Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - محمد صادق * - د ژباړو فهرست (لړلیک)

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

د معناګانو ژباړه سورت: توبه   آیت:
فَلَا تُعۡجِبۡكَ أَمۡوَٰلُهُمۡ وَلَآ أَوۡلَٰدُهُمۡۚ إِنَّمَا يُرِيدُ ٱللَّهُ لِيُعَذِّبَهُم بِهَا فِي ٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَتَزۡهَقَ أَنفُسُهُمۡ وَهُمۡ كَٰفِرُونَ
ገንዘቦቻቸውና ልጆቻቸውም አይድነቁህ፡፡ አላህ የሚሻው በቅርቢቱ ሕይወት በነርሱ (በገንዘቦቻቸውና በልጆቻቸው) ሊቀጣቸው ነፍሶቻቸውም እነሱ ከሓዲዎች ኾነው ሊወጡ ብቻ ነው፡፡
عربي تفسیرونه:
وَيَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ إِنَّهُمۡ لَمِنكُمۡ وَمَا هُم مِّنكُمۡ وَلَٰكِنَّهُمۡ قَوۡمٞ يَفۡرَقُونَ
እነሱም በእርግጥ ከእናንተ ለመኾናቸው በአላህ ይምላሉ፡፡ እነርሱም ከናንተ አይደሉም፡፡ ግን እነሱ (አጋሪዎችን ያገኘ እንዳያገኛቸው) የሚፈሩ ሕዝቦች ናቸው፡፡
عربي تفسیرونه:
لَوۡ يَجِدُونَ مَلۡجَـًٔا أَوۡ مَغَٰرَٰتٍ أَوۡ مُدَّخَلٗا لَّوَلَّوۡاْ إِلَيۡهِ وَهُمۡ يَجۡمَحُونَ
መጠጊያን ወይም ዋሻዎችን ወይም መግቢያን (ቀዳዳ) ባገኙ ኖሮ እነርሱ እየገሰገሱ ወደርሱ በሸሹ ነበር፡፡
عربي تفسیرونه:
وَمِنۡهُم مَّن يَلۡمِزُكَ فِي ٱلصَّدَقَٰتِ فَإِنۡ أُعۡطُواْ مِنۡهَا رَضُواْ وَإِن لَّمۡ يُعۡطَوۡاْ مِنۡهَآ إِذَا هُمۡ يَسۡخَطُونَ
ከነሱም ውስጥ በምጽዋቶች የሚዘልፉህ ሰዎች አሉ፡፡ ከርሷም (የሚሹትን) ቢስሰጡ ይደሰታሉ፡፡ ከርሷም ባይስሰጡ እነሱ ያን ጊዜ ይጠላሉ፡፡
عربي تفسیرونه:
وَلَوۡ أَنَّهُمۡ رَضُواْ مَآ ءَاتَىٰهُمُ ٱللَّهُ وَرَسُولُهُۥ وَقَالُواْ حَسۡبُنَا ٱللَّهُ سَيُؤۡتِينَا ٱللَّهُ مِن فَضۡلِهِۦ وَرَسُولُهُۥٓ إِنَّآ إِلَى ٱللَّهِ رَٰغِبُونَ
እነሱም አላህና መልክተኛው የሰጣቸውን በወደዱ፣ «አላህም በቂያችን ነው፤ አላህ ከችሮታው በእርግጥ ይሰጠናል፣ መልክተኛውም (ይሰጠናል)፣ እኛ ወደ አላህ ከጃዮች ነን» ባሉ ኖሮ (ለነሱ በተሻላቸው ነበር)፡፡
عربي تفسیرونه:
۞ إِنَّمَا ٱلصَّدَقَٰتُ لِلۡفُقَرَآءِ وَٱلۡمَسَٰكِينِ وَٱلۡعَٰمِلِينَ عَلَيۡهَا وَٱلۡمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمۡ وَفِي ٱلرِّقَابِ وَٱلۡغَٰرِمِينَ وَفِي سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱبۡنِ ٱلسَّبِيلِۖ فَرِيضَةٗ مِّنَ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٞ
ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድኾች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሠሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱት፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) (ነጻ በማውጣት)፣ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሠሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
عربي تفسیرونه:
وَمِنۡهُمُ ٱلَّذِينَ يُؤۡذُونَ ٱلنَّبِيَّ وَيَقُولُونَ هُوَ أُذُنٞۚ قُلۡ أُذُنُ خَيۡرٖ لَّكُمۡ يُؤۡمِنُ بِٱللَّهِ وَيُؤۡمِنُ لِلۡمُؤۡمِنِينَ وَرَحۡمَةٞ لِّلَّذِينَ ءَامَنُواْ مِنكُمۡۚ وَٱلَّذِينَ يُؤۡذُونَ رَسُولَ ٱللَّهِ لَهُمۡ عَذَابٌ أَلِيمٞ
ከእነሱም (ከመናፍቃን) እነዚያ ነቢዩን የሚያሰቃዩ «እርሱም ጆሮ ነው» (ወሬ ሰሚ ነው) የሚሉ አልሉ፡፡ በላቸው ለእናንተ የበጎ (ወሬ) ሰሚ ነው፡፡ በአላህ ያምናል፣ ምእምናንንም ያምናቸዋል፣ ከእናንተም ውስጥ ለነዚያ ላመኑት እዝነት ነው፡፡ እነዚያም የአላህን መልክተኛ የሚያሰቃዩ ለነሱ አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: توبه
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - محمد صادق - د ژباړو فهرست (لړلیک)

د شیخ محمد صادق او محمد الثاني حبيب لخوا ژباړل شوې ده. دې ته د رواد الترجمة مرکز تر څارنې لاندې انکشاف ورکړل شوی، او اصلي ژباړې ته د نظرونو څرګندولو، ارزونې، او دوامداره پرمختګ او بیاکتنې لپاره فرصت شتون لري.

بندول