Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាន់ណាច់ម៍   អាយ៉ាត់:
إِنَّ ٱلَّذِينَ لَا يُؤۡمِنُونَ بِٱلۡأٓخِرَةِ لَيُسَمُّونَ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةَ تَسۡمِيَةَ ٱلۡأُنثَىٰ
27. እነዚያ በመጪው ዓለም የማያምኑት መላዕክትን በእንስት ስም ይሰይማሉ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَمَا لَهُم بِهِۦ مِنۡ عِلۡمٍۖ إِن يَتَّبِعُونَ إِلَّا ٱلظَّنَّۖ وَإِنَّ ٱلظَّنَّ لَا يُغۡنِي مِنَ ٱلۡحَقِّ شَيۡـٔٗا
28. ለእነርሱም በእርሱ እውቀት የላቸውም። እነርሱ የሚከተሉት ጥርጣሬን ብቻ ነው:: ጥርጣሬ ደግሞ ሀቅን አይተካም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَأَعۡرِضۡ عَن مَّن تَوَلَّىٰ عَن ذِكۡرِنَا وَلَمۡ يُرِدۡ إِلَّا ٱلۡحَيَوٰةَ ٱلدُّنۡيَا
29. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከቁርኣን አፈንግጦና የዚችን ዓለም ኑሮ እንጂ ሌላ ከማይመኝ ሰው እራስህን አሽሽ::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ذَٰلِكَ مَبۡلَغُهُم مِّنَ ٱلۡعِلۡمِۚ إِنَّ رَبَّكَ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَن ضَلَّ عَن سَبِيلِهِۦ وَهُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱهۡتَدَىٰ
30. ይህ የእውቀታቸው ጣሪያ (መጨረሻ) ነው:: ጌታህ ግን መንገዱን የሳተውን ሁሉ አዋቂ ነው:: የተቀናውንም እንዲሁ አዋቂ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلِلَّهِ مَا فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِي ٱلۡأَرۡضِ لِيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَسَٰٓـُٔواْ بِمَا عَمِلُواْ وَيَجۡزِيَ ٱلَّذِينَ أَحۡسَنُواْ بِٱلۡحُسۡنَى
31. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የአላህ ነው:: እነዚያን ያጠፉትን በተግባራቸው ለመመንዳትና እነዚያን መልካም የሰሩትንም በመልካሟ (በገነት) ሊመነዳ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ٱلَّذِينَ يَجۡتَنِبُونَ كَبَٰٓئِرَ ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡفَوَٰحِشَ إِلَّا ٱللَّمَمَۚ إِنَّ رَبَّكَ وَٰسِعُ ٱلۡمَغۡفِرَةِۚ هُوَ أَعۡلَمُ بِكُمۡ إِذۡ أَنشَأَكُم مِّنَ ٱلۡأَرۡضِ وَإِذۡ أَنتُمۡ أَجِنَّةٞ فِي بُطُونِ أُمَّهَٰتِكُمۡۖ فَلَا تُزَكُّوٓاْ أَنفُسَكُمۡۖ هُوَ أَعۡلَمُ بِمَنِ ٱتَّقَىٰٓ
32. እነርሱም ከጥቃቅን ጥፋቶች በቀር ከባባድ ወንጀሎችንና አጸያፊ ተግባሮችን የራቁ ናቸው:: ጌታህ ምህረተ ሰፊ ነው:: እርሱ ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜም ሆነ በእናቶቻችሁ ማሕጸን ውስጥ ጽንሶች በሁናችሁበት ጊዜ ያውቃችኋል:: ስለዚህ እራሳችሁን አታሞግሱ:: እርሱ በትክክል የሚፈራውን ሰው ከሁሉም ይበልጥ አዋቂ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَفَرَءَيۡتَ ٱلَّذِي تَوَلَّىٰ
33. ያን ከእምነት የሸሸውን አየህን (እስቲ ንገረኝ)?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَعۡطَىٰ قَلِيلٗا وَأَكۡدَىٰٓ
34. ጥቂትን ብቻ ሰጥቶ ያቋረጠውን፤
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَعِندَهُۥ عِلۡمُ ٱلۡغَيۡبِ فَهُوَ يَرَىٰٓ
35, ለመሆኑ የሚያውቀው የሩቅ ሚስጢር አለውና እርሱንም ያያልን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَمۡ لَمۡ يُنَبَّأۡ بِمَا فِي صُحُفِ مُوسَىٰ
36. ወይስ በሙሳ ፅሁፍ ያለው አልተነገረውም?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِبۡرَٰهِيمَ ٱلَّذِي وَفَّىٰٓ
37. በኢብራሂም (ትእዛዛቱን) በፈፀመው ያለውስ አልተነገረዉምን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَّا تَزِرُ وَازِرَةٞ وِزۡرَ أُخۡرَىٰ
38. ይኸዉም ወንጀለኛ ነፍስ የሌላውን ነፍስ ወንጀል በፍጹም አትሸከምም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَن لَّيۡسَ لِلۡإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ
39. የሰው ልጅም የለፋበትን ብቻ እንጂ ሌላ የለዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَنَّ سَعۡيَهُۥ سَوۡفَ يُرَىٰ
40. የሰራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ثُمَّ يُجۡزَىٰهُ ٱلۡجَزَآءَ ٱلۡأَوۡفَىٰ
41. ከዚያም ጌታው ሙሉ ምንዳውን ይመነዳዋል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَنَّ إِلَىٰ رَبِّكَ ٱلۡمُنتَهَىٰ
42. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የሁሉም መጨረሻው ወደ ጌታህ ብቻ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَنَّهُۥ هُوَ أَضۡحَكَ وَأَبۡكَىٰ
43. እርሱ ያ ያሳቀና ያስለቀሰ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَأَنَّهُۥ هُوَ أَمَاتَ وَأَحۡيَا
44. እርሱ ያ የገደለና ሕያው ያደረገም ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាន់ណាច់ម៍
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ