Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي * - د ژباړو فهرست (لړلیک)

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

د معناګانو ژباړه سورت: هود   آیت:

ሁድ

الٓرۚ كِتَٰبٌ أُحۡكِمَتۡ ءَايَٰتُهُۥ ثُمَّ فُصِّلَتۡ مِن لَّدُنۡ حَكِيمٍ خَبِيرٍ
1.አሊፍ፤ ላም፤ ራ፤. ይህ ቁርኣን አናቅጾቹ በጥንካሬ የተሰካኩ ከዚያም የተዘረዘሩ፤ ጥበበኛና ውስጠ አዋቂ ከሆነው (አምላክ) ዘንድ የተወረደ መጽሐፍ ነው::
عربي تفسیرونه:
أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَۚ إِنَّنِي لَكُم مِّنۡهُ نَذِيرٞ وَبَشِيرٞ
2. መልዕክተኛው (እንዲህ በሚልበት ሰዎች ሆይ! ): «አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ:: እኔ ለእናንተ ከእርሱ ዘንድ የተላኩ አስፈራሪና አብሳሪ ነኝ።»
عربي تفسیرونه:
وَأَنِ ٱسۡتَغۡفِرُواْ رَبَّكُمۡ ثُمَّ تُوبُوٓاْ إِلَيۡهِ يُمَتِّعۡكُم مَّتَٰعًا حَسَنًا إِلَىٰٓ أَجَلٖ مُّسَمّٗى وَيُؤۡتِ كُلَّ ذِي فَضۡلٖ فَضۡلَهُۥۖ وَإِن تَوَلَّوۡاْ فَإِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٖ كَبِيرٍ
3. (እንዲህም በሚልበት ሰዎች ሆይ! ): «ጌታችሁን ምህረት ለምኑት:: ከዚያ ወደ እርሱ ተመለሱ:: እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መልካምን መጥቀም ይጠቅማችኋል:: ለትሩፋት ባለቤት ሁሉ ችሮታውን (ምንዳዉን) ይሰጠዋል:: ብትሸሹም እኔ በእናንተ ላይ የታላቅን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ::
عربي تفسیرونه:
إِلَى ٱللَّهِ مَرۡجِعُكُمۡۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ
4. «መመለሻችሁ ወደ አላህ ብቻ ነው። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።»
عربي تفسیرونه:
أَلَآ إِنَّهُمۡ يَثۡنُونَ صُدُورَهُمۡ لِيَسۡتَخۡفُواْ مِنۡهُۚ أَلَا حِينَ يَسۡتَغۡشُونَ ثِيَابَهُمۡ يَعۡلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعۡلِنُونَۚ إِنَّهُۥ عَلِيمُۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ
5. ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ! እነርሱ ከእርሱ ከአላህ ይደበቁ ዘንድ ደረቶቻቸውን ያጥፋሉ:: ሙስሊሞች ሆይ! አስተውሉ! ልብሶቻቸውን በሚከናነቡ ጊዜ የሚደብቁትንም ሆነ የሚገልጹትን ሁሉ ያውቃል:: እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ አዋቂ ነውና::
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: هود
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - د افریقا اکاډمي - د ژباړو فهرست (لړلیک)

محمد زین زهرالدین ژباړلی دی . د افریقا اکاډمۍ لخوا خپره شوې.

بندول