Check out the new design

ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ * - ߘߟߊߡߌߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ߬ߟߌ ߝߐߘߊ ߘߏ߫: ߦߋߟߋ߲   ߟߝߊߙߌ ߘߏ߫:
۞ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَتَّبِعُواْ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيۡطَٰنِۚ وَمَن يَتَّبِعۡ خُطُوَٰتِ ٱلشَّيۡطَٰنِ فَإِنَّهُۥ يَأۡمُرُ بِٱلۡفَحۡشَآءِ وَٱلۡمُنكَرِۚ وَلَوۡلَا فَضۡلُ ٱللَّهِ عَلَيۡكُمۡ وَرَحۡمَتُهُۥ مَا زَكَىٰ مِنكُم مِّنۡ أَحَدٍ أَبَدٗا وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يُزَكِّي مَن يَشَآءُۗ وَٱللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٞ
21. እናንተ ያመናችሁሆይ! የሰይጣንን እርምጃዎች አትከተሉ:: የሰይጣንን እርምጃዎች የሚከተል ሰው ሁሉ ኃጢአትን ተሸከመ:: እርሱ በመጥፎና በሚጠላ ነገር ያዛልና፤ በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከናንተ አንድም ፈጽሞ (ከወንጀል) ባልጠራ ነበር:: ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠራል:: አላህ ሁሉንም ሰሚ ሁሉንም አዋቂ ነው።
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَلَا يَأۡتَلِ أُوْلُواْ ٱلۡفَضۡلِ مِنكُمۡ وَٱلسَّعَةِ أَن يُؤۡتُوٓاْ أُوْلِي ٱلۡقُرۡبَىٰ وَٱلۡمَسَٰكِينَ وَٱلۡمُهَٰجِرِينَ فِي سَبِيلِ ٱللَّهِۖ وَلۡيَعۡفُواْ وَلۡيَصۡفَحُوٓاْۗ أَلَا تُحِبُّونَ أَن يَغۡفِرَ ٱللَّهُ لَكُمۡۚ وَٱللَّهُ غَفُورٞ رَّحِيمٌ
22. ከናንተም መካከል የችሮታና የክብረት ባለቤቶች የሆኑት ክፍሎች ለቅርብ ዘመዶችና ለድሆችና በአላህም መንገድ ለተሰደዱ ሰዎች ምንንም ነገር ላይሰጡ አይማሉ:: ይቅርታም ያድርጉ:: ጥፋተኞቹንም ይለፉ። አላህ ለእናንተ ሊምር አትወዱምን ? አላህ መሓሪና አዛኝ ነው::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
إِنَّ ٱلَّذِينَ يَرۡمُونَ ٱلۡمُحۡصَنَٰتِ ٱلۡغَٰفِلَٰتِ ٱلۡمُؤۡمِنَٰتِ لُعِنُواْ فِي ٱلدُّنۡيَا وَٱلۡأٓخِرَةِ وَلَهُمۡ عَذَابٌ عَظِيمٞ
23. እነዚያ ጥብቆቹንና ከዝሙት ዘንጊዎቹን ምዕምናት የሚሰድቡ ሰዎች ሁሉ በቅርቢቱም ሆነ በመጨረሻይቱ ዓለም ተረገሙ:: ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አለባቸው::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
يَوۡمَ تَشۡهَدُ عَلَيۡهِمۡ أَلۡسِنَتُهُمۡ وَأَيۡدِيهِمۡ وَأَرۡجُلُهُم بِمَا كَانُواْ يَعۡمَلُونَ
24. በእነርሱ ላይ ምላሶቻቸው እጆቻቸውና እግሮቻቸው ይሰሩት በነበሩት ነገር ሁሉ በሚመሰክሩባቸው ቀን ከባድ ቅጣት አለላቸው::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
يَوۡمَئِذٖ يُوَفِّيهِمُ ٱللَّهُ دِينَهُمُ ٱلۡحَقَّ وَيَعۡلَمُونَ أَنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلۡحَقُّ ٱلۡمُبِينُ
25. በዚያም ቀን አላህ ተገቢ ዋጋቸውን ይሞላላቸዋል:: አላህም ፍፁም ግልፅ እውነት መሆኑን ያውቃሉ።
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
ٱلۡخَبِيثَٰتُ لِلۡخَبِيثِينَ وَٱلۡخَبِيثُونَ لِلۡخَبِيثَٰتِۖ وَٱلطَّيِّبَٰتُ لِلطَّيِّبِينَ وَٱلطَّيِّبُونَ لِلطَّيِّبَٰتِۚ أُوْلَٰٓئِكَ مُبَرَّءُونَ مِمَّا يَقُولُونَۖ لَهُم مَّغۡفِرَةٞ وَرِزۡقٞ كَرِيمٞ
26. መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎቹ ወንዶች፤መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች ብቻ የተገቡ ናቸው:: ጥሩዎቹ ሴቶችም ለጥሩዎቹ ወንዶች፤ ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች ብቻ የሚገቡ ናቸው:: እነዚህ ጥሩዎቹም መጥፎዎቹ ከሚሉት ነገር ንጹህ የተደረጉ ናቸው:: ለእነርሱ በገነት ምህረትና መልካም ሲሳይ አለላቸው::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تَدۡخُلُواْ بُيُوتًا غَيۡرَ بُيُوتِكُمۡ حَتَّىٰ تَسۡتَأۡنِسُواْ وَتُسَلِّمُواْ عَلَىٰٓ أَهۡلِهَاۚ ذَٰلِكُمۡ خَيۡرٞ لَّكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَذَكَّرُونَ
27. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቹ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ በሌላ ሰዎች ቤቶች አትግቡ:: ይህ ጉዳይ ለእናንተም መልካም ነው:: እናንተ ትገነዘቡ ዘንድ በዚህ ታዘዛችሁ::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
 
ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ߬ߟߌ ߝߐߘߊ ߘߏ߫: ߦߋߟߋ߲
ߝߐߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ
 
ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ - ߘߟߊߡߌߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ

ߡߎ߬ߤ߭ߊߡߡߊߘߎ߫ ߛߌ߲ߣߌ߲ ߛߌߙߘߌ߲ߘߌ߲߫ ߓߟߏ߫. ߛߊ߬ߘߊ߬ߙߌ߫ ߊ߲ߞߊ߬ߘߌ߬ߡߌ߫ ߊߝߙߌߞߌ߫.

ߘߊߕߎ߲߯ߠߌ߲