Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: കഹ്ഫ്   ആയത്ത്:
وَإِذِ ٱعۡتَزَلۡتُمُوهُمۡ وَمَا يَعۡبُدُونَ إِلَّا ٱللَّهَ فَأۡوُۥٓاْ إِلَى ٱلۡكَهۡفِ يَنشُرۡ لَكُمۡ رَبُّكُم مِّن رَّحۡمَتِهِۦ وَيُهَيِّئۡ لَكُم مِّنۡ أَمۡرِكُم مِّرۡفَقٗا
16. «እነርሱንና ያንን ከአላህ ሌላ የሚገዙትን በተለያችሁ ጊዜ ወደ ዋሻው ተጠጉ። ጌታችሁ ለእናንተ ከችሮታው ይዘረጋላችኋልና፤ ከነገራችሁም ለእናንተ መጠቃቀሚያ ያዘጋጅላችኋልና።» (ተባባሉ)።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
۞ وَتَرَى ٱلشَّمۡسَ إِذَا طَلَعَت تَّزَٰوَرُ عَن كَهۡفِهِمۡ ذَاتَ ٱلۡيَمِينِ وَإِذَا غَرَبَت تَّقۡرِضُهُمۡ ذَاتَ ٱلشِّمَالِ وَهُمۡ فِي فَجۡوَةٖ مِّنۡهُۚ ذَٰلِكَ مِنۡ ءَايَٰتِ ٱللَّهِۗ مَن يَهۡدِ ٱللَّهُ فَهُوَ ٱلۡمُهۡتَدِۖ وَمَن يُضۡلِلۡ فَلَن تَجِدَ لَهُۥ وَلِيّٗا مُّرۡشِدٗا
17.ጸሐይዋ በወጣች ጊዜ ከዋሻቸው ወደ ቀኝ ጎን ስታዘነብል ታያታለህ:: በገባችም ጊዜ ከሰፊው ዋሻ ውስጥ እያሉ በግራ በኩል ትተዋቸዋለች:: ይህ ከአላህ ተዓምራት አንዱ ነው:: አላህ ያቀናው በእርግጥም የተቀናው እርሱ ብቻ ነው:: እርሱ ያጠመመውን ደግሞ ቅኑን መንገድ የሚመራው ረዳት ማንንም አታገኝለትም::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَتَحۡسَبُهُمۡ أَيۡقَاظٗا وَهُمۡ رُقُودٞۚ وَنُقَلِّبُهُمۡ ذَاتَ ٱلۡيَمِينِ وَذَاتَ ٱلشِّمَالِۖ وَكَلۡبُهُم بَٰسِطٞ ذِرَاعَيۡهِ بِٱلۡوَصِيدِۚ لَوِ ٱطَّلَعۡتَ عَلَيۡهِمۡ لَوَلَّيۡتَ مِنۡهُمۡ فِرَارٗا وَلَمُلِئۡتَ مِنۡهُمۡ رُعۡبٗا
18. እነርሱ በጥልቅ እንቅልፍ ውስጥ እያሉ የነቁ ይመስሉሃል:: ወደቀኝና ወደ ግራ ጎናቸው እናገላብጣቸዋለን:: ውሻቸዉም በዋሻቸው በር ላይ የፊት እግሩን ዘርግቷል:: ብታያቸው ኖሮ ከእነርሱ በእርግጥ የምትሸሽ ኾነህ በዞርክ ነበር:: በፍርሀትም በተሞላህ ነበር::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَكَذَٰلِكَ بَعَثۡنَٰهُمۡ لِيَتَسَآءَلُواْ بَيۡنَهُمۡۚ قَالَ قَآئِلٞ مِّنۡهُمۡ كَمۡ لَبِثۡتُمۡۖ قَالُواْ لَبِثۡنَا يَوۡمًا أَوۡ بَعۡضَ يَوۡمٖۚ قَالُواْ رَبُّكُمۡ أَعۡلَمُ بِمَا لَبِثۡتُمۡ فَٱبۡعَثُوٓاْ أَحَدَكُم بِوَرِقِكُمۡ هَٰذِهِۦٓ إِلَى ٱلۡمَدِينَةِ فَلۡيَنظُرۡ أَيُّهَآ أَزۡكَىٰ طَعَامٗا فَلۡيَأۡتِكُم بِرِزۡقٖ مِّنۡهُ وَلۡيَتَلَطَّفۡ وَلَا يُشۡعِرَنَّ بِكُمۡ أَحَدًا
19. ልክ እንዳስተኛናቸውም ሁሉ በመካከላቸው እንዲጠያየቁም ቀሰቀስናቸው:: ከእነርሱ አንድ ተናጋሪ «ምን ያህል ቆያችሁ አለ?» ሌሎቹም «አንድን ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየን።» አሉ። ተባባሉም: «ጌታችሁ የቆያችሁትን ጊዜ ልክ አዋቂ ነው:: ከዚህም ገንዘባችሁ ጋር አንዳችሁን ወደ ከተማይቱ ላኩ:: ከምግብ የትኛዋ ንጹህ መሆኗንም ይመልከት:: (ከንጹሑ) ምግብን ያምጣላችሁ:: ቀስም ይበል:: በእናንተም አንድንም ሰው አያሳውቅ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
إِنَّهُمۡ إِن يَظۡهَرُواْ عَلَيۡكُمۡ يَرۡجُمُوكُمۡ أَوۡ يُعِيدُوكُمۡ فِي مِلَّتِهِمۡ وَلَن تُفۡلِحُوٓاْ إِذًا أَبَدٗا
20. «እነርሱ በእናንተ ላይ ቢዘልቁ ይቀጠቅጧችኋል:: ወይም ወደ ሃይማኖታቸው ይመልሷችኋል፤ ያን ጊዜም በፍጹም ፍላጎታችሁን አታገኙም።» ተባባሉ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: കഹ്ഫ്
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക