Check out the new design

വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി * - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: റഅ്ദ്   ആയത്ത്:
۞ أَفَمَن يَعۡلَمُ أَنَّمَآ أُنزِلَ إِلَيۡكَ مِن رَّبِّكَ ٱلۡحَقُّ كَمَنۡ هُوَ أَعۡمَىٰٓۚ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُوْلُواْ ٱلۡأَلۡبَٰبِ
19. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከጌታህ ወደ አንተ የተወረደው ሁሉ እውነት መሆኑን የሚያውቅ ሰው ልክ እንደዚያ እርሱ እውር እንደ ሆነው ሰው ነውን? የሚገሠጹት የአእምሮ ባለቤቶች ብቻ ናቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
ٱلَّذِينَ يُوفُونَ بِعَهۡدِ ٱللَّهِ وَلَا يَنقُضُونَ ٱلۡمِيثَٰقَ
20. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን የሚሞሉ የጠበቀውንም ኪዳን የማያፈርሱ ናቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَٱلَّذِينَ يَصِلُونَ مَآ أَمَرَ ٱللَّهُ بِهِۦٓ أَن يُوصَلَ وَيَخۡشَوۡنَ رَبَّهُمۡ وَيَخَافُونَ سُوٓءَ ٱلۡحِسَابِ
21. እነዚያም አላህ እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቀጥሉ፤ ጌታቸውንም የሚያከብሩ፤ መጥፎንም ቁጥጥር የሚፈሩ ናቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَٱلَّذِينَ صَبَرُواْ ٱبۡتِغَآءَ وَجۡهِ رَبِّهِمۡ وَأَقَامُواْ ٱلصَّلَوٰةَ وَأَنفَقُواْ مِمَّا رَزَقۡنَٰهُمۡ سِرّٗا وَعَلَانِيَةٗ وَيَدۡرَءُونَ بِٱلۡحَسَنَةِ ٱلسَّيِّئَةَ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمۡ عُقۡبَى ٱلدَّارِ
22. እነዚያም የጌታቸውን ውዴታ ለመፈለግ የታገሱ ሶላትንም አዘውትረው የሰገዱ ሰዎች እኛ ከሰጠናቸው ሲሳይም በምስጢርም ሆነ በግልጽ የመጸወቱ ክፉውንም በበጎ የሚገፈትሩ ናቸው:: እነዚያ ለእነርሱ መጨረሻይቱ ምስጉን አገር አለችላቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
جَنَّٰتُ عَدۡنٖ يَدۡخُلُونَهَا وَمَن صَلَحَ مِنۡ ءَابَآئِهِمۡ وَأَزۡوَٰجِهِمۡ وَذُرِّيَّٰتِهِمۡۖ وَٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَدۡخُلُونَ عَلَيۡهِم مِّن كُلِّ بَابٖ
23. እርሷም የመኖሪያ ገነቶች ናት:: ይገቡባታል:: ከአባቶቻቸዉም ከሚስቶቻቸዉም ከዝርያቸዉም መልካም የሠራ ሰው ሁሉ ይገባባታል። መላዕክትም በእነርሱ ላይ ከየደጃፉ ሁሉ ይገባሉ።
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
سَلَٰمٌ عَلَيۡكُم بِمَا صَبَرۡتُمۡۚ فَنِعۡمَ عُقۡبَى ٱلدَّارِ
24. «ሰላም ለእናንተ ይሁን:: ይህ ምንዳ በመታገሳችሁ የተሰጣችሁ ነው:: የመጨረሻይቱም ሀገር ምን ታምር!» ይሏቸዋል::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَٱلَّذِينَ يَنقُضُونَ عَهۡدَ ٱللَّهِ مِنۢ بَعۡدِ مِيثَٰقِهِۦ وَيَقۡطَعُونَ مَآ أَمَرَ ٱللَّهُ بِهِۦٓ أَن يُوصَلَ وَيُفۡسِدُونَ فِي ٱلۡأَرۡضِ أُوْلَٰٓئِكَ لَهُمُ ٱللَّعۡنَةُ وَلَهُمۡ سُوٓءُ ٱلدَّارِ
25. እነዚያ የአላህን ቃል ኪዳን ከጠበቀ በኋላ የሚያፈርሱ፤ አላህም እንዲቀጠል በእርሱ ያዘዘውን ነገር የሚቆርጡ፤ በምድርም ላይ የሚያበላሹ እነዚያ ለእነርሱ እርግማን አለባቸው:: ለእነርሱም መጥፎ ሀገር ገሀነም አለላቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
ٱللَّهُ يَبۡسُطُ ٱلرِّزۡقَ لِمَن يَشَآءُ وَيَقۡدِرُۚ وَفَرِحُواْ بِٱلۡحَيَوٰةِ ٱلدُّنۡيَا وَمَا ٱلۡحَيَوٰةُ ٱلدُّنۡيَا فِي ٱلۡأٓخِرَةِ إِلَّا مَتَٰعٞ
26. አላህ ለሚሻው ሁሉ ሲሳይን ያሰፋል:: ለሚሻውም ያጠባል:: ከሓዲያን በቅርቢቱም ሕይወት ተደሰቱ:: የቅርቢቱም ሕይወት ከመጨረሻይቱ አንጻር ትንሽ መጠቀሚያ እንጂ ምንም አይደለችም::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ لَوۡلَآ أُنزِلَ عَلَيۡهِ ءَايَةٞ مِّن رَّبِّهِۦۚ قُلۡ إِنَّ ٱللَّهَ يُضِلُّ مَن يَشَآءُ وَيَهۡدِيٓ إِلَيۡهِ مَنۡ أَنَابَ
27. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች «በእርሱ ላይ ከጌታው ተዓምር ለምን አልተወረደልትም?» ይላሉ:: «አላህ የሚሻውን ሰው ያጠማል:: የተመለሰንም ሰው ወደ እርሱ ይመራል።» በላቸው::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَتَطۡمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكۡرِ ٱللَّهِۗ أَلَا بِذِكۡرِ ٱللَّهِ تَطۡمَئِنُّ ٱلۡقُلُوبُ
28. እነርሱም እነዚያ በአላህ ያመኑ ልቦቻቸዉም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው:: አስተውሉ:: አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ::
അറബി ഖുർആൻ വിവരണങ്ങൾ:
 
പരിഭാഷ അദ്ധ്യായം: റഅ്ദ്
സൂറത്തുകളുടെ സൂചിക പേജ് നമ്പർ
 
വിശുദ്ധ ഖുർആൻ പരിഭാഷ - അംഹാരിക് പരിഭാഷ - ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി - വിവർത്തനങ്ങളുടെ സൂചിക

മൊഴിമാറ്റം മുഹമ്മദ് സെയിൻ സഹ്റുദ്ദീൻ. ആഫ്രിക്ക അക്കാദമി പ്രസിദ്ധീകരണം.

അടക്കുക