Check out the new design

د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - محمد صادق * - د ژباړو فهرست (لړلیک)

XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

د معناګانو ژباړه سورت: فصلت   آیت:
وَمِنۡ ءَايَٰتِهِۦٓ أَنَّكَ تَرَى ٱلۡأَرۡضَ خَٰشِعَةٗ فَإِذَآ أَنزَلۡنَا عَلَيۡهَا ٱلۡمَآءَ ٱهۡتَزَّتۡ وَرَبَتۡۚ إِنَّ ٱلَّذِيٓ أَحۡيَاهَا لَمُحۡيِ ٱلۡمَوۡتَىٰٓۚ إِنَّهُۥ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرٌ
አንተ ምድርን ደረቅ ኾና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው፡፡ በእርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ (በቡቃያዎችዋ) ትላወሳለች፡፡ ትነፋለችም፡፡ ያ ሕያው ያደረጋት ጌታ በእርግጥ ሙታንን ሕያው አድራጊ ነው፡፡ እነርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና፡፡
عربي تفسیرونه:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يُلۡحِدُونَ فِيٓ ءَايَٰتِنَا لَا يَخۡفَوۡنَ عَلَيۡنَآۗ أَفَمَن يُلۡقَىٰ فِي ٱلنَّارِ خَيۡرٌ أَم مَّن يَأۡتِيٓ ءَامِنٗا يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِۚ ٱعۡمَلُواْ مَا شِئۡتُمۡ إِنَّهُۥ بِمَا تَعۡمَلُونَ بَصِيرٌ
እነዚያ አንቀጾቻችንን የሚያጣምሙ በእኛ ላይ አይደበቁም፡፡ በእሳት ውስጥ የሚጣለው ሰው ይበልጣልን? ወይስ በትንሣኤ ቀን ጸጥተኛ ኾኖ የሚመጣው ሰው? የሻችሁትን ሥሩ (ዋጋችሁን ታገኛላችሁ)፡፡ እርሱ የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና፡፡
عربي تفسیرونه:
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِٱلذِّكۡرِ لَمَّا جَآءَهُمۡۖ وَإِنَّهُۥ لَكِتَٰبٌ عَزِيزٞ
እነዚያ በቁርኣን እርሱ አሸናፊ መጽሐፍ ሲኾን በመጣላቸው ጊዜ የካዱት (ጠፊዎች ናቸው)፡፡
عربي تفسیرونه:
لَّا يَأۡتِيهِ ٱلۡبَٰطِلُ مِنۢ بَيۡنِ يَدَيۡهِ وَلَا مِنۡ خَلۡفِهِۦۖ تَنزِيلٞ مِّنۡ حَكِيمٍ حَمِيدٖ
ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፡፡ ጥበበኛ ምስጉን ከኾነው ጌታ የተወረደ ው፡፡
عربي تفسیرونه:
مَّا يُقَالُ لَكَ إِلَّا مَا قَدۡ قِيلَ لِلرُّسُلِ مِن قَبۡلِكَۚ إِنَّ رَبَّكَ لَذُو مَغۡفِرَةٖ وَذُو عِقَابٍ أَلِيمٖ
ካንተ በፊት ለነበሩት መልክተኞች የተባለው ብጤ እንጅ ለአንተ ሌላ አይባልም፡፡ ጌታህ የምህረት ባለቤትና የአሳማሚ ቅጣት ባለቤት ነው፡፡
عربي تفسیرونه:
وَلَوۡ جَعَلۡنَٰهُ قُرۡءَانًا أَعۡجَمِيّٗا لَّقَالُواْ لَوۡلَا فُصِّلَتۡ ءَايَٰتُهُۥٓۖ ءَا۬عۡجَمِيّٞ وَعَرَبِيّٞۗ قُلۡ هُوَ لِلَّذِينَ ءَامَنُواْ هُدٗى وَشِفَآءٞۚ وَٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ فِيٓ ءَاذَانِهِمۡ وَقۡرٞ وَهُوَ عَلَيۡهِمۡ عَمًىۚ أُوْلَٰٓئِكَ يُنَادَوۡنَ مِن مَّكَانِۭ بَعِيدٖ
በአጀምኛ የኾነ ቁርኣን ባደረግነው ኖሮ አንቀጾቹ «(በምናውቀው ቋንቋ) አይብራሩም ኖሯልን? (ቁርኣኑ) አጀምኛና (መልክተኛው) ዐረባዊ ይኾናልን?» ባሉ ነበር እርሱ ለእነዚያ ለአመኑት መምሪያና መፈወሻ ነው፡፡ እነዚያም የማያምኑት በጆሮዎቻቸው ውስጥ ድንቁርና ነው፡፡ (አይሰሙትም)፡፡ እርሱ በእነርሱ ላይ እውርነት ነው፡፡ እነዚያ ከሩቅ ስፍራ እንደሚጥጠሩ ናቸው፡፡ [1]
[1] አጀምኛ ማለት ከአረብኛ ውጪ ያሉ ቋንቋዎች ማለት ነው።
عربي تفسیرونه:
وَلَقَدۡ ءَاتَيۡنَا مُوسَى ٱلۡكِتَٰبَ فَٱخۡتُلِفَ فِيهِۚ وَلَوۡلَا كَلِمَةٞ سَبَقَتۡ مِن رَّبِّكَ لَقُضِيَ بَيۡنَهُمۡۚ وَإِنَّهُمۡ لَفِي شَكّٖ مِّنۡهُ مُرِيبٖ
ሙሳንም መጽሐፉን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ በእርሱም ተለያዩበት፡፡ ከጌታህም ያለፈች ቃል ባልነበረች ኖሮ በመካከላቸው በተፈረደ ነበር፡፡ እነርሱም ከእርሱ አወላዋይ በኾነ ጥርጣሬ ውስጥ ናቸው፡፡
عربي تفسیرونه:
مَّنۡ عَمِلَ صَٰلِحٗا فَلِنَفۡسِهِۦۖ وَمَنۡ أَسَآءَ فَعَلَيۡهَاۗ وَمَا رَبُّكَ بِظَلَّٰمٖ لِّلۡعَبِيدِ
መልካም የሠራ ሰው ለነፍሱ ነው፡፡ ያጠፋም ሰው በእርሷ ላይ ነው፡፡ ጌታህም ለባሮቹ በዳይ አይደለም፡፡
عربي تفسیرونه:
 
د معناګانو ژباړه سورت: فصلت
د سورتونو فهرست (لړلیک) د مخ نمبر
 
د قرآن کریم د معناګانو ژباړه - امهري ژباړه - محمد صادق - د ژباړو فهرست (لړلیک)

د شیخ محمد صادق او محمد الثاني حبيب لخوا ژباړل شوې ده. دې ته د رواد الترجمة مرکز تر څارنې لاندې انکشاف ورکړل شوی، او اصلي ژباړې ته د نظرونو څرګندولو، ارزونې، او دوامداره پرمختګ او بیاکتنې لپاره فرصت شتون لري.

بندول