Check out the new design

ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា * - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

PDF XML CSV Excel API
Please review the Terms and Policies

ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាន់នូរ   អាយ៉ាត់:
رِجَالٞ لَّا تُلۡهِيهِمۡ تِجَٰرَةٞ وَلَا بَيۡعٌ عَن ذِكۡرِ ٱللَّهِ وَإِقَامِ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءِ ٱلزَّكَوٰةِ يَخَافُونَ يَوۡمٗا تَتَقَلَّبُ فِيهِ ٱلۡقُلُوبُ وَٱلۡأَبۡصَٰرُ
37. አላህን ከማውሳትና ሶላትን ከመስገድ ዘካንም ከመስጠት ንግድም ሽያጭም የማያታልላቸው ልቦችና ዓይኖች በእርሱ የሚገላበጡበትን ቀን የሚፈሩ የሆኑ ሰዎች ያጠሩታል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
لِيَجۡزِيَهُمُ ٱللَّهُ أَحۡسَنَ مَا عَمِلُواْ وَيَزِيدَهُم مِّن فَضۡلِهِۦۗ وَٱللَّهُ يَرۡزُقُ مَن يَشَآءُ بِغَيۡرِ حِسَابٖ
38. አላህም የሰሩትን ስራ መልካሙን ሊመነዳቸው ከችሮታዉም ሊጨምርላቸው ያጠሩታል:: አላህም ለሚሻው ሁሉ ያለ ግምት ይሰጣል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَٱلَّذِينَ كَفَرُوٓاْ أَعۡمَٰلُهُمۡ كَسَرَابِۭ بِقِيعَةٖ يَحۡسَبُهُ ٱلظَّمۡـَٔانُ مَآءً حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَهُۥ لَمۡ يَجِدۡهُ شَيۡـٔٗا وَوَجَدَ ٱللَّهَ عِندَهُۥ فَوَفَّىٰهُ حِسَابَهُۥۗ وَٱللَّهُ سَرِيعُ ٱلۡحِسَابِ
39. እነዚያም በአላህ የካዱት ሰዎች መልካም ስራዎቻቸው በበረሃ ሜዳ እንዳለ ሲሪብዱ ነው:: ሲሪብዱ ውሃ የጠማው ሰው እንደውሃ አስቦት በቀረቡት ጊዜ ምንም ነገር ሆኖ እንደማያገኘው ነው፤ አላህንም እስፍራው ዘንድ ያገኘዋል:: ምርመራውንም ይሞላለታል፤ አላህም ምርመራው ፈጣን ነው።
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَوۡ كَظُلُمَٰتٖ فِي بَحۡرٖ لُّجِّيّٖ يَغۡشَىٰهُ مَوۡجٞ مِّن فَوۡقِهِۦ مَوۡجٞ مِّن فَوۡقِهِۦ سَحَابٞۚ ظُلُمَٰتُۢ بَعۡضُهَا فَوۡقَ بَعۡضٍ إِذَآ أَخۡرَجَ يَدَهُۥ لَمۡ يَكَدۡ يَرَىٰهَاۗ وَمَن لَّمۡ يَجۡعَلِ ٱللَّهُ لَهُۥ نُورٗا فَمَا لَهُۥ مِن نُّورٍ
40. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ወይም መጥፎ ስራዎቻቸው ከበላዩ ማዕበል ከበላዩ ደመና ያለበት ማዕበል በሚሸፍነው ጥልቅ ባህር ውስጥ እንዳሉ ጨለማዎች ነው:: እነዚያ ከፊላቸው ከከፊሉ በላይ ድርብርብ የሆኑ ጨለማዎች ናቸው:: በዚህች የተሞከረ ሰው እጁን ባወጣ ጊዜ ሊያያት አይደርስም:: አላህ ለእርሱ ብርሃንን ያላደረገለት ሰው ሁሉ ለእርሱ ምንጊዜም ምንም ብርሃን የለዉም::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يُسَبِّحُ لَهُۥ مَن فِي ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِ وَٱلطَّيۡرُ صَٰٓفَّٰتٖۖ كُلّٞ قَدۡ عَلِمَ صَلَاتَهُۥ وَتَسۡبِيحَهُۥۗ وَٱللَّهُ عَلِيمُۢ بِمَا يَفۡعَلُونَ
41. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ በሰማያትና በምድር ላይ ያለ ሁሉ በራሪዎችም ክንፎቻቸውን በአየር ላይ ያንሳፈፉ ሆነው ለእርሱ የሚያጠሩ መሆናቸውን አላወቅህምን? ሁሉም ስግደቱንና ማጥራቱን በእርግጥ አወቀ:: አላህ የሚሰሩትን ሁሉ አዋቂ ነውና::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۖ وَإِلَى ٱللَّهِ ٱلۡمَصِيرُ
42. የሰማያትም ሆነ የምድር ግዛት የአላህ ነው:: መመለሻም ወደ አላህ ነው::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
أَلَمۡ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يُزۡجِي سَحَابٗا ثُمَّ يُؤَلِّفُ بَيۡنَهُۥ ثُمَّ يَجۡعَلُهُۥ رُكَامٗا فَتَرَى ٱلۡوَدۡقَ يَخۡرُجُ مِنۡ خِلَٰلِهِۦ وَيُنَزِّلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مِن جِبَالٖ فِيهَا مِنۢ بَرَدٖ فَيُصِيبُ بِهِۦ مَن يَشَآءُ وَيَصۡرِفُهُۥ عَن مَّن يَشَآءُۖ يَكَادُ سَنَا بَرۡقِهِۦ يَذۡهَبُ بِٱلۡأَبۡصَٰرِ
43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ደመናን የሚነዳ መሆኑን አላየህምን? ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፤ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፤ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ሆኖ ታየዋለህ፤ ከሰማይም ከደመናም በውስጡ ካሉት ጋራዎችም በረዶን ያወርዳል:: በእርሱም የሚሻውን ሰው በጉዳት ይነካል:: ከሻዉም ሰው ላይ ይመልሰዋል:: የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል::
តាហ្វសៀរជាភាសា​អារ៉ាប់ជាច្រេីន:
 
ការបកប្រែអត្ថន័យ ជំពូក​: អាន់នូរ
សន្ទស្សន៍នៃជំពូក លេខ​ទំព័រ
 
ការបកប្រែអត្ថន័យគួរអាន - ការបកប្រែជាភាសាអាំហារីច - អាឃាដេមីអាហ្វ្រិកា - សន្ទស្សន៍នៃការបកប្រែ

ការបកប្រែដោយ ម៉ូហាំម៉ាត់​ សេន សហ៊ឌីន។ ចេញផ្សាយដោយ វិទ្យាស្ថានអាហ្វ្រិក។

បិទ