው (አማኝ )ዝርዮች ሆይ! (አላህን ተገዙ)፤ ኑህ በእርግጥ አምላኩን በብዛት አመስጋኝ ባሪያ ነበርና» አልናቸው።
عربي تفسیرونه:
وَقَضَيۡنَآ إِلَىٰ بَنِيٓ إِسۡرَٰٓءِيلَ فِي ٱلۡكِتَٰبِ لَتُفۡسِدُنَّ فِي ٱلۡأَرۡضِ مَرَّتَيۡنِ وَلَتَعۡلُنَّ عُلُوّٗا كَبِيرٗا
4. ለኢስራኢል ልጆችም፡ “በምድር ላይ ሁለት ጊዜ ጥፋት ትፈጽማላችሁ:: አለቅጥም አምባገነን ትሆናላችሁ::” ስንል በመጽሐፉ ውስጥ ገለጽን::
عربي تفسیرونه:
فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ أُولَىٰهُمَا بَعَثۡنَا عَلَيۡكُمۡ عِبَادٗا لَّنَآ أُوْلِي بَأۡسٖ شَدِيدٖ فَجَاسُواْ خِلَٰلَ ٱلدِّيَارِۚ وَكَانَ وَعۡدٗا مَّفۡعُولٗا
5. ከሁለቱ የመጀመሪያው ጥፋት መፈጸሚያ ወቅቱ በደረሰ ጊዜ የበረታ ኃይል ያላቸውን ባሮቻችንን በእናነተ ላይ ላክንባችሁ:: እነርሱም ቤቶችን ሁሉ በረበሩ:: ይህ መፈጸሙ የማይቀር ውሳኔ ነበር::
عربي تفسیرونه:
ثُمَّ رَدَدۡنَا لَكُمُ ٱلۡكَرَّةَ عَلَيۡهِمۡ وَأَمۡدَدۡنَٰكُم بِأَمۡوَٰلٖ وَبَنِينَ وَجَعَلۡنَٰكُمۡ أَكۡثَرَ نَفِيرًا
6. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ!) ከዚያም በኋላ በእነርሱ ላይ የድል አድራጊነትን እድል ሰጠናችሁ:: ገንዘብንና ወንዶች ልጆችንም ለገስናችሁ:: በሰው ኃይልም ብዙ አደረግናችሁ::
عربي تفسیرونه:
إِنۡ أَحۡسَنتُمۡ أَحۡسَنتُمۡ لِأَنفُسِكُمۡۖ وَإِنۡ أَسَأۡتُمۡ فَلَهَاۚ فَإِذَا جَآءَ وَعۡدُ ٱلۡأٓخِرَةِ لِيَسُـُٔواْ وُجُوهَكُمۡ وَلِيَدۡخُلُواْ ٱلۡمَسۡجِدَ كَمَا دَخَلُوهُ أَوَّلَ مَرَّةٖ وَلِيُتَبِّرُواْ مَا عَلَوۡاْ تَتۡبِيرًا
7. መልካምን ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ:: መጥፎንም ብትሠሩ በነፍሶቻችሁ ላይ ነው:: የኋለኛይቱ ጥፋት ቀጠሮ በደረሰ ጊዜ ፊቶቻችሁን ሊያስከፉ፤ መስጊዱንም በመጀመሪያ ጊዜ እንደገቡቡት ሊገቡ፤ ያሸነፉትንም ሁሉ ፈጽመው ማጥፋትን እንዲያጠፉ እንልካቸዋለን::
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: اسراء
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي - د ژباړو فهرست (لړلیک)

محمد زین زهرالدین ژباړلی دی . د افریقا اکاډمۍ لخوا خپره شوې.

بندول