Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: មូហាំម៉ាត់   អាយ៉ាត់:
وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَوۡلَا نُزِّلَتۡ سُورَةٞۖ فَإِذَآ أُنزِلَتۡ سُورَةٞ مُّحۡكَمَةٞ وَذُكِرَ فِيهَا ٱلۡقِتَالُ رَأَيۡتَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٞ يَنظُرُونَ إِلَيۡكَ نَظَرَ ٱلۡمَغۡشِيِّ عَلَيۡهِ مِنَ ٱلۡمَوۡتِۖ فَأَوۡلَىٰ لَهُمۡ
20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ያመኑት ሰዎች (ለዲን ለመታገል ግፊት ያለበት)« የቁርኣን ምዕራፍ አይወረድም ኖሯልን?» ይላሉ:: የጠነከረም ምዕራፍ በወረደና በውስጡም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅና በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የሆነ መከራ በእርሱ ላይ እንደወደቀበት ሰው አስተያያት ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ:: ለእነርሱው ተገባቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
طَاعَةٞ وَقَوۡلٞ مَّعۡرُوفٞۚ فَإِذَا عَزَمَ ٱلۡأَمۡرُ فَلَوۡ صَدَقُواْ ٱللَّهَ لَكَانَ خَيۡرٗا لَّهُمۡ
21. ታዛዥነትና መልካም ንግግር ይሻላቸዋል:: ትዕዛዙም ቁርጥ በሆነ ጊዜ ለአላህ ትእዛዝ እውነተኞች በሆኑ ኖሮ ለእነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَهَلۡ عَسَيۡتُمۡ إِن تَوَلَّيۡتُمۡ أَن تُفۡسِدُواْ فِي ٱلۡأَرۡضِ وَتُقَطِّعُوٓاْ أَرۡحَامَكُمۡ
22. ብትሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أُوْلَٰٓئِكَ ٱلَّذِينَ لَعَنَهُمُ ٱللَّهُ فَأَصَمَّهُمۡ وَأَعۡمَىٰٓ أَبۡصَٰرَهُمۡ
23. እነዚህ እነዚያ አላህ የረገማቸው ያደነቆራቸዉም ዓይኖቻቸውንም ያወራቸው ናቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَفَلَا يَتَدَبَّرُونَ ٱلۡقُرۡءَانَ أَمۡ عَلَىٰ قُلُوبٍ أَقۡفَالُهَآ
24. ቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አሉባቸውን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
إِنَّ ٱلَّذِينَ ٱرۡتَدُّواْ عَلَىٰٓ أَدۡبَٰرِهِم مِّنۢ بَعۡدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمُ ٱلۡهُدَى ٱلشَّيۡطَٰنُ سَوَّلَ لَهُمۡ وَأَمۡلَىٰ لَهُمۡ
25. እነዚያ ለእነርሱ ቅኑው መንገድ ከተብራራላቸው በኋላ ወደ ኋላቸው የተመለሱት ሰይጣን መቀልበሳቸውን ለእነርሱ ሸለመላቸው:: ለእነርሱም አዘናጋቸው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمۡ قَالُواْ لِلَّذِينَ كَرِهُواْ مَا نَزَّلَ ٱللَّهُ سَنُطِيعُكُمۡ فِي بَعۡضِ ٱلۡأَمۡرِۖ وَٱللَّهُ يَعۡلَمُ إِسۡرَارَهُمۡ
26. ይህ እነርሱ ለእነዚያ አላህ ያወረደውን ለጠሉት «በነገሩ ከፊሉን እንታዘዛችኃለን» ያሉ በመሆናቸው ነው:: አላህም መደበቂያቸውንም ያውቃል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَكَيۡفَ إِذَا تَوَفَّتۡهُمُ ٱلۡمَلَٰٓئِكَةُ يَضۡرِبُونَ وُجُوهَهُمۡ وَأَدۡبَٰرَهُمۡ
27. መላዕክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን የሚመቱ ሲሆኑ በገደሏቸው ጊዜ (ሁኔታቸው እንዴት ይሆናል?)
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمُ ٱتَّبَعُواْ مَآ أَسۡخَطَ ٱللَّهَ وَكَرِهُواْ رِضۡوَٰنَهُۥ فَأَحۡبَطَ أَعۡمَٰلَهُمۡ
28. ይህ እነርሱ አላህን ያስቆጣውን ነገር ሁሉ ስለተከተሉ ውዴታውንም ስለጠሉ ነው:: ስለዚህ ስራዎቻቸውን አበላሸባቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَمۡ حَسِبَ ٱلَّذِينَ فِي قُلُوبِهِم مَّرَضٌ أَن لَّن يُخۡرِجَ ٱللَّهُ أَضۡغَٰنَهُمۡ
29. እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው ሰዎች በሙስሊሞች ላይ የነበራቸዉን ቂሞቻቸውን አላህ አለማውጣቱን ጠረጠሩን?
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: មូហាំម៉ាត់
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ