Check out the new design

ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ * - ߘߟߊߡߌߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ߬ߟߌ ߝߐߘߊ ߘߏ߫: ߛߎߘߐߛߣߍߡߊ   ߟߝߊߙߌ ߘߏ߫:
عَسَىٰ رَبُّكُمۡ أَن يَرۡحَمَكُمۡۚ وَإِنۡ عُدتُّمۡ عُدۡنَاۚ وَجَعَلۡنَا جَهَنَّمَ لِلۡكَٰفِرِينَ حَصِيرًا
8. (የኢስራኢል ልጆች ሆይ! በመጽሐፉም አልን ብትጸጸቱ) «ጌታችሁ ሊያዝንላችሁ ይከጀላል:: ወደ ማጥፋት እንደገና ብትመለሱም እኛም ወደ ቅጣቱ እንመለሳለን:: ገሀነምንም ለከሓዲያን ሁሉ ማሰሪያ አድርገናል።»
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
إِنَّ هَٰذَا ٱلۡقُرۡءَانَ يَهۡدِي لِلَّتِي هِيَ أَقۡوَمُ وَيُبَشِّرُ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ ٱلَّذِينَ يَعۡمَلُونَ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أَنَّ لَهُمۡ أَجۡرٗا كَبِيرٗا
9. ይህ ቁርኣን ወደዚያች በሁሉ ነገር ቀጥተኛ ወደ ሆነችው መንገድ ይመራል:: እነዚያንም በጎ የሚሠሩትንም አማኞች ለእነርሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መሆኑን ያበስራል::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَأَنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ أَعۡتَدۡنَا لَهُمۡ عَذَابًا أَلِيمٗا
10. እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ለእነርሱ አሳማሚ ቅጣትን አዘጋጅተንላቸዋል::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَيَدۡعُ ٱلۡإِنسَٰنُ بِٱلشَّرِّ دُعَآءَهُۥ بِٱلۡخَيۡرِۖ وَكَانَ ٱلۡإِنسَٰنُ عَجُولٗا
11. ሰው መልካምን ነገር እንደሚለምን ሁሉ መጥፎንም ነገር ይለምናል:: ሰዉም ቸኳይ ነውና::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَجَعَلۡنَا ٱلَّيۡلَ وَٱلنَّهَارَ ءَايَتَيۡنِۖ فَمَحَوۡنَآ ءَايَةَ ٱلَّيۡلِ وَجَعَلۡنَآ ءَايَةَ ٱلنَّهَارِ مُبۡصِرَةٗ لِّتَبۡتَغُواْ فَضۡلٗا مِّن رَّبِّكُمۡ وَلِتَعۡلَمُواْ عَدَدَ ٱلسِّنِينَ وَٱلۡحِسَابَۚ وَكُلَّ شَيۡءٖ فَصَّلۡنَٰهُ تَفۡصِيلٗا
12. ሌሊትንና ቀንን ለችሎታችን ምልክቶች አደረግን:: የሌሊትን ምልክትም አበስን:: የቀንን ምልክትም የምታሳይ አደረግን:: ይህም የሆነበት ከአላህ ትርፍን ልትፈልጉበትና የዓመታትንም ቁጥርና ሒሳብን ታውቁበት ዘንድ ነው:: ነገሩንም ሁሉ ለያይተን ዘረዘርነው::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَكُلَّ إِنسَٰنٍ أَلۡزَمۡنَٰهُ طَٰٓئِرَهُۥ فِي عُنُقِهِۦۖ وَنُخۡرِجُ لَهُۥ يَوۡمَ ٱلۡقِيَٰمَةِ كِتَٰبٗا يَلۡقَىٰهُ مَنشُورًا
13. ሰውን ሁሉ በራሪውን (ሥራውን) በአንገቱ ላይ አስያዝነው:: ለእርሱም በትንሣኤ ቀን የተዘረጋ ሆኖ የሚያገኘው የሆነን መጽሐፍ እናወጣለታለን::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
ٱقۡرَأۡ كِتَٰبَكَ كَفَىٰ بِنَفۡسِكَ ٱلۡيَوۡمَ عَلَيۡكَ حَسِيبٗا
14. (ከዚያም) «መጽሐፍህን አንብብ:: ዛሬ ባንተ ላይ ተቆጣጣሪነት በነፍስህ ብቻ በቃ።» ይባላል።
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
مَّنِ ٱهۡتَدَىٰ فَإِنَّمَا يَهۡتَدِي لِنَفۡسِهِۦۖ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّمَا يَضِلُّ عَلَيۡهَاۚ وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰۗ وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّىٰ نَبۡعَثَ رَسُولٗا
15. በቀናው መንገድ የተመራ ሁሉ የሚመራው ለእራሱ ብቻ ነው:: ከቀናው መንገድ የተሳሳተም የመሳሳቱ ጉዳት በእርሱ ላይ ብቻ ነው:: ተሸካሚም ነፍስ የሌላይቱን ኃጢአት አትሸከምም:: መልዕክተኛንም እስከምንልክ ድረስ ማንንም የምንቀጣ አይደለንም።
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَإِذَآ أَرَدۡنَآ أَن نُّهۡلِكَ قَرۡيَةً أَمَرۡنَا مُتۡرَفِيهَا فَفَسَقُواْ فِيهَا فَحَقَّ عَلَيۡهَا ٱلۡقَوۡلُ فَدَمَّرۡنَٰهَا تَدۡمِيرٗا
16. ማንኛዋንም ከተማ ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ ባለ ጸጋዎችዋን እናዛቸዋለን:: በውስጧም ያምፃሉ:: በእርሷም ላይ የቅጣት ቃሉ ይፈጸምባታል:: ከዚያም ማውደምን እናወድማታለን::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
وَكَمۡ أَهۡلَكۡنَا مِنَ ٱلۡقُرُونِ مِنۢ بَعۡدِ نُوحٖۗ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ بِذُنُوبِ عِبَادِهِۦ خَبِيرَۢا بَصِيرٗا
17. ከኑሕም በኋላ ከየክፍለ ዘመናት ሰዎች ያጠፋናቸው ብዙዎች ናቸው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የባሮቹንም ኃጢአቶች ውስጠ አዋቂ ተመልካች መሆን በጌታህ ብቻ በቃ::
ߊߙߊߓߎߞߊ߲ߡߊ ߞߘߐߦߌߘߊ ߟߎ߬:
 
ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌ߬ߘߊ߬ߟߌ ߝߐߘߊ ߘߏ߫: ߛߎߘߐߛߣߍߡߊ
ߝߐߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ ߞߐߜߍ ߝߙߍߕߍ
 
ߞߎ߬ߙߣߊ߬ ߞߟߊߒߞߋ ߞߘߐ ߟߎ߬ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߡߎߤߊߙߌߞߊ߲ ߘߟߊߡߌߘߊ - ߊߞߊ߬ߘߌߡߌߘߌ ߊߝߙߌߞߌߟߊ - ߘߟߊߡߌߘߊ ߟߎ߫ ߦߌ߬ߘߊ߬ߥߟߊ

ߡߎ߬ߤ߭ߊߡߡߊߘߎ߫ ߛߌ߲ߣߌ߲ ߛߌߙߘߌ߲ߘߌ߲߫ ߓߟߏ߫. ߛߊ߬ߘߊ߬ߙߌ߫ ߊ߲ߞߊ߬ߘߌ߬ߡߌ߫ ߊߝߙߌߞߌ߫.

ߘߊߕߎ߲߯ߠߌ߲