Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អះកហ្វ   អាយ៉ាត់:
۞ وَٱذۡكُرۡ أَخَا عَادٍ إِذۡ أَنذَرَ قَوۡمَهُۥ بِٱلۡأَحۡقَافِ وَقَدۡ خَلَتِ ٱلنُّذُرُ مِنۢ بَيۡنِ يَدَيۡهِ وَمِنۡ خَلۡفِهِۦٓ أَلَّا تَعۡبُدُوٓاْ إِلَّا ٱللَّهَ إِنِّيٓ أَخَافُ عَلَيۡكُمۡ عَذَابَ يَوۡمٍ عَظِيمٖ
21. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በአል አሕቃፍ የነበረው የዓድ ወንድም የሆነው ሁድ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላም አስፈራሪዎች ባለፉት መልኩ «ከአላህ ውጪ ሌሎች አማልክትን አታምልኩ:: የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁ።» በሚል ሲያስጠነቅቃቸው (የነበረውን አስታውስ)
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالُوٓاْ أَجِئۡتَنَا لِتَأۡفِكَنَا عَنۡ ءَالِهَتِنَا فَأۡتِنَا بِمَا تَعِدُنَآ إِن كُنتَ مِنَ ٱلصَّٰدِقِينَ
22. «ከአማልክቶቻችን ልታሸሸን መጣህን? እውነተኛ ከሆንክ ያንን የምታስፈራራን ቅጣት አሁን እንዲከሰት አድርግ» አሉት።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
قَالَ إِنَّمَا ٱلۡعِلۡمُ عِندَ ٱللَّهِ وَأُبَلِّغُكُم مَّآ أُرۡسِلۡتُ بِهِۦ وَلَٰكِنِّيٓ أَرَىٰكُمۡ قَوۡمٗا تَجۡهَلُونَ
23. «የቅጣቱ መከሰቻ ትክከለኛ ወቅት እውቀት ያለው ከአላህ ዘንድ ብቻ ነው:: የተላኩበትን መልዕክት ብቻ አደርስላችኋለሁ:: ግና እንደማያችሁ መሀይማን ህዝቦች ናችሁ።» አላቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَلَمَّا رَأَوۡهُ عَارِضٗا مُّسۡتَقۡبِلَ أَوۡدِيَتِهِمۡ قَالُواْ هَٰذَا عَارِضٞ مُّمۡطِرُنَاۚ بَلۡ هُوَ مَا ٱسۡتَعۡجَلۡتُم بِهِۦۖ رِيحٞ فِيهَا عَذَابٌ أَلِيمٞ
24. ለቅጣት የተላከባቸውን (ዳመና) ወደ ሸለቆዎቻቸው አቅጣጫ ሲጓዝ ባዩ ጊዜ «ይህ ዝናብ የሚያወርድልን ዳመና ነው» አሉ:: አይደለም። ይልቁንም ያ በፍጥነት ይከሰት ዘንድ የጠየቃችሁት ቅጣት ነው:: አሳማሚ ቅጣት ያዘለ ንፋስ ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
تُدَمِّرُ كُلَّ شَيۡءِۭ بِأَمۡرِ رَبِّهَا فَأَصۡبَحُواْ لَا يُرَىٰٓ إِلَّا مَسَٰكِنُهُمۡۚ كَذَٰلِكَ نَجۡزِي ٱلۡقَوۡمَ ٱلۡمُجۡرِمِينَ
25. በጌታዋ ትዕዛዝ ሁሉን ነገር ታጠፋለች» (አላቸው)፡፡ ባዶ ቤቶቻቸው እንጂ ሌላ ነገር የማይታይ ሆነው አነጉ:: አመጸኞች ህዝቦችን በዚህ መልኩ እንቀጣለን::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ مَكَّنَّٰهُمۡ فِيمَآ إِن مَّكَّنَّٰكُمۡ فِيهِ وَجَعَلۡنَا لَهُمۡ سَمۡعٗا وَأَبۡصَٰرٗا وَأَفۡـِٔدَةٗ فَمَآ أَغۡنَىٰ عَنۡهُمۡ سَمۡعُهُمۡ وَلَآ أَبۡصَٰرُهُمۡ وَلَآ أَفۡـِٔدَتُهُم مِّن شَيۡءٍ إِذۡ كَانُواْ يَجۡحَدُونَ بِـَٔايَٰتِ ٱللَّهِ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُواْ بِهِۦ يَسۡتَهۡزِءُونَ
26. ለእናንተ ያልሰጠነውን ኃይልና ምቾት ለእነርሱ ሰጥተናል:: መሰሚያ ጆሮዎችን፤ መመልከቻ ዓይኖችን እና ማሰቢያ አእምሮንም ለግሰናቸዋል:: ግና ጆሮዎቻቸዉም፤ ዓይኖቻቸዉም፤ አእምሮዎቻቸዉም የፈየዷቸው ነገር አልነበረም:: የአላህን አናቅጽ ያስተባብሉ ነበርና:: በመሆኑም በእነርሱ ላይ ያ ያፌዙበት በነበረው ቅጣት ወረደባቸው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلَقَدۡ أَهۡلَكۡنَا مَا حَوۡلَكُم مِّنَ ٱلۡقُرَىٰ وَصَرَّفۡنَا ٱلۡأٓيَٰتِ لَعَلَّهُمۡ يَرۡجِعُونَ
27. በዙሪያችሁ የነበሩ ከተሞችንም አጠፋን:: ይመለሱ ዘንድም ተደጋጋሚ ታዐምራትን አሳይተናቸው ነበር::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
فَلَوۡلَا نَصَرَهُمُ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُواْ مِن دُونِ ٱللَّهِ قُرۡبَانًا ءَالِهَةَۢۖ بَلۡ ضَلُّواْ عَنۡهُمۡۚ وَذَٰلِكَ إِفۡكُهُمۡ وَمَا كَانُواْ يَفۡتَرُونَ
28. እነዚያ መቃረቢያ ይሆናቸው ዘንድ ከአላህ ሌላ በረዳትነት የያዟቸው አማልክት በመከራቸው ወቅት ለምን አልረዷቸዉም? ይልቁንም ከእነርሱ ራቁ:: ይህ ሀሰታቸውና ይቀጥፉት የነበረው ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាល់អះកហ្វ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ