Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ម៉ាអ៊ីដះ   អាយ៉ាត់:
قَالَ عِيسَى ٱبۡنُ مَرۡيَمَ ٱللَّهُمَّ رَبَّنَآ أَنزِلۡ عَلَيۡنَا مَآئِدَةٗ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ تَكُونُ لَنَا عِيدٗا لِّأَوَّلِنَا وَءَاخِرِنَا وَءَايَةٗ مِّنكَۖ وَٱرۡزُقۡنَا وَأَنتَ خَيۡرُ ٱلرَّٰزِقِينَ
114. «የመርየም ልጅ ዒሳም፡- ‹ጌታችን አላህ ሆይ! ከሰማይ ማዕድን አውርድልን ለእኛ ለመጀመሪያዎቻችንና ለመጭዎቹም ትውልዶች በዓል (የደስታ እለት) ካንተ የሆነችም ተዐምር ትሆንልን ዘንድ :: ሲሳይንም ለግሰን:: አንተ ከለጋሾች ሁሉ የበለጥክ ለጋሽ ነህና› አለ።»
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ ٱللَّهُ إِنِّي مُنَزِّلُهَا عَلَيۡكُمۡۖ فَمَن يَكۡفُرۡ بَعۡدُ مِنكُمۡ فَإِنِّيٓ أُعَذِّبُهُۥ عَذَابٗا لَّآ أُعَذِّبُهُۥٓ أَحَدٗا مِّنَ ٱلۡعَٰلَمِينَ
115. አላህም፡- «ማዕዷን አወርድላችኋለሁ:: ግና ከዚህ ተአምር በኋላ ከመካከላችሁ በእኔ ለካዱት ሁሉ በዓለማት ላይ ማንንም የማልቀጣውን አስከፊ ቅጣት እቀጣቸዋለሁ።» አለ።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَإِذۡ قَالَ ٱللَّهُ يَٰعِيسَى ٱبۡنَ مَرۡيَمَ ءَأَنتَ قُلۡتَ لِلنَّاسِ ٱتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَٰهَيۡنِ مِن دُونِ ٱللَّهِۖ قَالَ سُبۡحَٰنَكَ مَا يَكُونُ لِيٓ أَنۡ أَقُولَ مَا لَيۡسَ لِي بِحَقٍّۚ إِن كُنتُ قُلۡتُهُۥ فَقَدۡ عَلِمۡتَهُۥۚ تَعۡلَمُ مَا فِي نَفۡسِي وَلَآ أَعۡلَمُ مَا فِي نَفۡسِكَۚ إِنَّكَ أَنتَ عَلَّٰمُ ٱلۡغُيُوبِ
116. (መልዕክተኛች ሙሐመድ ሆይ!) አላህ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! ሰዎችን ‹እኔንና እናቴን ከአላህ ውጭ ሁለት አማልዕክት አድርጋችሁ ያዙን።› ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ የሚሆነውን አስታውስ:: ዒሳም አለ፡- «ክብርና ልዕልና ላንተ ብቻ ይሁን! ለእኔ ልለው የማይገባኝን ነገር ማለቴ ፈጽሞ አግባብ አይደለም:: ይህን ተናግሬ ከሆነም ታውቀዋለህ:: አንተ በውስጤ ያለውን ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ:: እኔ ግን ባንተ ውስጥ ያለውን አላውቅም:: አንተ ሩቅ ሚስጥራትን ሁሉ አዋቂ ነህና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
مَا قُلۡتُ لَهُمۡ إِلَّا مَآ أَمَرۡتَنِي بِهِۦٓ أَنِ ٱعۡبُدُواْ ٱللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمۡۚ وَكُنتُ عَلَيۡهِمۡ شَهِيدٗا مَّا دُمۡتُ فِيهِمۡۖ فَلَمَّا تَوَفَّيۡتَنِي كُنتَ أَنتَ ٱلرَّقِيبَ عَلَيۡهِمۡۚ وَأَنتَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ شَهِيدٌ
117. «የነገርኳቸው ያን ያዘዝከኝን ብቻ ነው:: ‹የእኔም የእናንተም ጌታ የሆነውን አላህን ብቻ አምልኩ ነው› ያልኳቸው:: በመካከላቸው በነበርኩበት ወቅት ስለ እነርሱ መስካሪ ነበርኩ:: እንዳርግ ካደረግከኝ በኋላ ግን የእነርሱ ጠባቂና ተቆጣጣሪ አንተው ብቻ ነበርክ:: አንተ በሁሉም ነገር ላይ መስካሪ ነህና።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِن تُعَذِّبۡهُمۡ فَإِنَّهُمۡ عِبَادُكَۖ وَإِن تَغۡفِرۡ لَهُمۡ فَإِنَّكَ أَنتَ ٱلۡعَزِيزُ ٱلۡحَكِيمُ
118. «ብትቀጣቸው እነርሱ የአንተው ባሮችህ ናቸው:: ብትምራቸው ደግሞ አንተ ኃያልና ጥበበኛ ነህ።» ይላል።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ ٱللَّهُ هَٰذَا يَوۡمُ يَنفَعُ ٱلصَّٰدِقِينَ صِدۡقُهُمۡۚ لَهُمۡ جَنَّٰتٞ تَجۡرِي مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدٗاۖ رَّضِيَ ٱللَّهُ عَنۡهُمۡ وَرَضُواْ عَنۡهُۚ ذَٰلِكَ ٱلۡفَوۡزُ ٱلۡعَظِيمُ
119. አላህም እንዲህ ይላል፡- «ይህ ቀን እውነቱ ለእውነተኞች የሚጠቅምበት ቀን ነው::» ለእውነተኞች ከስሮቿ ወንዞች የሚፈሱባት ገነት ተዘጋጅቶላቸዋል:: በውስጧም ለዝንተ ዓለም ይኖራሉ:: አላህ በእነርሱ ተግባር ተደስቷል:: እነርሱም በእርሱ ችሮታ ተደስተዋል:: ይህ ታላቅ ስኬት ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَمَا فِيهِنَّۚ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيۡءٖ قَدِيرُۢ
120. የሰማያት የምድርና በውስጣቸው ያሉ ፍጡራን ሁሉ ባለቤትነት የአላህ ብቻ ነው:: እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់ម៉ាអ៊ីដះ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ